የወሎ ግንባር ወደ መቋጫው እያመራ ነው፤ “የሚያልቀው ያሳዝናል”

“በወሎ ግንባር ትህነግ ያሰለፈውና ከስር ከስር የሚተካው ሃይል ብዛቱ በትግራይ ሰው የቀረ አይመስልም” ሲል ለአዲስ አበባ ዘጋቢ እማኝነቱን የገለጸው የደሴ ነዋሪ ” ማልቀስ ለወላድ ነው። የሰው ልጅ፣ ምንም የማያውቁ ታዳጊዎች አለቁ። አየር ሃይል እሳቱን እየተፋ …” አልጨረሰም። መፍትሄው ምን እንደሆነ አልታይ ብሎታል። የሚያስጨንቀውም እሱ ነው።

አቶ ጌታቸው ረዳ ” ኮምቦልቻ ለንገባ ነው፤ ተጨማሪ የድል ዜና አለ” ሲሉ ከማስጠንቀቂያ ጋር የጦር ግንባር ድል ዜናና ቀጣይ ድል ካስታወቁ ዛሬ ሶስተኛ ቀን ነው። የጀርመን ሬዲዮ በዋናው ገጹ ሳይሆን በፌስ ቡክ አምዱ ኩታ በር መያዟን አመልክቶ ኮምቦልቻ እንደምትያዝ ከጻፍ ዘሬ አምስተኛ ቀን ነው። የመቀለ ዘጋቢ እንደነገረው ጠቅሶ ጀርመን ሬዲዮ እንዳለው ከሆነ የትግራይ ተገንጣይ ሃይል ኮምቦልቻን ለመያዝ በቅርብ ርቀት ላይ ነበር።

ከአምስት ቀን በሁዋላ የግንባር ዜና መልኩን እንደቀየረ በሚገለጽበት በአሁኑ ወቅት የትህነግ ሃይል “መግለጫ” በሚል የመከላከያ ሰራዊት እጅ እንዲሰጥ አሳስቧል። መግለጫውን ” በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተንጠለጠለ ሃይል” ሲሉ የአብን ምክትል ሊቀመንበር ምስክርነታቸውን ሲሰጡ አመልክተዋል።

May be an image of text

በዚህ መካከል ” የትግራይ ወራሪ ሃይል በሉት” ሲሉ ከክልሉ ወጥቶ ንጽሃንን ደጃቸው ድረስ መጥቶ እየዘረፈ፣ ማሳቸውን እያጨደና ተቋማትን እያወደም ያለውን ሃይል እንዲዋጉ አቶ ደጉ በገሃድ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ የወሎ ህዝብ ሰሜንና ደቡብ ሳይል፣ ገጠርና ከተማ ሳይል የሰው ጎርፍ ለመመከት ወደ ግንባር ተሟል። በውስጥ ሆነው የሚያስተኩሱትን እየለቀመ ለህግ እያቀረበ መሆኑ ተሰምቷል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር የሱፍ ኢብራሂም በሰጡት ምስክርነት ” ወገን ጦር በወሰደው እርምጃ አሸባሪው ቡድን እየተሽመደመደ መሆኑን ተመልክቻለሁ” ብለዋል።

አቶ የሱፍ እንዳሉት የደሴና አካባቢው ወጣቶች ለወገን ጦር ውጤታማ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን፣ ጦርነቱ በሚካሄድበት ቦታ የሚገኙት አቶ የሱፍ ኢብራሂም ለአሚኮ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል። የወገን ጦር በጠላት ላይ በወሰደው እርምጃ አሸባሪው ቡድን መራመድ በማይችልበት ደረጃ እየተሸመደመደ መሆኑን ተመልክቻለሁ ብለዋል፡፡

መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻው ገዢ ቦታዎችን በመያዝ በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ኪሳራ እያደረሱ መሆኑን፣ የደሴ ከተማ፣ የኩታበር፣ የተሁለደሬ እና አካባቢው ወጣት ምሽግ ድረስ በመግባት ውኃ፣ ትጥቅ እና ስንቅ በማቅረብ ላይ መሆኑንን፣ ከዚያ ባለፈም ለወገን ጦር መረጃ በመስጠት ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠሉን አቶ የሱፍ መስክረዋል።

See also  የአረብ ሊግ የሕዳሴ ግድብ አመልክቶ ያወጣውን መግለጫ " የአንድ አገር ቃል አቀባይ" ስትል ኢትዮጵያ አጣጣለች

በዘመቻውም የማኅበረሰቡ ጉልህ ሚና እንዳለው ሲያስታውቁ “የወገን ጦርን ሕዝቡ በሚገባው ልክ በመደገፉ ጠላት ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ እንዲቀር አድርጎታል” ብለዋል። ጦርነቱ ሀገር አፈርሳለሁ ብሎ ከተነሳ ባንዳ ጋር በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለትግሉ በመረባረብ የሚጠበቅበትን ኀላፊነት መወጣት እንዳለበት አስረድተዋል። ለኢሳት ሲናገሩ ደግሞ “ይህ ሃይል እንኳን ኮምቦልቻና ደሴን ሊይዝ መቀለ ተመልሶ የመግባት እድል የለውም”

የኢትዮ 12 ምስክር እንዳለው አየር ሃይል እያገዘ፣ በጥምረት ከምድር ሃይሉ ጋር በሚወስዱት ጥቃት እያለቀ ያለው ወጣት እጅግ እንደሚያሳዝንና ይህ ሁሉ ሰው እንዲያልቅ የሚደረግበት ምክንያት እንደማይገባው አመልክቷል። የትግራይ ምስኪኖች ከክልላቸው ወጥተው እየረገፉ መሆኑ እጅግ እንዳሳመመው አመልክቷል። ይህን ሲል መስዋዕትነቱ ከወገንም መኖሩ እንደማይካድ አመልክቷል። ግን አይወዳደርም።

እንደ እሱ ግምት ትህነግ ተተኪ እያስገባ ውጊያውን አክርሮ ከተማ ለመቆጣጠር ያለው አቅም የተመናመነ፣ ምን አልባትም በሁለትና ሶስት ቀናት ውስጥ ተጨባጭ ለውጥ ይታያል። በተያያዘ ጀግናው የመከላክያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ሀይል ፋኖ እንዲሁም የአማራ ሚሊሻ በቦሩ ሜዳ ወራሪውን የትህነግ ታጣቂ እየደመሰሰ መሆኑንን እዛው ሆኖ በላከው ቪዲዮ ቴውድሮስ አስታውቋል። የሚወራውና በተግባር እየሆነ ያለው የተለያየ መሆኑንን አመልክቷል።

አየር ሃይል ጥቃት መሰንዘር ከጀመረ ወዲህ ትህነግ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት፣ ጥቃቱም በተጠኑ ቦታዎች የተደረጉና ዒላማቸውን የመቱ መሆናቸውን መንግስት አመልክቷል።

Leave a Reply