በማይጠብሪና ዓድዋ የትህነግ ሰራዊት ማሰልጠኛ ማደራጃና ትጥቅ አመሳስሎ የሚያመርትበት ማዕከል ላይ አየር ኃይል እርምጃ ወሰደ

ዓድዋ አካባቢ የሚገኘው፣ ጠላት ወታደራዊ ትጥቅ እና ወታደራዊ አልባሳትን አመሳስሎ የሚያመርትበት ማዕከል በአየር ድብደባ ከጥቅም ውጭ ሆነ

የኢፌዴሪ አየር ኃይል በአሸባሪው ህወሓት የወታደር ማሰልጠኛዎች፣ የመሳሪያ ማከማቻዎች፣ የነዳጅ ማከማቻዎች እና ሌሎችም ለሽብር ስራው የሚጠቀምባቸው የተመረጡ አካባቢዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ቀጥሏል።

ዓድዋ አካባቢ የሚገኘው፣ ጠላት ወታደራዊ ትጥቅ እና ወታደራዊ አልባሳትን አመሳስሎ የሚያመርትበት ማዕከል በአየር ድብደባ ከጥቅም ውጭ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ዓድዋ አካባቢ የሚገኘው፣ ጠላት ወታደራዊ ትጥቅ እና ወታደራዊ አልባሳትን አመሳስሎ የሚያመርትበት ማዕከል በአየር ድብደባ ከጥቅም ውጭ ሆኗል ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ኢፕድ ባገኘው መረጃ ዛሬም በምዕራብ ግንባር ማይጠብሪ ላይ የሚገኘውን የአሸባሪው ማሰልጠኛና የሰው ኃይል ማደራጃ ጣቢያ ላይ አየር ኃይላችን እርምጃ ወስዷል።

ባለፉት ቀናት አየር ኃይሉ ንጹሃን ዜጎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የተመረጡ የአሸባሪው ህውሓት የሚጠቀምባቸው ዒላማዎች ላይ የተሳካ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑ ይታወቃል።

(ኢ ፕ ድ)

See also  "በቡጢ መታኝ ስወድቅ ደፈረኝ" የ80 ዓመት አዛውንት

Leave a Reply