ጆ ባይደን አምልጧቸው ሳይነገራቸው እንደማይናገሩ አሳበቁ

የማስታወስ ችሎታቸው ላይ በርካታ ትችትና ስላቅ የሚቀርብባቸው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን “ጋዜጠኞች” ፊት ቀርበው ማብራሪያ ሲሰጡ ለጥያቄ እድል የሚሰጡት በተራ ቁጥር ተዘጋጅቶ በሚሰጣቸው መሰረት እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል። የሚገርመው ባይደን ስም እየጠሩ ጋዜጠኞችን ለጥያቄ ሲጋብዙ ስለማያውቋቸው ወደ ቀኝ እያዩ ” አቤት” የሚለው ጋዜጠኛ ግን ከግራቸው የመሆኑ ወይም እሳቸው ወደ ግራ እያማተሩ ዝርዝር ሲያነቡ ጠያቂው ከቀኝ ” አቤት” እንደሚል በየጊዜው ፊልም የሚያሳብቀው ሃቅ ነው።

ለጥያቄ ሲቀርቡ በሚሰጣቸው ሊስት ተራ ቁጥር መሰረት ስም እየጠሩ እድል እየሰጡ የሚሉትን ካሉ በሁዋላ ሲጨርሱ ” እነሱ የነገሩኝ እነዚህን እንዳስተናግድ ነው” በማለት መናገራቸው በበርካቶች ዘንድ ትችት ቢያስነሳባቸውም፣ አንድ ጉምቱ ፖለቲከኛ ግን ” ማን ናቸው እነዚህ ሰዎች? ማን ነው መሪያችን” ሲሉ በቲውተር ገጻቸው ክፉኛ ዘለፋ ሰንዝረዋል።


ተጨማሪ ያንብቡ


ይህን ማንሳት የተፈለገው በኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ ቀደም ሲካሄዱ ከነበሩና አሜሪካ ተንደርድራ በስላቅ እውቅና ስትሰጥበት ከነበረው ምርጫዎች ሁላ የተሻለ እንደሆነ የተመሰከረለት፣ ተቃዋሚዎችና ትራዛቢዎች ሳይቀሩ የመሰከሩለትን ምርጫ ተከትሎ የተከናወነውን የመንግስት ምስረታ አስመልክቶ ባይደን ተጠይቀው ” ስለ ኢትዮጵያ ተናግሬ የአሜሪካንን ህዝብ ግራ ማጋባት / ኮንፊውዝድ ማድረግ/ አልፈልግም/ ሲሉ በመደመጣቸው ነው።

በበጀት መጨመርና አለመጨመር ጉዳይ ለፕሬስ ማብራሪያ ለመስጠት ብቅ ያሉት ባይደን፣ እግረመንገዱን ለተነሳላቸው ጥያቄ ነበር ” የመለው ነገር የለም” ሲሉ የመለሱት። መልሳቸው ሳይሆን አመላለሳቸውን ወደ ስልጣን ከመጡ በሁዋላ ካላቸው ልምድ ጋር በማዛመድ የታዘቡትን ለኢትዮ 12 የገለጹ አስተያየት ሰጪ ” ጆባይደን መመሪያ አልተሰጣቸውም” ብለዋል።

ሲያብራሩም “በበጀት ጣሪያ ላይ መግለጫ ለመስጠት ያዘጋጁዋቸው ከጀርባ ያሉ የአሜሪካ መሪዎች፣ ስለ ኢትዮጵያ ምንም ስላሉዋቸው ጆባይደን ለግዜው የአሜሪካን ህዝብ ማደናገር እንደማይፈልጉ አስታውቀው ያለፉት እነ ሱዛን ራይስ የሚሉትን ጉዳይ በደን ስላልነገሯቸው ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም”

የኢትዮጵያ ጎረቤት አገሮች ተሰምቶ በማይታወቅ ቃላትና ልዩ ክብር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን አግነው አጋርነታቸውን በገለጹበት ሁኔታ የፕሮክሲ ወይም ውክልና ጦርነት ጉዳይ መምከኑ፣ ሕዝብ ድምጹን መስጠቱንና ለማንም ተጽዕኖ እንደማይገበር፣ መንግስትን ተችግሮም ቢሆን እንደሚደግፍ በገሃድ ባስታወቀበት፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ድጋፋቸውን በገሃድ ባሳዩበት፣ አፍሪካ ህብረት አጋርነቱንና እውቅናውን ባወጀበት፣ ቁልፍ አጋሮች ድግፋቸውን አጠናክረው በቀጠሉበት፣ ፈርሶ የነበረው የባህር ሃይል ዳግም በታየበት፣ የመድና የአየር ሃይል ሞገሳቸውን ባስገመገሙበት፣ የፖሊስ ሰራዊት ዘመናዊ አደረጃጀት የታየበትን የሹመት በዓል አሜሪካም ሆነች የምትነዳቸው ተቋማትና አገራት እንዴት ብለው ሊያጣጥሉት ይችላሉ? ይህ የበርካቶች ጥያቄ ሲሆን ምላሹ አድሮ የሚታይ ይሆናል።

አስተያየት ሰጪው እንዳሉት ግን አሜሪካና አሜሪካን ተከትለው ዝምታን የመረጡ አገሮች፣ ሚዲያዎቻቸው ለጊዜው ዝም ቢሉም ኢትዮጵያ የመከላከል ጨዋታዋን ቀይራለች። ከመንግስት ምስረታው በፊት ሳይታሰብ በድንገት ሰባቱን የተባበሩት መንግስታት ሰራተኞች ከሰፊና እልህ አስጨራሽ ትዕግስት በሁዋላ በድንገት መንቀሏን ሁሉም ጠጠሮቹ እንደተገነዳደሱበት የቦውሊንግ ውድድር ይመሰላል።

የተመድም ሆነ አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ተተክሎ የነበረው የስለላ ተቋማቸው በመነቀሉ እሱን ለማስተካከል ደፋ ቀና እያሉ መሆኑንን ያስታወሱት አስተያየት ሰጪ ” አሁን አጥቂዎቹ ወደ ተከላክካይነት ተቀይረዋል። መከላከልን ደግሞ ስላላሰቡበት ለጊዜው አልቻሉትም” ሲሉ ነገሮች በቅርብ መላካቸውን እንደሚቀይሩ ጠቁመዋል። አያይዘውም ዲፕሎማሲው አልነበረከከም ባይነትን በጥበብ በማስኬድ ደረጃ እድገት እንደሚያሻውም አመልክተዋል።

Leave a Reply