ኢኮኖሚውን ለመታደግ የአዲሱ መንግስት የቤት ስራዎች

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአንድ በኩል ብዙ ተስፋዎች የሚስተዋሉበት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ትላልቅ ስጋቶች ያንዣበቡበት ስለመሆኑ የዘርፉ ምሁራን ያስረዳሉ። የለውጡ መንግስት ኢኮኖሚው ከገባበት ቀውስ ለማውጣት በ2011 ይፋ ያደረገው እና በ2012 ዓ.ም ወደ ትግበራ የገባው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመሰረታዊነት ለመፍታት እንደሚያስችል ተስፋ የተጣለበት ነው።

ይህን የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ መንግስት ተጨባጭ እርምጃዎችን በመውሰድ ግብርናን በማዘመን ረገድ የሰራቸው ስራዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው። ለግብርና አስፈላጊ የሆኑ በርካታ የግብርና ግብዓቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ በማድረግ ግብርናውን የማዘመን ስራው መሰረት እንዲጥል መደረጉን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ያብራራሉ።

መታረስ ሲገባቸው ታጥረው የቆዩ መሬቶች እንዲታረሱ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ሰፋፊ ስራዎች ተሰርተዋል። የፋይናንስ ዘርፉን በማሻሻል ረገድ የተሰሩ ስራዎችም ኢኮኖሚውን ለማሻሻል ትልቅ መሰረት የሚጥሉ እና ተስፋን ያለመለሙ ነበሩ። የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ተስፋ ብቻም ሳይሆን ስጋቶችም ያንዣበቡበት ነው።

በፍጥነት እየጋለበ የሚገኘው የዋጋ ንረት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ተግዳሮቶች ስጋቶች ያንዣበቡበት መሆኑን ያመላክታሉ። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶች የተለያዩ መንስኤዎች እንዳሉት የሚናገሩት የምጣኔ ሀብት ምሁራን በቀጣይ መንግስት ኢኮኖሚውን ከተግዳሮቶች ለማላቀቅ ጠንክሮ መስራት እንዳለበት ይጠቁማሉ።

በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህር የሆኑት ዶክተር ተስፋዬ ጮፋና እንደሚናገሩት፤ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግሮች መንስኤዎች ከፖለቲካው የሚመነጭ ነው። ለረጅም ዓመታት የኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ተገንብቷል። ይህ ደግሞ በገበያ ውድድር ሳይሆን አድሎ ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ ፈጥሯል። ይህም አሁን በኢኮኖሚ ዘርፍ ለሚስተዋሉ ቀውሶች መሰረት ናቸው።

ኢኮኖሚው የኪራይ ሰብሳቢዎች ኢኮኖሚ ስለነበር አንዳንዶች ሳይሰሩ የሚበለጽጉበት፣ ሳይሰሩ ባለኩባንያ የሚሆኑበት የኢኮኖሚ አሰራር ተፈጥሮ እንደነበር የሚያስታውሱት ዶክተር ተስፋዬ ይህ ሁኔታ ተጠረቃቅሞ አሁን ያለውን የኢኮኖሚ ችግሮችን ፈጥሯል ይላሉ።

በሌላ በኩል መንግስት ለረጅም ዓመታት መልካም አስተዳደር እና ዴሞክራሲ ግንባታ ብሎ ቢያወራም እነዚህ ነገሮች ተግባራዊ አልተደረጉም። መልካም አስተዳደር እና ዴሞክራሲ መገንባት አልተቻለም። መልካም አስተዳደር እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ከተቋማት የሚመነጩ ናቸው። እነዚህ ተቋማት አልተገነቡም። ህዝብን የሚያገለግሉ፣ ህዝብ የሚተማመንባቸው ተቋማት እንዳይገነቡ ተደርገዋል። ለህዝብ ታማኝ የሆነ ጠንካራ ተቋም ከተገነባ ኪራይ ሰብሳቢ ኢኮኖሚ ለመገንባት እና ኪራይ ለመሰብሰብ ስለማይቻል ጠንካራ ተቋም እና ዴሞክራሲ እንዳይኖር ተደርጓል። ይህም ዛሬ የሚስተዋሉ የኢኮኖሚ ችግሮች እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ሲሉ ያብራራሉ።

እንደ ዶክተር ተስፋዬ ገለጻ፤ የትምህርት ሥርዓቱ ተወዳዳሪ፣ ተግባር ተኮር እና ጠንካራ የትምህርት ሥርዓት አልተገነባም የሚሉት ዶክተር ተስፋዬ፤ የትምህርት ሥርዓቱ ለፖለቲካ ፍጆታ ነበር። የትምህርት ቤቶች እና የዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ማብዛት ላይ ያተኮረ ነበር። የትምህርት ቤቶች እና የዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ማብዛት መልካም ሆኖ ሳለ በየጊዜ እያጠናከሩ መሄድ ያስፈልግ ነበር። ትምህርቱ በካድሬዎች የሚመሩ የትምህርት ተቋማት ማዕከል ሆኗል። ይህም ለትምህርት ሥርዓት ችግር መንስኤ የሆነ ሲሆን ሀገሪቱን አሁን ላለው የኢኮኖሚ ቀውስ ዳርጓል።

በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ከኢኮኖሚ ችግሮች ለመውጣት ከተለያዩ አካላት የሚበደሩትን ብድሮች በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን የሚያነሱት ዶክተር ተስፋዬ፤ ኢትዮጵያ ከተለያዩ አበዳሪ አካላት የምትወስዳቸውን ብድሮች በምን ላይ እየዋለ እንደነበር በአግባቡ ክትትል ሲደረግ አልነበረም ይላሉ። ብድሮች ለኪራይ ሰብሳቢዎች መጠቀሚያ ሲሆኑ ነበር። ከዚያ ባሻገር ብድር ከሚሰጡ አካላት ጋር በእጅአዙር የብድር ጥቅም ግንኙነቶች ነበሩ። በበለጠ ሀገሪቱ የተጠቀመችበት ሳይሆን ውስን ግለሰቦች የተጠቀሙበት የብድር ሁኔታ ስለነበር። አሁን የሚስተዋሉ የኢኮኖሚ ችግሮች ተከስተዋል ይላሉ።

በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህር የሆኑት ዶክተር ሞላ አለማየሁ በበኩላቸው፤ መንግስት ከኢኮኖሚ አንጻር መስራት ያለባቸው የሚታወቁ የመንግስት ሀላፊነቶች አሉ። የስራ እድል ፈጠራ፣

 ተስፋዬ፤ የትምህርት ሥርዓቱ ለፖለቲካ ፍጆታ ነበር። የትምህርት ቤቶች እና የዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ማብዛት ላይ ያተኮረ ነበር። የትምህርት ቤቶች እና የዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ማብዛት መልካም ሆኖ ሳለ በየጊዜ እያጠናከሩ መሄድ ያስፈልግ ነበር። ትምህርቱ በካድሬዎች የሚመሩ የትምህርት ተቋማት ማዕከል ሆኗል። ይህም ለትምህርት ሥርዓት ችግር መንስኤ የሆነ ሲሆን ሀገሪቱን አሁን ላለው የኢኮኖሚ ቀውስ ዳርጓል።

በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህር የሆኑት ዶክተር ሞላ አለማየሁ በበኩላቸው፤ መንግስት ከኢኮኖሚ አንጻር መስራት ያለባቸው የሚታወቁ የመንግስት ሀላፊነቶች አሉ። የስራ እድል ፈጠራ፣ልማትና እድገትን ማረጋገጥ፣ የሀገሪቱን ንግድ ጤናማ ማድረግ የመንግስት ሃላፊነቶች ናቸው። መንግስት ሃላፊነቱን በአግባቡ አለመወጣት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚስተዋለው የኢኮኖሚ ቀውስ ዋነኛው ምክንያት ነው ይላሉ።

መንግስት በአንድ ኢኮኖሚ ላይ በአመዛኙ ኢኮኖሚውን የማሳለጥ ሃላፊነት በተለይም የገበያውን እና የንግድ ሥርዓቱን የማሳለጥ ሃላፊነት፤ ከዚያ አለፍ ብሎ የንግድ ሥርዓት ሲዛባ የማስተካከል ሃላፊነት የመንግስት ሃላፊነት ነው። መንግስት እነዚህን ሃላፊነቶችን በአግባቡ ባለመወጣቱ የተከማቹ ችግሮች አሁን የሚስተዋለው የኢኮኖሚ ቀውስ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል የሚሉት ዶክተር ሞላ ይህም ጤናማ የንግድ እንቅስቃሴ እንዳይኖር አድርጎታል።

በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በመፍታት ስጋቶችን ለመቀነስ እና እድሎችን ለማስፋት የተለያዩ እርምጃዎች መወሰድ እንዳለባቸው የዘርፉ ልሂቃን የተለያዩ ምክረ ሃሳቦችን ያስቀምጣሉ።

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ ማህበር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ነባራዊ ሁኔታን አስመልክቶ ባሳተመው ህትመት፤ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ አሁንም መልካም ተስፋዎች የሚታዩበት መሆኑን በመግለጽ የሚስተዋልበትን መንገራገጮች በማለፍ ውጤት ለማስመዝገብ ሊወሰዱ የሚገቡ የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎችን አመላክቷል። ሊወሰዱ የሚገቡ

 እርምጃዎችንም በሶስት ከፍሎ አስቀምጧል። ከማክሮ ኢኮኖሚ አንጻር፣ ከከተሜነት እና ከልማት አንጻር እንዲሁም ከህዝብ ቁጥር መጨመርና እንቅስቃሴ ጋር ተያያዥነት ያላቸው እርምጃዎችን አመላክቷል።

