ትህነግ – በሰሜን ወሎና በጎንደር የህዝቡን የኢኮኖሚ መሰረቶች በሙሉ ማውደሙና መዝረፉ ይፋ ሆነ

አሸባሪው ህወሃት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎና በጎንደር የህዝቡን የኢኮኖሚ መሰረቶች አውድሟል

አሸባሪው ህወሃት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎና በጎንደር የህዝቡን የኢኮኖሚ መሰረቶች ማውደሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ህዝቡን ለመከራና ስቃይ በመዳረግ ዳግም ወደ ፖለቲካ ስልጣን ለመምጣት አደገኛ ሙከራ ውስጥ የተዘፈቀው ላለፉት 27 አመታት ስልጣን ላይ የነበረው አሸባሪው ቡድን፤ አብዛኛው የትግራይ ክልል ህዝብን ከሴፍቲኔት ተረጅነት እንኳን ሊያላቅቅ አልቻለም፣ ቡድኑ ለክልሉ ህዝብም ደህንነት ያለውን ግዴለሽነት በተደጋጋሚ አሳይቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አሸባሪ ቡድኑ በወረራቸው የሰሜን ወሎና ጎንደር አካባቢዎች ያደረሰው መጠነ ሰፊ ውድመት የአማራ ህዝብ ጠላትነቱን ዳግም ያስመሰከረበት መሆኑን ገልጿል።

በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች የሚወጡ ሪፖርቶች እንዳመለከቱት የብዙ ቤተሰቦች የኢኮኖሚ አቅሞችን አውድሟል፤ በወረራቸው አካባቢዎች ያሉ አርሶ አደሮች የአሸባሪው ታጣቂዎች የደረሱ ሰብሎችን እየዘረፉ ማመልከታቸውን ጠቅሷል።

“አርሶአደሩ ያከማቸው እህል ተዘርፏል የቀረውም እንዲወድም ሆኗል፤ የእርዳታ እህል ማከማቻ መጋዘኖች የአሸባሪው ቡድን የዘርፋ ሰለባ ከመሆናቸው ባሻገር ከተረጂዎችም ይቀማል” ብሏል መግለጫው፡፡

ቡድኑ ያስከተለው መጠነ ሰፊ ውድመት በግለሰብ ላይ ብቻ ሳይሆን እንደማህበረሰብ የህዝብ መገልገያዎችን የህፃናት መዋያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች፣ ባንኮች፣ የጤና ማዕከላት፣ ሆቴሎችና ሎሎችም ተቋማት ወድመዋል፡፡


ተጨማሪ ያንብቡ

በግንባታ ሂደት ላይ ያለው የአዋሽ ወልዲያ ሃራ ገበያ የባቡር መንገድ ፕሮጀክት ሃላፊነት በማይሰማው አሸባሪ ቡድን የጥቃት ሰለባ ሆኗል ፡፡

“ሽብር ቡድኑ የሚያስከትላቸው መጠነ ሰፊ ውድመቶች ለትግራይ ህዝብ የሚፈይድለት ነገር እንደሌለ ይታወቃል፤ ይልቁንም የትግራይና የአማራን ህዝብ ወደ ባሰ ስቃይና እንግልት ያስገባል” ሲል ሚኒስቴሩ አመልክቷል፡፡

የሽብር ቡድኑ በሰሜን ወሎ እንዲሁም በጎንደር የፈፀመውና እየፈፀመ ያለው ውድመት በፖለቲካው አለሁ ለማለት የሚደረግ የመጨረሻው መፍጨርጨር እንደሆነም ነው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በችግር ውስጥያሉና እገዛ የሚሹ በሰሜን ወሎና ጎንደር ያሉ ህዝቦችን ትኩረት እንዲሰጣቸው የጠየቀው መግለጫው፤ ወራሪው በያዛቸው አካባቢዎች ያሉ ዜጎች የተፋጠነ የሰብአዊ እርዳታ እንዲደርሳቸው ጥሪ አቅርቧል።

Ena

Leave a Reply