በሩሲያና ቻይና በጦር ቴክኖሎጂ የተዘረረቺው አሜሪካ !

“ቻይናና ሩሲያ አሜሪካን ለማጥፋት ደቂቃዎች ብቻ ያስፈልጓቸዋል?!!”

በሩሲያና ቻይና በጦር ቴክኖሎጂ የተዘረረቺው አሜሪካ !

ታላላቅ የአለማችን መገናኛ ብዙሃን ስለ ሩሲያና ቻይና የጦር አቅም ይዘውት እየወጡ ያሉት መረጃ አነጋጋሪ ሆኗል ። ከሁሉ በላይ ትኩረቴን የሳበው የአሜሪካው ተነባቢ ጋዜጣ THE NATIONAL INTEREST ይዞት የወጣው አስገራሚ መረጃ ነው ። የናሽናል ኢንተረስቱ ተንታኝ David T.Pyne ሩሲያና ቻይና አሜሪካን ለማውደም የሚፈጅባቸው ጊዜ ደቂቃዎች ብቻ ነው ሲል ይደመድማል ። እንዴት ? የሚለው ጥያቄ እዚህ ጋር መነሳቱ አይቀርም ።

አብረን እንየው !

ሩሲያና ቻይና አሜሪካን በብዙ ርቀት አልፈው ከሄዱባቸው የጦር ቴክኖሎጂዎች ቀዳሚው የኑክሌርና ሚሳኤል ቴክኖሎጂያቸው ነው ። የነዚህ ሁለት ሀገራት የሚሳኤል ቴክኖሎጂ አሜሪካ በቅርብ ላትደርስበት ሆኖ የተሰቀለ የትኛውንም የአለም ክፍል በደቂቃዎች ውስጥ ወደ ፍርስራሽነት የሚቀይር ነው ። ሩሲያ የተራቀቀውን Supersonic Electromagnetic ሚሳኤልን የታጠቀቺው ከዛሬ 20 አመት በፊት ነበር ። ይህንን ከእርሷ በቀር ሌላ አለም የልለውን ቴክኖሎጂ ለወዳጆቿ ቻይና እና ሰሜን ኮሪያ እንካችሁ አለቻቸው ። የልብ ወዳጅነት ለመቼ ነውና !?

እነዚህ ሀገራት በ Supersonic Electromagnetic ሚሳኤል ሳይረኩ ዛሬ ከድምፅ በብዙ እጥፍ የሚልቀው የ Hypersonic ሚሳኤሎች ባለቤት ሆነዋል ።

አሜሪካ ከአስርት አመታት በፊት ያሏት የኑክሌር መሳሪያዎች ብዛት 30,000 ነበር ። ነገር ግን ዋነኛ ተቀናቃኟ ሶቭየት ህብረት በመፈራረሷና እርሷን ሊገዳደር የሚችል ሀገር የለም ብላ በማሰቧ ከአላስፈላጊ ከፍተኛ ወጪ ለመታደግ ሲባል አሁን አሜሪካ ያሏት የኑክሌር መሳሪያዎች ብዛት 1,750 ብቻ ነው ይላል የ National Interest ሀተታ ። ከነዚህ የአሜሪካ ኑክሌር መሳሪያዎች በአሁኑ ሰአት በማንኛውም ሰአት ለመወንጨፍ ዝግጁ የሆኑት 750 ብቻ ናቸው ።