እንደ ማህበሩ ምክረ ሃሳብ መሰረት ከማክሮ ኢኮኖሚ ልማት አንጻር ወደ አምራች ዘርፉ መዋቅራዊ ሽግግርን ለማሳደግ የዘርፉን ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ያለመ ልዩ የድጋፍ መርሃ ግብር ያስፈልጋል። በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ለኢንተርፕራይዞች የሚደረገው የድጋፍ ሥርዓት ኢንተርፕራይዞቹ የሚያ ጋጥሟቸውን አደጋዎችና ውድድሮች ግምት ውስጥ ሳያስገባ ወጥ ነው።

የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ከውጭ ከሚገቡ ምርቶች ከፍተኛ ፉክክር ይገጥማቸዋል። ከዚህም በላይ ከውጭ ማስገባትን በመቀጠሉ ለውድ ሎጅስቲክስ ተጋላጭ ነው። ስለሆነም እነሱ በሚያጋጥሟቸው ልዩ ተግዳሮቶች ላይ በመመርኮዝ ለዘርፎች የተለየ የድጋፍ ሥርዓት መንደፍ ያስፈልጋል። ይህ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን በስራ ፣ በሀገር ውስጥ ምርት እና በወጪ ንግድ ውስጥ ያለውን ድርሻ ከፍ ያደርገዋል።

በግሉ ዘርፍ ወደሚመሩ ልማት መሸጋገርም ኢኮኖሚውን ወደፊት ለማራመድ ሊወሰዱ ከሚገቡ ማክሮ ኢኮኖሚያዊ እርምጃዎች መካከል ተጠቃሽ መሆኑን የጠቆመው ማህበሩ፤ በመንግስት እጅ ሰፊ የሀብት ክምችት መብዛት እና የመንግስት

 ኢንቨስትመንቶች እየሰፋ መሄድ ኢኮኖሚው ውጤታማ እንዳይሆን ሊያደርግ ይችላል። በመሆኑም ባለፉት ዓመታት የተጀመረውን ልማት ግለቱን እና ፍጥነቱን ጠብቆ ለማስቀጠል ወደ የግል ዘርፍ መሪ ኢንቨስትመንት የመሸጋገርን አስፈላጊነት ጠቁሟል።

መንግሥት የግሉን ዘርፍ የዕድገትና የልማት ሞተር ለማድረግ የገባውን ቃል ደጋግሞ ቢገልጽም ፣ የግሉ ዘርፍ የብድርና የውጭ ምንዛሪ ተደራሽነትን የሚሻሙ የመንግስት ኢንቨስትመንቶች በመቀጠላቸው የግሉ ዘርፍ የመሪነት ሚና በመረከብ ረገድ ብዙም ለውጦች አልታዩም። የእድገቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የግሉ ዘርፍ የፋይናንስ ችግሮችን መፍታት የግድ ነው።

የሠራተኛውን ክህሎቶች ከኢንዱስትሪዎች ፍላጎት ጋር ማጣጣም ሌላኛው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ነው። በየዓመቱ ከቴክኒክና ሙያ ተቋማትና ከዩኒቨርሲቲዎች ተመርቀው የሚወጡ በርካታ ወጣቶች ቢኖሩም በከተማም ሆነ በገጠር ከፍተኛ ሥራ አጥነት፣ ተገቢውን ክፍያ አለማግኘት፣ እንዲሁም ገበያው ውስጥ ያለው የክህሎት አለመመጣጠን ጣልቃ ገብነትን የሚፈልግ ቁልፍ ተግዳሮት ነው። ደግሞ እየተመረቱ ያሉት ክህሎቶች በኢኮኖሚው ውስጥ ኢንዱስትሪዎች የሚፈልጓቸው ክህሎቶች አይደሉም። ከዩኒቨርሲቲዎች የሚወጡ ተመራቂዎች ክህሎት እና ኢንዱስትሪዎች የሚፈልጉት ክህሎት የሚጣጣሙ እየሆኑ አይደለም። በመሆኑም ሁለቱ የሚጣጣሙበትን መንገድ ማመቻቸት ያስፈልጋል።

እንደ ማህበሩ ምክረ ሃሳብ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ የዋጋ ግሽበትን እያባባሱ ያሉ ምክንያቶች መመርመርም ሌላኛው ትኩረት የሚሻ ማክሮ ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ነው። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ሸማቾችን የሚፈታተን ከመሆን ባሻገር ኩባንያዎችንም እየተፈታተነ ያለ ነው። የዋጋ ግሽበቱን ተከትሎ በየወቅቱ ለሰራተኞቻቸው ደመወዝ ለመጨመር ይገደዳሉ። በዚህም ምክንያት ተወዳዳሪነታቸው አደጋ ውስጥ እየወደቀ ነው። የዋጋ ንረትን ለመግታት ነገሮችን ከግምት ያስገባ የገንዘብ ፖሊሲ ቁልፍ ሚና ይጫወታል።

