ዕርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ከገቡት አንድ ሺ 111 ከባድ ተሽከርካሪዎች 869ኙ አልተመለሱም


የሰብዓዊ ዕርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ክልል ከገቡ አንድ ሺ 111 ከባድ ተሽካርካሪዎች ውስጥ 869ኙ ተሽካርካሪዎች ትግራይ መቅረታቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ገለጹ፡፡

አምባሳደር ፍጹም በቲወተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ አሳልፎ የአገር መከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ክልል ከወጣበት ጊዜ አንስቶ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብዓዊ ዕርዳታ 34 ሺ 380 ቶን እህሎችና አልሚ ምግቦችን ወደ ትግራይ ክልል ልኳል።እነዚህን የሰብዓዊ ዕርዳታዎች ጭነው ወደ ትግራይ ከሄዱት አንድ ሺ 111 ከባድ ተሽከርካሪዎች ውስጥ የተመለሱት 242 ተሽከርካሪዎች ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ መንግሥት ካላፈው ሰኔ መጨረሻ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ የህይወት አድን ምግቦችና የህክምና ቅሳቁሶችን የሚያደርሱ አንድ ሺ 111 ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ መሄዳቸውን ጠቁመው፤ ከእነዚህ ውስጥ 869ኙ ከባድ ተሽከርካሪዎች ትግራይ ውስጥ አስቀርቶ ተሽከርካሪዎቹን አሸባሪው ሕወሓት አማራንና አፋር ክልሎችን ለመውረርና ለማውደም የሚያስችለውን ታጣቂ ኃይል እያመላለሰባቸው ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

(ኢ ፕ ድ)

Leave a Reply