የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትርአቶ ቀጀላ መርዳሳ የሥራ ርክክብ አደረጉ

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት አቶ ቀጀላ መርዳሳ ከቀድሞው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ጋር የሥራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

ለአዲሱ ሚኒስትርም የቀድሞዋ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር የነበሩት ዶ.ር ኂሩት ካሳው እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በርክክቡ ወቅትም ለሚኒስትሩ ስለ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አደረጃጀትና እየተሠሩ ስላሉ ሥራዎች እንዲሁም ለወደፊት የታቀዱ እቅዶች በዶ.ር ኂሩት ካሳው ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል፡፡

አቶ ቀጀላ መርዳሳ ፥ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው በመመደባቸው የተሰማቸውን ደስታ የገለፁ ሲሆን የኢትዮጵያን ገፅታ ሊቀይር የሚችል ሥራን ለመሥራት የተጣለባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት ካለው አመራርና ሠራተኛ ጋር በመወያየት እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ፥ የሚኒስቴሩ አመራሮች ላደረጉላቸው አቀባበል አመስግነዋል፡፡

ምንጭ፦ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር

Leave a Reply