በተጨማሪም በኢኮኖሚው ላይ ሚና ሳይኖ ራቸው የዋጋ ግሽበትን የሚያባብሱ የመንግሥት ኢንቨስትመንቶችን መፈተሽ ያስፈልጋል። የግብርና ምርታማነትን ማሻሻል የምግብ ሸቀጦች የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ያለው ሚና ከፍ ያለ በመሆኑ ይህን ለማሻሻል መንግስት እያደረገ ያለው ጣልቃ ገብነት መልካም ነው። ጣልቃ ገብነቱም ከምግብ ዋጋ ግሽበት ጋር በቀጥታ የተገናኘ በመሆኑ ወሳኝ ነው። ለእነዚህ ሁሉ ጣልቃ ገብነቶች በመጀመሪያ በሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት አባባሽ ምክንያቶች ዙሪያ የምርመራ ጥናት ማካሄድ ይመከራል።

የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህሩ ዶክተር ሞላ አለማየሁ የኢኮኖሚክስ ማህበርን ምክረ ሃሳብ ያጠናክራሉ። አዲስ የሚመሰረተው መንግስት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ በአግባቡ በመረዳት እነዚህን ችግሮችን ለመፍታት ራሱን ማዘጋጀት አለበት። የረጅም እና የአጭር ጊዜ እቅዶችን አዘጋጅቶ ሃላፊነቶችን ሊወጣ በሚችል አኳኋን ራሱን ማዘጋጀት እና ማደራጀትም አለበት።

በኢኮኖሚው ውስጥ የተፈጠሩ ችግሮችን መለየት አለበት። ከስራ አጥነት፣ ከዋጋ ግሽበት ፣ የሀገሪቱን የንግድ ሚዛን ከማመጣጠን አኳያ የተፈጠሩ ችግሮችን መለየት አለበት የሚሉት ዶክተር ሞላ፤ ችግሮቹ ከተለዩ በኋላ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ከዚያ ሁለተኛ የሚመጡትን ችግሮችን ለይቶ መንቀሳቀስ አለበት። ለዚህ ደግሞ አስፈላጊው ዝግጅት እና መዋቅራዊ ተግባቦት ሊኖረው ይገባል ይላሉ።

ለህዝቡ ቅርብ የሆኑ ተቋማዊ መዋቅሮችን መፍጠር ያስፈልጋል። በአሁኑ ወቅት ኢኮኖሚያዊ አሻጥሮች ተፈጠሩ ተብሎ የሚጠቀሱ ችግሮችን ቀድሞ ለመቆጣጠር የሚያስችል አደረጃጀቶች ባለመኖራቸው

 የተፈጠሩ ናቸው። የንግድ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ከህግ ውጪ ሲንቀሳቀሱ ክትትል እና ቁጥጥር የሚያደርግ እና ወደ መስመር የሚያስገባ ተቋማዊ አወቃቀሮች ቢኖሩ ይህ ሁሉ ችግር ላይፈጠር ይችል ነበር። አሁንም ችግሩን ለመቅረፍ ተቋማዊ ችግሮችን መፍታት የግድ ነው ይላሉ።

እንደ ዶክተር ሞላ የዋጋ ግሽበት በዘመቻ ሳይሆን በጥናት ላይ በተመረኮዘ እርምጃ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል የሚለውን የኢኮኖሚክስ ማህበርን ምክረ ሃሳብ ያጠናክራሉ። መንግስት ግሽበትን ለመከላከል ጥረት በማድረግ ላይ ነው። ለግሽበቱ ምክንያት እየሆኑ ያሉትን አንዳንዶቹን የንግድ ተቋማትን እየዘጋ ነው። በመዝጋት ግን የዋጋ ግሽበቱ ይባባሳል እንጂ አይፈታም።

በፊት መንግስት ቢያስጠነቅቃቸው እና ወደ መጥፎ መንገድ እንዳይገቡ አድርጓቸው ቢሆን ህዝቡም በግሽበቱ ሳይጎዳ በቀላሉ፣ የታሸገባቸውም ሳይታሸግባቸው፣ መንግስትም ብዙ መስዋዕት ሳይከፍል በቀላሉ መፍታት ይቻል ነበር። በቀጣይ የሚመሰረት መንግስት በህዝብ ተሰሚነት ያለው ፣ ለህዝብ ቅርብ በሆነ እና አፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጥ በሚችል መልኩ መደራጀት አለበት ማለት ነው።

ጦርነት በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ከባድ ነው የሚለውን የዶክተር ተስፋዬን ሃሳብ ያጠናከሩት ዶክተር ሞላ፤ ጦርነት የኑሮ ውድነት እና ግሽበትን ይጨምራል፤ እድገትን ደግሞ ይገታል። ለልማት ስራዎች የሚውል ገንዘብ ለጦርነት ስለሚውል የኢኮኖሚውን እድገት ይጎዳል ይላሉ። ሌሎች ስራዎችን የሚሰራ የሰው አዕምሮ ነው ጦርነት ላይ ተጠምዶ ያለው። ሃሳብን ሁሉ ይበላል። በተለይ የመሪዎች በልማት ላይ ትኩረት እንዳያደርጉ ያደርጋል። ጦርነት አማራጭ ሲታጣ ብቻ የሚገባበት ነው ይላሉ።

