ደቡብ ወሎ ክተት ተጠራ

በአፋር ጭፍር በኩል የተደረገውን ሙከራ የአፋር ሃይል እንደመከተ ቢነገርም በውጫሌ በኩል ግን ያን ማድርገ እንዳልተቻለ፣ ውጊያው በከፍተኛ ሁኔታ መቀጠሉን መረጃዎች ያመለክታሉ። ትህነግ ግዛቱን እያሰፋ እንደሆነም እየተጠቀሰ ነው። ዝርዝር ቦታዎችን መናገር አስቸጋሪ ቢሆንም በጭግርና ረሃብ ሕዝብ ሲሰቃይበት የከረመበት የደሴ ግንባር ለነዋሪዎች የከፋ ሆኗል።

ሕዝብ ትህነግን ስለማይፍለግና በትህነግ በድጋሚ ሊገዛ የሚችልበት አግባብ አለመኖሩ ይህይንኑ ተከትሎ የእርስ በእርስ መጫረስ በየአቅጣጫው እንዳይጀመር ስጋት የገባቸው ድምጻቸውን እያሰሙ ነው።

ደቡብ ወሎ ዞን ጥሪ አቅርቧል።

ከደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ለመላው የወሎ ህዝብ የቀረበ የክተት ጥሪ!


አሸባሪው፣ ጨፍጫፊው፣ ዘራፊውና ወራሪው የትግራይ ኃይል በውጫሌ፣ በተሁለደሬ፣ በወረባቦና ደላንታ ግንባሮች ጦርነት በመክፈት የተለመደውን በህዝባችን ላይ የክፋት በትሩን ለማሳረፍ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ነው።
ይህ የክፋት ኃይል ግልጽ ወረራ በፈጸመባቸው በሰሜን ወሎ፣ ዋግ ኽምራ፣ በከፊል ደቡብና ሰሜን ጎንደር አካባቢዎች ቁጥሩ በውል የማይታወቅ የአማራ ህዝብ በጅምላ ተጨፍጭጭፏል። በቅርቡ በተሁለደሬና ወረባቦ ወረዳዎች ሰርጎ በመግባትም የፈጸመው ኢ- ሰብዓዊ ድርጊት አሰቃቂ እንደነበር ይታወሳል።
ህዝባችን ለዘመናት ለፍቶ፣ ጥሮና ግሮ ያፈራው ሐብትና ንብረቱን በአሸባሪውና ወራሪው ኃይል ተዘርፏል፣ ወድሟል። የመንግሥትና የግል አገልግሎት መስጫ ተቋማትም በዚሁ ኃይል ተዘርፈዋል። ጻናትን ጨምሮ እናቶችና ሴት እህቶቻችን በአሸባሪ ቡድኑ በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍረዋል።
አሁንም የሚፈጽመው ወረራ፣ ዝርፊያና ጭካኔ የተሞላበት ጅምላ ጭፍጨፋውን የቀጠለ ሲሆን በውጫሌ፣ በተሁለደሬ፣ በወረባቦና ደላንታ ግንባሮች
ሰርጎ ለመግባት ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከአማራ ልዩ ኃይል፣ የሚሊሻ ኃይላችን እና ፋኖ ጋር ውጊያ ገጥሟል።
አሸባሪው ትህነግና ግብረ አበሮቹ ከኢትዮጵያ ምድር እስከወዲያኛው እስካልተነቀሉ ድረስ የአማራ ህዝብም ሆነ የኢትዮጵያ ህልውና በጽኑ መሰረት ላይ አይቆምም።
የአማራ ህዝብ ህልውናም ሆነ የኢትዮጵያ ትንሳኤ የሚረጋገጠው በትህነግ መቃብር ላይ መሆኑን ለአፍታም ቢሆን ባለመዘንጋት እየተደረገ ያለውን የህልውና ትግል መሳሪያ ያለው በመሳሪያው፣ ጉልበት ያለው በጉልበቱ፣ ሐብት ያለው በሐብቱ፣ ሃሳብ ያለው በሃሳቡ ከአገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከአማራ ልዩ ኃይል፣ ከሚሊሻና ፋኖ ጎን በመሰለፍ የአሸባሪውን ቡድን ግብዓተ መሬት ማረጋገጥ ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለምና ሁሉም አቅሙ የፈቀደውን ድጋፍ እንዲያደርግ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የክተት ጥሪውን ያቀርባል።
የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር

Leave a Reply