“ሁሉም ወደ ወሎ ይዝመት፣ ይዝመት …” ጦርነቱ የሰው ጎርፍ ማሰማራት ነውና

” ሌባው ሊሰርቅ፣ ሊገልና ሊያርድ እንጄ ህይወት ሊሰጥ አይመጣን” የሚለው የመጥሃፉ አባባል ዛሬ እየሰራ ነው። ትህነግ እግሩ በረገጠበት ሁሉ ሰላማዊ ዜጎችን በተለይም አማራን ለማጥፋት እሳት እየረጨ፣ በጅምላና በተናጠል እየገደለ፣ ሃብት እየዘረፈ፣ ተቋም እያወደመ፣ አገልግሎት እያስተጓጎለ፣ የሰዎችን በቀዬያቸው በሰላም የመኖር መብትና ተፈጥሯዊ ሂደት እያስተጓጎለ ይገኛል። ይህን ሁሉ የሚያደርገው “ከአማራ ጋር የማወራርደው ሂሳብ አለኝ፤ እንደ አባቶቻቸው እንጨርሳቸዋለን” በሚል በግልጽ ባስቀመጠው አጀንዳው አማካይነት ነው።

በዚሁ ዓላማና ግቡ መሰረት ትህነግ ሰሜን ጎንደርን፣ ደቡብ ጎንደረን ወሮ ነበር። ወሮ ደጃቸው ድረስ ሄዶ የፈጸመውን ምስኪን አርሶ አደሮችና አቅመ ደካሞች በግልጽ አስታውቀዋል። ደብረታቦርን ቆርጦ ወደ ባህር ዳር ለማቅናት ጫፍ በደረሰበት ቅጽበት ክተት ተጠርቶ ሕዝብ ይርመሰመስ የነበረውን ሃይል አስወግዶ ህልሙን አምክኖበታል። በወልቃይት ግንባር የተሰራውን ግንብ መቋቋም ባለመቻሉ በአፋር በኩል የጅቡቲን መንገድ ለመቁረጥ በአደባባይ ለዓለም ሚዲያዎች አስታውቆ ቢዘመትም ሳይሳካለት ቆይቷል።

የተውሰደበትን እርምጃ ባለመቋቋሙ አገግሞ በደሴ ግንባር ኮምቦልቻና ደሴን ለመያዝና እንደለመደው በዝርፊያ ሊያጥብ የትግራይ ወጣቶችን አስለፎ እሳት እየረጨ ነው። ይህ ከፍተኛ የሆነ የሰው ሃይል አስለፎ እየተርመሰመሰ ወረራ የሚፈጽመው ቡድን አማራውን እርስትና ስንቅ አልባ አድርጎ በሴፍቲ ኔት እየተረዳ የሚኖር የደቀቀ ማህበረሰብ ሊያደርገው ነው ሃሳቡ።

ኮምቦላቻንና ደሴን እንደማያስነኩ የተማማሉ ዜጎች ትህነግ አካሄዱ እስከወዲያኛው እንዳይነሱ አድርጎ አውድሞ ሊያጠፋቸው እንደሆነ ስለገባቸው ከቁም ሞት ይልቅ እስከመጨረሻው ለመዋደቅ ወደ ፍልሚያው እየገቡ ነው። በማዕበል የመጣውን ሃይል በማዕበል ለማስወገድ ፍልሚያው ልክ በጎንደር እንደሆነው እየሆነ ነው። ይህ ግንባር ከተመከተ ቡድኑ ያከትምለታል።

“ሁሉም ወደ ወሎ ይትመም፣ ይዝመት” -ሲሉ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በገሃድ ጥሪ አቅርበዋል። የአማራ ፋኖ እንደ ልማዱ ድል ሊያበስር እየተመመ ነው። ግንባር የደረሰም አለ። ከየአካባቢው ሃይል ተነቃንቋል። አፋር ሌላው ተጠቂና ለሃብቱ ሲባል እንዲወድም የተፈረደበት ሰላማዊ ህዝብ በመሆኑ ተነስቷል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም አሸባሪው የትህነግ ኃይል ያለማቋረጥ በርካታ ወገን ገድሏል፣ ሕዝብ አፈናቅሏል። መንግሥትና ሕዝብ የሠራውን መሠረተ ልማት አውድሟል ነው ያሉት። ጥቃቱን መመከት የሚቻለው ራስን በማደራጀትና በአንድነት በመነሳት ነውም ብለዋል።

የጥቃቱ ዓላማ ኢትዮጵያን ማፍረስና ምሥራቅ አፍሪካን ማተራመስ መሆኑን ገልጸዋል። ትግሉ የአማራና የአፋር ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ መሆኑን ነው የተናገሩት።ን የክልሉ መንግሥት አስቀድሞ ባደረገው የክተት ጥሪ የጠላትን ኃይል በተለያዩ አካባቢዎች መግታት መቻሉን ነው የገለፁት።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ ጋር በመሆን በተለያዩ አካባቢዎች መመከት መቻሉንም አስታውቀዋል። በቅርብ ጊዜ የጠላት ኃይል ከጀርባው ብዙ ሕዝብ በማስከተል ትኩረቱን ደሴና ኮምቦልቻ ላይ በማድረግ ጥቃት እያደረሰ መሆኑን ተናግረዋል።

ጥቃቱን ለመመከት ጀግናው መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሻ ከጀግናው የአካባቢው ሕዝብ ጋር ጠላትን እየተፋለመው መሆኑን ገልጸዋል። አኩሪ ጀብዱ እየተፈጸመ መሆኑንም አንስተዋል። የደቡብ ወሎ ሕዝብ በአንድነት በመትመም ከሠራዊቱ ጋር በመሰለፍ ስንቅ በማዘጋጀት እና ሞራሉን በማነሳሳት የጀግንነት ደጀንነቱን እያረጋገጠ ይገኛልም ነው ያሉት።

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2655 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply