ኩታ በር ነጻ ስትወጣ አቶ ጌታቸው የተዘጋውን የኮምቦልቻ አየር ማረፊያ የጥቃት ነጥብ መሆኑንን አስታወቁ

ኩታ በር በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እጅ መግባቷን እማኞች እየገለጹ ባለበት፣ መከላከያ ከልዩ ሃይል፣ ሚሊሽና ፋኖ ጋር በመሆን እይጻዳ ወደ ወርቃሪያና አባሰላማ እያመራ መሆኑ በሚነገበት በአሁኑ ወቅት አቶ ጌታቸው በኮምቦልቻ አየር ማረፊያ አውሮፕላን እንዳያርፍ የትህነግ ሃይል ማሳሰቡ አመለከቱ።

የትህንግ ሃይል ደሴንና ኮምቦልቻን ለመቆጣጠር ሰላሳ ኪሎሜትር እንደቀረው በመጥቀስ አቶ ጌታቸው ከሳምንት በፊት አስታውቀው ነበር። እሳቸውን ተከትሎም የትህነግ ደጋፊዎች ” በመጨረሻ ደሴ” በማለት በማህበራዊ ሚዲያ ምስልና ጽሁፍ ሲያሰራጩ ነበር። ያነሱትም አሉ።

ይህንኑ ተከትሎ የክልሉ መንግስት በሰሜንና ደቡብ ጎንደር እንዳደረገው ክተት አውጆ ወረራውን እንደቀለበሰ በወሎ ግንባርም ክተት በማወጅ ሕዝብ ወደ ግንባር እንዲተም፣ የማይችል በደጀንነት እንዲያግዝ ጥሪ አቅርቧል። በተመሳሳይ የአየር ሃይል ከጀርባ የጠላትን ሃይል፣ ሎጅስቲክ፣ መሳሪያና ማስለጠኛ ማጥቃት ጀምሮ ትህነግ ያሰለፈርውን የሰው ጎርፍ ማስቆም እንደቻለ በየአቅጣጫው ከተለያዩ የወታደራዊ ጥቃት ዜናዎች ጋር እየተሰማ ሰንብቷል።

መከላከያም ትህነግ ቀጣይ ውጊያ ለመዋጋት የመጨረሻ ተጠባባቂ ሃይሉን እንዳንቀሳቀሰ አመልክቶ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንን አየር ሃይልን ጠቅሶ አመልክቷል። ከደጀን ህዝብ፣ ከልዩ ሃይልና ፋኖ ጋር በጋራ በተካሄዱ ኦፕሬሽኖች ስም ጠቅሶ የወሰደውን ጥቃትና ያደረሰውን ጉዳት ይፋ እያደረገ ይገኛል።

በዚህ መሃል ነው አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ስራ ካቆመ ሁለት ሳምንት የሞላውን የኮምቦልቻ የሲቪል አየር ማረፊያ “አውሮፕላን ማረፍና መነሳት አይችልም” ሲሉ ውሳኔው ከባድና የማያወላዳ እንደሆነ ያስታወቁት። አያይዘውም የኮምቦልቻና የደሴ ሕዝብ በቤቱ ተቀምጦ ንብረቱን እንዲጠብቅ መክረዋል። ለወትሮ በደረሰበት የአማራ ክልሎች በሙሉ ንብረት ሲያግዝ፣ መሰረተ ልማት ሲያፈርስ፣ የደረሰ ማሳ ሲያጭድና ሲያጓጉዝ የነበረው ሃይል ለምን ኮምቦልቻና ደሴ ሕዝብ ቤቱ እንዲቀመጥ ጥሪ እንዳደረገ በቲውተር ገጻቸው ይፋ አላደረጉም።

ከመንግስት ወገን በይፋ ባይሰማም በወሎ ግንባር ካለፉት ሰባት ቀናቶች በፌት እንደነበረው ሳይሆን አሁን ውጥረቱና በመከላከያ ላይ የነበረው ጫና እንደቀነሰ ይሰማል። ሕዝቡም ወደ ግንባር ዘልቆ የሰው ማዕበል ያሰለፈውን የትህነግን ወራሪ ሃይል ለመዋጋት ከወሰነ በሁዋላ ነገሮች መላካቸውን በመጠኑም ቢሆን መቀየራቸውን የሚገልጹ አሉ። ከዛም አልፎ በሳምንቱ መጨረሻ ነገሮች ሙሉ በሙሉ መልካቸውን እንደሚቀይሩ የሚያመላክቱ መረጃዎች እየወጡ ባለበት ወቅት አቶ ጌታቸው ይህን ማለታቸው አስገራሚ ሆኗል።

አቶ ጌታቸው ጎንደርን በሰዓታት እንደሚቆጣጠሩ፣ ባህርዳርንም እንደሚይዙና ወደ ደብረብርሃን እንደሚያመሩ ቀደም ባሉት ጊዚያት ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው። ይህን የቲውተር መረጃ ከማሰራጨታቸው በፊት በትግራይ ቲቪ ቀርበው ጦርነቱ የቀናት ወይም የሳምንት ጉዳይ መሆኑንን አመልክተው ነበር። በዚሁ የውይይት ክፍለ ጊዜ አንድም “የትግራይ ተወላጀ ቢነካ ዋ” በሚል በየከተማው በሰላም የሚኖረውን የትግራይ ተወላጅ ሰላም የሚያውክ ገለጻ ሲሰጡ ነበር።

እጅግ በንዴትና በቁጣ.፣ በማስጠንቀቂያና በስድንብ በታጀበው ንግግራቸው ” ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ የድርጅትዎ አስተዋጾ ምን ይሆናል” ተብለው በውይይቱ ላይ ተጠይቀው ነበር። ለኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ተቆርቋሪ ሆነው የቀረቡት አቶ ጌታቸው ሴኮ ቱሬ በአርባ ደቂቃ ዓመድ አደረግነው ሲሉ የኢትዮጵያ መከላከያ ላይ የተወሰደውን የክህደት እርምጃ ማን እንደፈጸመው አወያይዋ አላነሳችም።

ትህነግ ሰሞኑንን “መንግስታችሁን ክዱና እኔን ዳግም አንግሱኝ” የሚል መግለጫ ማሰራጨቱ የሚታወስ ነው።

በሌላ ዜና የአፋር ልዩ ሃይል መጋላ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ነጻ ማውጣቱን በመስል የተደገፈ መረጃ ተረጋግጧል። ትህንነግ ሰፊ8 ቁጥር ያለው ሃይል በየአቅጣጫው አሰልፎ የገጠመውን ጦርነት የአፋር ክልል መመከቱ ተጠቁሟል።

Leave a Reply