ሀገሪቱ የገባችበት ጦርነት አደገኛ ውጤት እንዳያስከትል ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል የሚሉት ዶክተር ሞላ፤ ቢቻል በድርድር ካልተቻለ ደግሞ ሌሎች መፍትሄዎችን በመጠቀም ጦርነቱ የሚቋጭበትን መንገድ መፈለግ ያስፈልጋል ይላሉ። የተራዘመ ጦርነት የተጠራቀመ አሉታዊ ውጤት ይዞ ይመጣል። ጦርነቱ እየተራዘመ በሚሄድበት ወቅት ጦርነቱ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሊስፋፋ ይችላል። የኢኮኖሚ ችግሮች እየሰፉ ሲሄዱ ህዝቡ ወደ አመጽ ሊሄድ ይችላል። እንደዚያ ከመሆኑ በፊት በድርድር ወይም ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።

የሲቪል ሰርቪስ የምጣኔ ሀብት መምህሩ ዶክተር ተስፋዬ ጮፋና እንደሚሉት፤ አሁን ያለው መንግስትም የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ሌሎች ተጨማሪ እርምጃዎችን በመውሰድ የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመፍታት ያደረገው ጥረት ቢኖርም፤ ለረጅም ዓመታት የተከመረ ችግር በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት ጥረት ቢደረግም እንኳ የችግሩ መዘዞች ወዲያው አልተቋረጡም። ኢኮኖሚውን እየረበሸ ቀጥሏል።

በመሆኑም በኢኮኖሚው ላይ ለረጅም ዓመት የቆየው ችግር ጫና ምክንያት የለውጡ መንግስት በወሰደው እርምጃ ጭምር ችግሩን መቅረፍ አልተቻለም ብለዋል። ኢኮኖሚ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ችግሩን ለመቅረፍ ገና ብዙ መስራት ይጠበቅበታል።

አዲስ የሚመሰረተው መንግስት የችግሩን ጥልቀት በመረዳት ከኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካል ኢኮኖሚ በአስተሳሰብም በተግባርም መውጣት አለበት። ኪራይ ሰብሳቢ ኢኮኖሚ አሁንም አለ። ኢኮኖሚው ከኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ተላቋል ማለት አይቻልም። ይህን ኢኮኖሚ ማስተካከል አለበት። ሳይሰሩ እና ከሌሎች ልዩነት ሳይፈጥሩ ባለስልጣናትን መሳሪያ በማድረግ ሀብት የሚሰብስቡ አልጠፉም።

ከመንግስት ጋር አስመስለው እየሄዱ ያሉ ኪራይ ሰብሳቢዎች ዛሬም አሉ። የእነዚህ ሰዎች ዓላማ በተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ሳይሆን የመንግስት ስልጣን ጥቅም ስለሚያስገኝላቸው ነው። በፊት የነበራቸውን ኪራይ ሰብሳቢ አመለካከት ስለቀየሩ ሳይሆን ከስልጣን የሚያገኙትን ጥቅም ለማስጠበቅ ስለሚፈልጉ ስለሚያስመስሉ ነው። እንደዚህ አይነት ሰዎች ደግሞ በርካቶች ናቸው። ይህንን መንግስት በጥልቀት መገምገም አለበት። ከገመገመ በኋላም የእርምት እርምጃ መውሰድ አለበት።

በዚህም ምክንያት አሁን ያለው መንግስት ኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካል ኢኮኖሚን ሙሉ በሙሉ በማስወገድ ኢኮኖሚው በገበያ ውድድር ላይ፣ በፈጠራ ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ መገንባት አለበት። ይህንን የማስተካከል ስራ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ይላሉ። በግለሰቦች ላይ እርምጃ ከመውሰድ ባሻገር እርምጃው በተቋማት ላይ መቀጠል አለበት።

ዜጎች ከሀገሪቱ ኢኮኖሚ ፍትሃዊ የሆነ ጥቅም ማግኘትም አለባቸው የሚሉት ዶክተር ተስፋዬ፤ ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች አግባብነት ያለው ግብር በመሰብሰብ ለድሃው ጠቃሚ የሆኑ የመሰረተ ልማት ስራዎችን የመገንባት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ውድድር ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ እድገት የሚያመጣውን የኢኮኖሚ እድገት መንግስት በመሰረታዊነት ማረጋገጥ አለበት።

ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ አቅም የሌላት ኢትዮጵያ ቀርቶ በኢኮኖሚ የበለጸጉ ሀገራት ጭምር ተጨባጭ ለውጥ የማያመጡ ተቋማት ላይ ክትትል በማድረግ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳሉ። ተቋማትን ለማስተካከል ጥረት አድርገው መስተካከል፣ መታረም እና የተቀመጠለትን ደረጃ ማሟላት ካልቻለ፤ ማስመዝገብ ያለበትን ውጤት ካላስመዘገበ መንግስት ተጨባጭ መለኪያ መሳሪያዎችን አዘጋጅቶ በዚያ መለኪያ መሰረት በመገምገም መዝጋትም ሆነ ማቋረጥ አግባብነት አለው ይላሉ።

