ወደ ወሎ መዝመት ኢትዮጵያን የመታደግ ጉዳይ ነው! ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ

demeke zewdu

የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ መልዕክት

አሸባሪውንና ወራሪውን የትግራይ ኃይል ባህሪን ጠንቅቀን እናውቀዋለን። በደረሰበት ቦታ ኹሉ እስኪያልፍ ድረስ “ከእናንተ ጋር ችግር የለብኝም” ቢልም፣ ሕዝብን ከማጥፋት ወደኋላ አይልም። ሕዝባችን ላይ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ያደረሰውን ግፍና በደል እናውቀዋለን።

አሁኑ በተያያዘው የጦር ወረራው በየደረሰበት ቦታ ገና እግሩን ከመትከሉ ነው ሕዝብ እየጨፈጨፈ ያለው። በአፋር ጋሊኮማ፣ በአማራ አጋምሳ፣ ቆቦ፣ ንፋስ መውጫ፣ ጭና፣ ውርጌሳ… ብዙ ማይካድራዎችን አሳይቶናል፡፡ በላዔሰብ ስለመሆኑ ታውቆ ያደረ ጉዳይ ነው፡፡ አሁን ተጨማሪ እልቂት ለማድረስ ወሎ ላይ ያለ የሌለ ኃይሉን አሰልፏል፡፡ ለዚህ መድኃኒቱ እሱ በጀመረው መንገድ መዝመት ነው። ይህ ወረሪ ኃይል እየፈጸመ ያለውን መጠነ ሰፊ ወረራ መላ ኢትዮጵያውያን በሙሉ አቅማቸው ሊመክቱት ይገባል።

ጀግናው የወሎ ሕዝብ ከቦታው ባለመልቀቅና የጠላትን የእንቅስቃሴ መረጃዎች ለወገን ጦር በመስጠት፣ ምቹ ሁኔታ ሲያገኝ ጠላትን በጋራ በማጥቃት ሊያግዝ ይገባል። ❝የትግራይ ወራሪ ኃይል መጣ❞ ብሎ መሸሸ የለም። ራያ ላይ የሸሸውን ወልዲያ ላይ ዝም አይለውም። ወልዲያ ላይ የሸሸውን ደሴ የመግባት ዕድል ቢያገኝ ዝም አይለውም። ስለሆነም ሕዝባችን አንድ ልብ መካሪ፤ አንድ ቃል ነጋሪ ኹኖ እንዲመክት ወገናዊ ጥሪየን አቅርባለሁ፡፡

በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የምትኖሩ የአማራ ልጆች እንዲሁም መላ ኢትዮጵያውያን በወሎ ግንባር ያሰፈሰፈውን ወራሪ ኃይል በመመከት ወሎ ታሪካዊ የፍፃሜው ቦታ እንዲሆን ለማድረግ ርብርብ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ንቅናቄ መሀል ሀገር ያለውን ኢትዮጵያዊ ኃይል ያካተተ እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡ አሁን የሚጠበቀው ከሌላ ቦታ ወደ ወሎ መዝመት አንጅ ከወሎ መውጣት አይደለም፡፡

መላው የአማራ ሕዝብ ደመኛ ጠላቱ የሆነው ትህነግ ወሎ ላይ የከፈተውን የጦር ወረራ በማክሸፍ ህልውናውን ማፅናት አለበት፡፡ መዝመት የሚችል ይዝመት። ገንዘብ ያለው በገንዘብ ያግዝ። መኪና ያለው መኪናውን ለዘመቻ ያውል። ኹሉንም አቅም አሟጦ በመጠቀም ወራሪው ኃይል ወሎ ላይ ግብዓተ መሬቱ ሊፈፀም ይገባል፡፡ አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ኃይል የፈፀመው ወረራ የአማራ ጉዳይ ብቻ አይደለም።

በመላ ኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመ ነው። በዜጎቿና በክብሯ አልፎም በሉዓላዊነቷ ላይ የተቃጣ በመሆኑ ወደ ወሎ መዝመት ኢትዮጵያን የመታደግ ጉዳይ ነው፡፡ ወራሪው ኃይል ከኹሉም አካባቢ ተጠራርቶ ሲወረን እኛም ከመላ ኢትዮጵያ ተጠራርተን ወደ ወሎ መዝመት አለብን። በተባበረ ክንድ ወራሪውን ኃይል እስካልደመሰሰን ድረስ እንደ አማራም፣ እንደ ኢትዮጵያም ሰላም ማግኘት አንችልም። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ህልውና የሚጸናው በዚህ ደመኛ ጠላቷ መቃብር ላይ ነው!!

Leave a Reply