“ወታደራዊውን ጉዳይ ለእኛ ተውልን” ሌ/ጄ አበባው ታደሰ

“እናንተ ደጀን በመሆን ከጀርባችን ሁኑልን እንጂ ወታደራዊ ጥበቡን ለእኛ ተውልን” የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታምዦር ሹም ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ማስታወቃቸው ተሰምቷል። መከላከያ ሰራዊትንም ሆነ ደጀኑንን ሕዝብ በወሬ ለማተራመስ ተከፍሏቸው የሚሰሩ፣ አገር ወዳድ መስለው የሚቀስቀሱና በባንዳነት አገር እያስመቱ ያሉ ላይ ሕዝብ እርምጃ እየወሰደ መሆኑም ተሰምቷል። ጠላትንም ለመመከት ህዝብ እየጎረፈ ነው።

“ኢትዮዽያ እየሞትን የምናስቀጥላት እናት ሀገራችን ናት። ይሄ ከአባቶቻችን የወረስነው እውነተኛው ማንነታችን ነው። ለአማራ፣ ለአፋር እንዲሁም በአጠቃላይ ለመላው የኢትዮዽያ ህዝብ የማስተላልፈው መልእክት ቢኖር ‘ኢትዮዽያን አፈርሳለሁ!’ ብሎ በአደባባይ ተናግሮ የተነሳው ጠላታችን ግብአተ መሬት በቅርቡ ይጠናቀቃል ሆኖም ግን የአሸባሪው ፕሮፓጋንዲስቶች እና የእርሱ ተላላኪ ባንዳዎች በሚነዙት ወሬ ባለመሸበር እንዲሁም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሙያዊ ክህሎት ሳይኖራቸው ከሀሰተኛ መረጃዎች ተነስተው ያልተገባ አስተያየት እና ነቀፋ ለሚሰጡ ቡድኖችና ግለሰቦች ጆሮ ሳትሰጡ በውስጣችን የተሰገሰጉ የአሸባሪው ተላላኪዎችን እና ባንዳዎችን በመያዝ፣ አካባቢያችሁን ከአሸባሪዎች በመጠበቅ እና ከሰራዊቱ ጀርባ ደጀን በመሆን የጀመራችሁትን ድጋፍ አጠናክራችሁ በመቀጠል ሞራል ሁኑልን እንጂ ወታደራዊ ጥበቡን ለእኛ ተውልን! ” ነው ያሉት ሌ/ጄ አበባው ታደ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በንፋስ መውጫ ባንዶችን ልሳናቸውን በማዘጋትና በመቆጣጠር ወረራውን መቀለበስ እንደተቻለ የሚናገሩ ወገኖች በወሎ ግንባር በርካታ ባንዳዎችና አገር ወዳድ መስለው ከጀርባ ለጠላት መረጃ የሚሰጡ ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተሰምቷል። ሕዝብ መካከል ሆነው የሃሰት መረጃ በማሰራጨት የሚሰሩትንም ሕዝብ እያጋለጠ በመስጠት ላይ መሆኑ ተሰምቷል።

ኢትዮጵያ በየጊዘው አሜካላና እንግዴ የሆኑ ጥቂት ጭንጋፎች እንደሚያጋጥሟት በመግለጽ በየግንባሩ በሁለት ልብ የሚያነክሱና የሚሰሩ እየተያዙ መሆናቸውም መረጃዎች በተከታታይ እየወጡ ነው። አዲስ ዝመን እንዳስታወቀው በአክቲቪስት ስም አገር እየበተኑና ለትህነግ እየሰሩ ያሉትን ሕዝብ ለይቶ ቢውቃቸውም ትዕግስቱ ከልክ ማለፉን ጠቁሟ አቋሙን ይፋ አድርጓል። አንዳንድ የዩቲዩብ ተንታኝ ነን የሚሉ በተለይ አማራውንና አፋሩን መሰረት አድርጎ የሚደረገውን ዘመቻ በገሃድ እየደገፉ ቅስቀሳ ሲያደርጉ መታየታቸውን ዘገባው አስታውሷል። ከሽብርተኛ ቡድኖች ሃሳብ ጋር በአክቲቪስም ስም ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ተመልክቷል።

በተመሳሳይ በወሎ ግንባር ሕዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የጠላትን ሃይል ለመደምሰስ ወደ ግንባር እየዝመተ መሆኑንን የካባቢው አስተዳደሮች በምስልና በድምጽ በተደገፋ ማስረጃ ሲተሙ አሳይቷል።


You may also like...

Leave a Reply