በቀጣይ አገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት የምሰማራ ይሆናል፡፡ ለነበረኝ ትልቅ ሃላፊነትና ለተደረገልኝ ትብብር አመሰግናለሁ:: አገራችን ኢትዮጵያን ፈጣሪ ይጠብቃት፡፡ኢትዮጵያችን እንደ ገናና ታሪኳ ሁሉ ጸንታ ትኖራለች፡፡
ኢንጂነር ስለሺ በቀለ
ዛሬ ይፋ የሆነውን የካቢኔ ሚኒስትሮች ሹመት ተከትሎ የዶክተር አብርሃም በላይ የመከላከያ ሚኒስትር መሆንና የወሃ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በካቤኔ ሚኒስትር ዝርዝር ውስጥ አለመካተታቸው መነጋገሪያ ሆነ።
ለረዥም ዓመታት ለኦሮሞ ተወካዮች ሲሰጥ የነበረው ማዕረግ፣ የማሙያ ማዕረግ ከመሆን የዘለለ አቅም የሌለው የመከላከያ ሚኒስቴር ሹመት ለዶክተር አብርሃም መሰጠቱን ከቀድሞው የወ/ሮ ኪርያ የፌደሬሽን ምክር ቤት ወንበር ላይ አቶ አገኘሁ ተሻገር እንዲቅመጡበት መደረጉ ጋር አገናኝተውታል።
የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ህገመንግስት ትርጉም የሚሰጥበት፣ የድንበር ጉዳዮችና የማንነት አጀንዳዎች ፍርድ የሚያገኙበት ትልቁ የስልታን አካል በመሆኑ ለማንም ወገን አሳልፎ ሰጥቶ አያውቅም።
በዚህም የተነሳ የውልቃይትና ጠገዴ፣ እዲሁም የራያ ጉዳይ ሊታፈን እንደቻለ የጠቆሙ እንዳሉት አቶ አገኘሁ ይህን ቦታ መያዛቸው በበርካታ የትህነግ ደጋፊዎች ዘንድ ንዴት ፈጥሯ፤ ቀደም ሲል ልክ ወ/ሮ ኬሪያ ላይ ሌሎች ሲያሰሙት የነበረውን ዓይነት ቅሬታ ነው የሚደመጠው።
የ360 የቀን ተቀን ተንታኝ ኤርሚያስ ሹመቱ ዶክተር አብይ የወልቃይት ጉዳይን በአቶ አገኘሁ በኩል ወደ ትግራይ ለማስመለስ የያዙት ዕቅድ አድርጎ ወደ ሴራ ትንታኔ ቢቀይረውም፣ አቶ አገኘሁ ለዚህ ስጋት፣ ዛሬ ለከፍተኛ ደም መፋሰስ ምክንያት የሆነውና ይህን ተከትሎ ለሚነሳ ሃሜት፣ የቀደምው ዓይነት ፍትህ የሚያዛባ አካሄድ እንዳይደገም የብረት መዝጊያ እንዲሆኑ ድርጅታቸው ወገቡን ይዞ ተሟግቶ እንዳሾማቸው ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።
ዛሬ በተሰማው አዲስ የካቢኔ ሹመት የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ሆነው ተሹመው የነበሩት ዶክተር አብርሃም ወደ መከላከያ ሚኒስትርነት
መዛወራቸው፣ ልክ ቀደም ሲል ይደረግ እንደነበረው “ለቁጥር ማሙያ ነው” እንደሆነ አድርገው እየገለጹ ያሉ አሉ።
ለትህነግ የህዝብ ግንኙነት ሆኖ ከማገልገል በላይ በተለያዩ ቋንቋዎች የተሰራጩና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የሚያወግዙ የሚመስላቸውን መረጃዎች የሚያሰራጩት የኖርዌይ ተወላጁ ሼትል ትራድቮል በቲውተር ገጻቸው የዶክተር አብርሃምን በመከላከያ ሚኒስትርነት መሾም “የጦርነት ስትራቴጂ ” ከሆነ እናየዋለን ሲሉ ከምኑም ጋር ያልተገናኘ ሃሳብ አሻምተዋል።
ቀደም ሲል ትህነግ ባዘጋጀውና አሁን ድረስ በሚሰራበት አግባብ የመከላከያ አደረጃጀት ለሲቪል የመከላከያ ሚኒስትር ተሿሚ ይሄ ነው የሚባል ሃላፊነት የማይሰጥ መሆኑ እየታወቀ ሰውየው የጦርነት ለውጥ ስትራቴጂ አድርገው መውሰዳቸው አስገራሚ ሆኗል። ወይም መረጃውን የሰጡዋቸው መሳቂያ እንዳደረጓቸው ተመልክቷል።
የኢንጂነር ስለሺ አለመሾም ጋር በተያያዘ ግምገማ ከተደረገ በሁውላ ውሳኔው እንደተወሰነየሚገልጹ ያሉተን ያህል ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እጅግ ለላቀ አገራዊ ሀላፊነት መታጨታቸውን የሚገልጹ ኣሉ
ራሳቸው በፌስ ቡክ ገጻቸው ይህን ኣስፈረዋል
ውድ የተከበሩ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚ/ር እና
ውድ የተክበሩ ዶ/ር ኢ/ር ሃብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚ/ር እንኳን ደስ አላችሁ!!