እነዚህ ተቋማት በህዝብ ግብር የሚተዳደሩ ናቸው። ህዝብ ደግሞ ለውጥ ለማያመጣ ተቋም ግብር እየከፈለ መቀጠል የለበትም። ስለዚህ ለህዝብ አስፈላጊውን አስተዋጽኦ ማበርከት አለበት። እንደዚህ አይነት ነገሮችን መንግስት ትኩረት እየሰጠ መቀጠል አለበት ብለዋል።

እንደ ዶክተር ተስፋዬ ማብራሪያ፤ ተቋማት ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻና ተወዳዳሪ የሆኑ ተቋማት መገንባት አለባቸው። ለአብነት ያህል ሀገሪቱን ኢኮኖሚ የሚመሩ ተቋማት ካላስፈላጊ የፖለቲካ ተፅዕኖ ነጻ በሆነ መንገድ ነው መንቀሳቀስ ያለባቸው። የህዝብ ተቋም እንደመሆናቸው በጥናትና ምርምር ውጤቶች ላይ ተመርኩዞ ኢኮኖሚውን መምራት የሚችል ተ ቋም መሆን አለበት።

ሆኖም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ የሚመሩ ተቋማት እስካሁን ድረስ ጠንካራ የጥናትና ምርምር ዲፓርትመንት እንኳ የላቸውም። በዓመት ውስጥ የሚያሳትማቸው የጥናትና ምርምር ውጤቶች የሉም። ስለዚህ እንደዚህ አይነት ኢኮኖሚውን የሚመሩ ተቋማት መጠናከርና የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ለመወጣት በሚያስችል መልኩ መዋቀር አለባቸው ይላሉ።

ጦርነት ኢኮኖሚውን የሚጎዳ ነው የሚሉት ዶክተር ተስፋዬ ሀብት ከኢንቨስትመንት ወደ ጦርነት የሚመደብበት ሁኔታ ይፈጠራል ብለዋል። ጦርነት እንዳይከሰት በተቻለ አቅም ጥረት ማድረግ ተገቢ ነበር። ጦርነት እንዳይከሰት ማድረግ የሚቻለው ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ሲገነቡ እና ለህዝብ ተዓማኒ የሆኑ ተቋማት ሲፈጠሩ ነው የሚሉት ዶክተር ተስፋዬ፤ ጦርነት ሲኖር ለልማት የሚውሉ የውጭ ምንዛሬዎች ከጦርነቱ ጋር ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ ግንኙነት ላላቸው ነገሮች ይውላሉ።

እንደ ዶክተር ተስፋዬ ገለጻ፤ ከዚህ ቀደም ከተደረጉ ጦርነቶች ብዙ መማር ያስፈልጋል። አሁን ፖለቲከኞች ችግሮችን በውይይት መፍታት ባለመቻላቸው እና ካለፉት ጦርነቶች ተገቢውን ትምህርት መውሰድ ባለመቻሉ ሀገሪቱ ጦርነት ውስጥ ትገኛለች። ስለዚህ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በአጭር ጊዜ የሚፈታበትን መንገድ ማፈላለግ እና በቀጣይ መሰል ጦርነት እንዳይከሰት ትምህርት መውሰድ ያስፈልጋል።

መላኩ ኤሮሴ

አዲስ ዘመን መስከረም 24/2014

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአንድ በኩል ብዙ ተስፋዎች የሚስተዋሉበት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ትላልቅ ስጋቶች ያንዣበቡበት ስለመሆኑ የዘርፉ ምሁራን ያስረዳሉ። የለውጡ መንግስት ኢኮኖሚው ከገባበት ቀውስ ለማውጣት በ2011 ይፋ ያደረገው እና በ2012 ዓ.ም ወደ ትግበራ የገባው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመሰረታዊነት ለመፍታት እንደሚያስችል ተስፋ የተጣለበት ነው።

ይህን የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ መንግስት ተጨባጭ እርምጃዎችን በመውሰድ ግብርናን በማዘመን ረገድ የሰራቸው ስራዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው። ለግብርና አስፈላጊ የሆኑ በርካታ የግብርና ግብዓቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ በማድረግ ግብርናውን የማዘመን ስራው መሰረት እንዲጥል መደረጉን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ያብራራሉ።

መታረስ ሲገባቸው ታጥረው የቆዩ መሬቶች እንዲታረሱ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ሰፋፊ ስራዎች ተሰርተዋል። የፋይናንስ ዘርፉን በማሻሻል ረገድ የተሰሩ ስራዎችም ኢኮኖሚውን ለማሻሻል ትልቅ መሰረት የሚጥሉ እና ተስፋን ያለመለሙ ነበሩ። የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ተስፋ ብቻም ሳይሆን ስጋቶችም ያንዣበቡበት ነው።

በፍጥነት እየጋለበ የሚገኘው የዋጋ ንረት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ተግዳሮቶች ስጋቶች ያንዣበቡበት መሆኑን ያመላክታሉ። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶች የተለያዩ መንስኤዎች እንዳሉት የሚናገሩት የምጣኔ ሀብት ምሁራን በቀጣይ መንግስት ኢኮኖሚውን ከተግዳሮቶች ለማላቀቅ ጠንክሮ መስራት እንዳለበት ይጠቁማሉ።

በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህር የሆኑት ዶክተር ተስፋዬ ጮፋና እንደሚናገሩት፤ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግሮች መንስኤዎች ከፖለቲካው የሚመነጭ ነው። ለረጅም ዓመታት የኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ተገንብቷል። ይህ ደግሞ በገበያ ውድድር ሳይሆን አድሎ ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ ፈጥሯል። ይህም አሁን በኢኮኖሚ ዘርፍ ለሚስተዋሉ ቀውሶች መሰረት ናቸው።

ኢኮኖሚው የኪራይ ሰብሳቢዎች ኢኮኖሚ ስለነበር አንዳንዶች ሳይሰሩ የሚበለጽጉበት፣ ሳይሰሩ ባለኩባንያ የሚሆኑበት የኢኮኖሚ አሰራር ተፈጥሮ እንደነበር የሚያስታውሱት ዶክተር ተስፋዬ ይህ ሁኔታ ተጠረቃቅሞ አሁን ያለውን የኢኮኖሚ ችግሮችን ፈጥሯል ይላሉ።

ኢኮኖሚውን ለመታደግ የአዲሱ መንግስት የቤት ስራዎችበሌላ በኩል መንግስት ለረጅም ዓመታት መልካም አስተዳደር እና ዴሞክራሲ ግንባታ ብሎ ቢያወራም እነዚህ ነገሮች ተግባራዊ አልተደረጉም። መልካም አስተዳደር እና ዴሞክራሲ መገንባት አልተቻለም። መልካም አስተዳደር እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ከተቋማት የሚመነጩ ናቸው። እነዚህ ተቋማት አልተገነቡም። ህዝብን የሚያገለግሉ፣ ህዝብ የሚተማመንባቸው ተቋማት እንዳይገነቡ ተደርገዋል። ለህዝብ ታማኝ የሆነ ጠንካራ ተቋም ከተገነባ ኪራይ ሰብሳቢ ኢኮኖሚ ለመገንባት እና ኪራይ ለመሰብሰብ ስለማይቻል ጠንካራ ተቋም እና ዴሞክራሲ እንዳይኖር ተደርጓል። ይህም ዛሬ የሚስተዋሉ የኢኮኖሚ ችግሮች እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ሲሉ ያብራራሉ።

እንደ ዶክተር ተስፋዬ ገለጻ፤ የትምህርት ሥርዓቱ ተወዳዳሪ፣ ተግባር ተኮር እና ጠንካራ የትምህርት ሥርዓት አልተገነባም የሚሉት ዶክተር ተስፋዬ፤ የትምህርት ሥርዓቱ ለፖለቲካ ፍጆታ ነበር። የትምህርት ቤቶች እና የዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ማብዛት ላይ ያተኮረ ነበር። የትምህርት ቤቶች እና የዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ማብዛት መልካም ሆኖ ሳለ በየጊዜ እያጠናከሩ መሄድ ያስፈልግ ነበር። ትምህርቱ በካድሬዎች የሚመሩ የትምህርት ተቋማት ማዕከል ሆኗል። ይህም ለትምህርት ሥርዓት ችግር መንስኤ የሆነ ሲሆን ሀገሪቱን አሁን ላለው የኢኮኖሚ ቀውስ ዳርጓል።

በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ከኢኮኖሚ ችግሮች ለመውጣት ከተለያዩ አካላት የሚበደሩትን ብድሮች በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን የሚያነሱት ዶክተር ተስፋዬ፤ ኢትዮጵያ ከተለያዩ አበዳሪ አካላት የምትወስዳቸውን ብድሮች በምን ላይ እየዋለ እንደነበር በአግባቡ ክትትል ሲደረግ አልነበረም ይላሉ። ብድሮች ለኪራይ ሰብሳቢዎች መጠቀሚያ ሲሆኑ ነበር። ከዚያ ባሻገር ብድር ከሚሰጡ አካላት ጋር በእጅአዙር የብድር ጥቅም ግንኙነቶች ነበሩ። በበለጠ ሀገሪቱ የተጠቀመችበት ሳይሆን ውስን ግለሰቦች የተጠቀሙበት የብድር ሁኔታ ስለነበር። አሁን የሚስተዋሉ የኢኮኖሚ ችግሮች ተከስተዋል ይላሉ።

በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህር የሆኑት ዶክተር ሞላ አለማየሁ በበኩላቸው፤ መንግስት ከኢኮኖሚ አንጻር መስራት ያለባቸው የሚታወቁ የመንግስት ሀላፊነቶች አሉ። የስራ እድል ፈጠራ፣