የሩሲያን የኑክሌር መሳሪያ ያየን እንደሆነ በአሁኑ ሰአት ሩሲያ 8,000 የሚሆን ለጦርነት ዝግጁ የሆነ የኑክሌር መሳሪያ አላት ። ያ ማለት ከአሜሪካ በ 4.5 እጥፍ ይበልጣል ። ሩሲያ 6 Superweapon nuclear ሲስተም ያሏት ሲሆን አሜሪካ አንድም የላትም ። እነዚህ ስድስት የኑክሌር መሳሪያዎች አቻ የሌላቸው አውዳሚ መሳሪያዎች ናቸው ። ሩሲያ ከድምፅ ከ 10 እጥፍ በላይ የሚፈጥኑ አስር ሺህ ኪሎሜትሮችን በደቂቃዎች አቆራርጠው የሚሄዱ ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤሎች ባለቤት ስትሆን እነዚህ ሚሳኤሎችን መከላከል የሚያስችል ፀረሚሳኤል እስካሁን አሜሪካ መገንባት አልቻለችም ። የአሜሪካ ፀረሚሳኤሎች አንድን ሚሳኤል መክቶ ለማክሸፍ 9 ሰከንድ አካባቢ የሚፈጅባቸው ሲሆን የሩሲያው ሚሳኤል ግን በ 8 ሰከንድ ውስጥ የአሜሪካን ፀረሚሳኤሎች 20 ማይል ትቷቸው ይጓዛል ። ስለዚህ የአሜሪካ ፀረሚሳኤል ከሩሲያ ሚሳኤል አንፃር ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ መሆኑ ነው ።

ቻይናን በተመለከተ !

ቻይና በአሁኑ ሰአት አሜሪካ ከምትገምተው የኑክሌያር ብዛት በ 20 እጥፍ የሚልቅ የኑክሌር መሳሪያዎች ባለቤት መሆኗ ተረጋግጧል ። ይህም ማለት የቻይና የኑክሌር አረር ከአሜሪካ በ ሁለት እጥፍ ይበልጣል ። በቅርብ አመታት ውስጥ የቻይና የኑክሌር መሳሪያ ብዛት ከአሜሪካ በ 4 እጥፍ እንደሚበልጥ ይጠበቃል ። ቻይና ሩሲያ ሲጣመሩ ደግሞ የአሜሪካና የነቻይና ንጥጥር አንድ ለአስር ይሆናል ማለት ነው ። ያ ማለት አነርሱ የአሜሪካ 1000% ይሆናሉ ማለት ነው ።

ከሁሉ በላይ ግን ቻይና የታጠቀቺው DF-41 የተሰኘው ሚሳኤል ለአሜሪካ እጅግ አስደንጋጩ መርዶ ነው ። DF-41 በአለማችን ላይ ረጂም ርቀትን በመጓዝ የሚስተካከለው የለም ። 15,000 ኪሎሜትር ይጓዛል ። ያ ማለት በአለም ላይ በየትኛውም ቦታ ሚሳኤሉ የታጠቀውን ኑክሌር መዘርገፍ ይችላል ። ይህ ሚሳኤል በሰአት 30,626 ኪሎሜትር ይጓዛል ። ያ ማለት አሜሪካን ለማውደም የማፈጅበት ጊዜ የተወሰኑ ደቂቃዎች ናቸው ማለት ነው ። ሚሳኤሉ የሚሸከመው የኑክሌር መሳሪያም 150,000 ቶን ይመዝናል በዚህ ተወዳዳሪ የለውም ።

በባህር ሃይል ያየን እንደሆነ ቻይና 350 የተራቀቁ የጦር መርከቦች ሲኖሯት የአሜሪካ ጦር መርከቦች 295 ናቸው ።

የአሜሪካ ስትራቴጂክ ኮማንድ አዛዥ አድሚራል Carles Richard ይጠይቃል ” እኛ ያሉንን 400 የኑክሌር አረሮችን ለማዘመን ከ 10 እስከ 15 አመት ይፈጅብናል ቻይናዎች ግን ይህንን ለማድረግ ጥቂት ቀናት ብቻ ይበቋቸዋል ። ይህ እኛን ትልቅ አደጋ ውስጥ የሚከተን ነው ። ለመሆኑ እነዚህ ቻይናዎች እጅግ ግዙፍ ግዙፍ የሆኑ የኑክሌር መሳሪያዎችን ከየትኛውም አለም በፈጠነ መልኩ የሚገነቡበት ሚስጥሩ ምንድን ነው ?” በማለት ይጠይቃል ።

ተፃፈ በሰኢድ መሀመድ አልሀበሺ

Leave a Reply