ትህነግ ሚሊዮን ሕዝብ ጨርሸም ቢሆን አማራን አንገቱን አስደፋዋለሁ ብሎ አቅዶ ነው ጦርነት የከፈተው። በርካታ ወጣት እየረገፈ፣ አሁንም ሌላ ይዞ ይመጣል። አማራን አንገቱን ማስደፋት ከቻለ በጣት የሚቆጠሩ የራሱ አመራሮች ብቻ ቢቀሩም አይጨንቀውም። አማራን አጥፍቶት ቢጠፋም እንደ ክስረት አያየውም። እየመጣ ያለው ጠላት ይሄ ነው!!

ከፋብሪካ እስከ ሊጥ፣ ከዩኒቨርሲቲ እስከ ዶሮ የሚዘርፈው ባዳበረው ቅጥ ያጣ ጥላቻና ደመኝነት ነው። የስምንት አመት ህፃን፣ የቄስ ሚስት የሚደፍረው ካቀደው የመጨረሻ የጠላትነት ደረጃ ነው። እንሰሳ ሰው ሳይለይ በጥይት የሚጨፈጭፈው ማጥፋትን እቅዱ አድርጎ ስለመጣ ነው!

በርካቶች የተጨፈጨፉት ማጥፋትን አላማው አድርጎ በመጣው ጠላት ነው።
ከአራት ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ችግር ውስጥ የወደቀው በዚህ ደመኛ ጠላት ነው። በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ የተፈናቀለው በዚህ ክፉ ጠላት ነው። በርካታ መሰረተ ልማቶች የወደሙት በደመኛው ጠላት ነው!

ግን አይተነዋል!

ከአመት በፊት ዳንሻ ላይ መውጫ ሲያጣ ቀሚስ ለብሷል! ቀሚስ አስለብሰነዋል!

ዘንድሮ አፋር ላይ አፈር ግጧል!

ወደ ዳባት እዘልቃለሁ ብሎ የሞተ መስሎ አፈር ለብሶ ተኝቶ በፋኖዎች ተይዟል። ሲሸነፍ በሞትኩ፣ ምድር በዋጠችኝ ብሎ ሳይችል እጁን ሰጥቷል!

በጋይንት ቅስሙን ተሰብሮ ተመልሷል!

በቋራ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ተመልሷል!

ወልቃይት ጠገዴ ላይ 12 ጊዜ ሞክሮ ተመትቷል!

ባለፈው ደሴና ኮምቦልቻን እዘርፋለሁ፣ አወድማለሁ ብሎ መጥቶ ተመትቶ ተመልሷል።

በጋሸና እና በማይጠምሪ ግንባር እየተቀጠቀጠ ነው!

እንደሚሸነፍ ብቻ ሳይሆን አሸንፈን አይተነዋል። እናሸንፈዋለን!

ከእኛ የሚጠበቀው አሁንም አሸባሪው አሁንም እንደወረረን መሆኑን ማመን ነው። በርካታ ሕዝባችን በመከራ ውስጥ ሆኖ፣ በጠላት ተይዞ አርፈን መቀመጥ እንደማንችል ማመን አለብን። ሲነጋ ሲመሽ በደመኛ ጠላት መወረራችን ማስታወስ አለብን!

ከእኛ የሚጠበቀው የጦርነት ወቅት መሆኑን በሚገባ ተገንዝቦ ትኩረት መሰብሰብ ነው!

ከእኛ የሚጠበቀው የከፋ አደጋ ከሚደርስ ራሳችንን መስዋዕትነት አድርገንም የእናቶችን ሰቆቃ፣ የህፃናትን መከራ፣ የከተሞቻችን መውደም፣ ሕዝብ ውርደት እንዳይደርስበት ለመታደግ መቁረጥ ነው!

ከእኛ የሚጠበቀው ቀዬን ለቅቆ ከመሄድ በቻልነው መፋለም ነው!

ከእኛ የሚጠበቀው እንደነሱ መቁረጥ ነው! እነሱ እርጉዝም ይዘው እየመጡ መሆኑን አምነን ከተፈናቃይነት ወጥተን ጦር ሜዳው ላይ መገኘት ነው። እንደ ሕዝብ የተከፈተውን ጦርነት እንደ ሕዝብ መመከት ነው!

አሸንፈን አሳይተነዋል። እናሸንፈዋለን! ከማሸነፍ ውጭ ምንም አማራጭ የለም! ትህነግ አሸንፎ በሕልውና መኖር አይቻልም!

Via -Getachew Sheferaw

Leave a Reply