እስክ ዛሬ ድረስ ላለፉት 5 አመታት ስመራው የነበረውን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚ/ር፤ ዛሬ በጸደቀው የአስፈጻሚ መ/ቤቶች አደረጃጀት መሰረት በመሾማችሁ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ ሁለቱም ዘርፎች ለአገራችን ማደግ ና መለውጥ ወሳኝ ተቋማት ናቸው፡፡ በውጤታማነት እንደምትመሩ ባለሙሉ እምነት ነኝ፡፡ የበኩሌ ድጋፍም ሁሌም አይለያችሁም፡፡
ውድ ኢትዮጵያዊያን የአገሬ ህዝቦች፡ እናት አገራችን ኢትዮያን እና ህዝቦቿን፤ ላለፉት አምሰት አመታት ሚኒስትር በመሆን በቅንነት፤ በታማኝነትና በምችለው ሁሉ አገልግያለሁ፡፡
ይህ ሃላፊነት ተሰጥቶኘ በዚህ ከፍተኛ የአገራችንና ህዝቧ አገለግሎት ውስጥ ብዙ መልካምና ወጤታማ ሰራዎችን የሚኒስቴር መ/ቤቱንና ተጠሪ ተቋማትን ሰራተኞች እንዲሁም ብቃት ያላችውን ምሁራንንና ኤክሰፐርቶችን በማሰባሰብ ሰርተናል፡፡ ብዙ አስቸጋሪ ጊዜያትንም አሳልፈናል፡፡ ግድባችንም በጥቂት ወራት ሀይል ያመነጫል፡፡ በዚህና በሌሎችም መስኮች ያደረግሁት አስተዋጽኦ በፈታኞቹ ወቅቶችና ሰአታት አገሬን ቀና አድርጓታል ብዬ አምናለሁ፡፡
በቀጣይ አገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት የምሰማራ ይሆናል፡፡ ለነበረኝ ትልቅ ሃላፊነትና ለተደረገልኝ ትብብር አመሰግናለሁ:: አገራችን ኢትዮጵያን ፈጣሪ ይጠብቃት፡፡ኢትዮጵያችን እንደ ገናና ታሪኳ ሁሉ ጸንታ ትኖራለች፡፡
አዲስምዕራፍ

ባዲሱ ሹመት መረሰረት
- 1. አቶ ደመቀ መኮንን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
- 2. ዶክተር አብርሃም በላይ መከላከያ ሚኒስትር
- 3. አቶ አህመድ ሽዴ የገንዘብ ሚኒስትር
- 4. ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
- 5. አቶ ኡመር ሁሴን የግብርና ሚኒስትር
- 6. ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር
- 7. ዶክተር ኢንጀነር ሃብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር
- 8. ዶክተር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር
- 9. ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ- የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስትር
- 10. አቶ ገብረ መስቀል ጫላ የንግድና እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
- 11. አቶ መላኩ አለበል የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
- 12. አቶ ብናልፍ አንዱዓለም የሰላም ሚኒስትር
- 13. ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የፍትሕ ሚኒስትር
- 14. ዶክተር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስትር
- 15. አቶ በለጠ ሞላ- የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
- 16. አምባሳደር ናኒሴ ጫሊ- የቱሪዝም ሚኒስትር
- 17. አቶ ላቀ አያሌው- የገቢዎች ሚኒስትር
- 18. ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ-የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር
- 19. ኢንጂነር ታከለ ኡማ- የማዕድን ሚኒስትር
- 20. ዶክተር ፍፁም አሰፋ- የፕላንና ልማት ሚኒስትር
- 21. ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ-የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
- 22. አቶ ቀጀላ መርዳሳ -የባህልና ስፖርት ሚኒስትር በመሆን ሹመታቸው ጸድቆ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