አና ጎሜዝ “አሸባሪው የህወሃት ቡድን የአደገኛ ወንጀለኞች፤የጨቋኞችና የውሸታሞች ስብስብ መሆኑን አውቃለሁ”

አሸባሪው የህወሃት ቡድን የአደገኛ ወንጀለኞች፤ጨቋኞች እና ውሸታሞች ስብስብ መሆኑን አውቃለሁ -አና ጎሜዝ

በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንደነበረው ሰው አሸባሪው የህወሃት ቡድን የአደገኛ ወንጀለኞች፤ጨቋኞች እና ውሸታሞች ስብስብ መሆኑን አውቃለሁ ሲሉ የቀድሞ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባል አና ጎሜዝ ገለጹ።

አና ጎሜዝ በ1997 ዓ.ም ኢትዮጵያ ያካሄደችውን አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫ ለመታዘብ የመጣው የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ነበሩ።

በወቅቱ አፋኝ በነበረው በህወሃት የበላይነት የሚመራው መንግስት ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፤ፍትሃዊ እና ተዓማኒ እንዳይሆን በማድረጉ አና ጎሜዝ ሲያብጠለጥሉት ቆይተዋል።

Advertisements

አና ጎሜዝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚያደርገውን ተደጋጋሚ ጫና በመቃወም ለድርጅቱ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና ለግብረሰናይ ድርጅት አመራሮች በትዊተር መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚሁ መልዕክታቸው በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ እና ልምድ እንደነበረው ሰው የአሸባሪው ህወሃት ቡድን የአደገኛ ወንጀለኞች፤ጨቋኞች እና ውሸታሞች ስብስብ ነው ብለዋል።

የጸጥታው ምክር ቤት እና የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ላይ የሚነዙት ያልተገባ ወቀሳ ነባራዊ ሁኔታን ያላገናዘበ ነው በሚል በርካቶች እየተቃወሙት ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ ከተልዕኳቸው ውጪ ሲንቀሳቀሱ ከአገር እንዲወጡ የተደረጉ የተመድ ሰራተኞች ለአሸባሪው ቡድን የተለያየ ድጋፍ ሲያቀርቡ የነበሩ መሆናቸው ተጠቅሷል።

የአሁኑ ተመድ ኢትዮጵያ ፋሽስቱ የኢጣሊያ መንግስት ጸብ አጫሪነቱን እንዲያቆም እና የሀገሯን ሉዓላዊነት እንዲያከብር ለ’ሊግ ኦፍ ኔሽንስ’ እአአ 1935 ያቀረበችውን አቤቱታ ወደጎን በማለት ለኢጣሊያ ይሁንታ መስጠቱ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ አለም አቀፍ ህጎችን መነሻ በማድረግ ለአሸባሪው ቡድን ድጋፍ ያደረጉ የተመድ ተወካዮች ላይ እርምጃ ብትወስድም ፤የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እውነታውን ባለመቀበል ኢትዮጵያ ላይ ፊቱን ማዞሩ ”ታሪክ እራሱን ደገመ ”የሚያስብል አቋም እንዲይዝ አድርጎታል።

(ኢዜአ)

Leave a Reply