 ተስፋዬ፤ የትምህርት ሥርዓቱ ለፖለቲካ ፍጆታ ነበር። የትምህርት ቤቶች እና የዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ማብዛት ላይ ያተኮረ ነበር። የትምህርት ቤቶች እና የዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ማብዛት መልካም ሆኖ ሳለ በየጊዜ እያጠናከሩ መሄድ ያስፈልግ ነበር። ትምህርቱ በካድሬዎች የሚመሩ የትምህርት ተቋማት ማዕከል ሆኗል። ይህም ለትምህርት ሥርዓት ችግር መንስኤ የሆነ ሲሆን ሀገሪቱን አሁን ላለው የኢኮኖሚ ቀውስ ዳርጓል።

በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ከኢኮኖሚ ችግሮች ለመውጣት ከተለያዩ አካላት የሚበደሩትን ብድሮች በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን የሚያነሱት ዶክተር ተስፋዬ፤ ኢትዮጵያ ከተለያዩ አበዳሪ አካላት የምትወስዳቸውን ብድሮች በምን ላይ እየዋለ እንደነበር በአግባቡ ክትትል ሲደረግ አልነበረም ይላሉ። ብድሮች ለኪራይ ሰብሳቢዎች መጠቀሚያ ሲሆኑ ነበር። ከዚያ ባሻገር ብድር ከሚሰጡ አካላት ጋር በእጅአዙር የብድር ጥቅም ግንኙነቶች ነበሩ። በበለጠ ሀገሪቱ የተጠቀመችበት ሳይሆን ውስን ግለሰቦች የተጠቀሙበት የብድር ሁኔታ ስለነበር። አሁን የሚስተዋሉ የኢኮኖሚ ችግሮች ተከስተዋል ይላሉ።

በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህር የሆኑት ዶክተር ሞላ አለማየሁ በበኩላቸው፤ መንግስት ከኢኮኖሚ አንጻር መስራት ያለባቸው የሚታወቁ የመንግስት ሀላፊነቶች አሉ። የስራ እድል ፈጠራ፣ልማትና እድገትን ማረጋገጥ፣ የሀገሪቱን ንግድ ጤናማ ማድረግ የመንግስት ሃላፊነቶች ናቸው። መንግስት ሃላፊነቱን በአግባቡ አለመወጣት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚስተዋለው የኢኮኖሚ ቀውስ ዋነኛው ምክንያት ነው ይላሉ።

መንግስት በአንድ ኢኮኖሚ ላይ በአመዛኙ ኢኮኖሚውን የማሳለጥ ሃላፊነት በተለይም የገበያውን እና የንግድ ሥርዓቱን የማሳለጥ ሃላፊነት፤ ከዚያ አለፍ ብሎ የንግድ ሥርዓት ሲዛባ የማስተካከል ሃላፊነት የመንግስት ሃላፊነት ነው። መንግስት እነዚህን ሃላፊነቶችን በአግባቡ ባለመወጣቱ የተከማቹ ችግሮች አሁን የሚስተዋለው የኢኮኖሚ ቀውስ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል የሚሉት ዶክተር ሞላ ይህም ጤናማ የንግድ እንቅስቃሴ እንዳይኖር አድርጎታል።

በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በመፍታት ስጋቶችን ለመቀነስ እና እድሎችን ለማስፋት የተለያዩ እርምጃዎች መወሰድ እንዳለባቸው የዘርፉ ልሂቃን የተለያዩ ምክረ ሃሳቦችን ያስቀምጣሉ።

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ ማህበር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ነባራዊ ሁኔታን አስመልክቶ ባሳተመው ህትመት፤ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ አሁንም መልካም ተስፋዎች የሚታዩበት መሆኑን በመግለጽ የሚስተዋልበትን መንገራገጮች በማለፍ ውጤት ለማስመዝገብ ሊወሰዱ የሚገቡ የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎችን አመላክቷል። ሊወሰዱ የሚገቡ

 እርምጃዎችንም በሶስት ከፍሎ አስቀምጧል። ከማክሮ ኢኮኖሚ አንጻር፣ ከከተሜነት እና ከልማት አንጻር እንዲሁም ከህዝብ ቁጥር መጨመርና እንቅስቃሴ ጋር ተያያዥነት ያላቸው እርምጃዎችን አመላክቷል።

ኢኮኖሚውን ለመታደግ የአዲሱ መንግስት የቤት ስራዎችኢኮኖሚውን ለመታደግ የአዲሱ መንግስት የቤት ስራዎችኢኮኖሚውን ለመታደግ የአዲሱ መንግስት የቤት ስራዎችእንደ ማህበሩ ምክረ ሃሳብ መሰረት ከማክሮ ኢኮኖሚ ልማት አንጻር ወደ አምራች ዘርፉ መዋቅራዊ ሽግግርን ለማሳደግ የዘርፉን ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ያለመ ልዩ የድጋፍ መርሃ ግብር ያስፈልጋል። በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ለኢንተርፕራይዞች የሚደረገው የድጋፍ ሥርዓት ኢንተርፕራይዞቹ የሚያ ጋጥሟቸውን አደጋዎችና ውድድሮች ግምት ውስጥ ሳያስገባ ወጥ ነው።

Leave a Reply