ከሩብ ቢሊዮን ብር በላይ የታቀፈቸው ” የትህነግ መሪ” ሰንሰለታማ የዝርፊያ ድራማ

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ሆኖ ለማንም በማይገባ ምክንያት አፋራና አማራን ወሮ የያዘው ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሄር የፋይናንስ መረጃ ደህንነት ምክትል ዳይሬክተር በነበሩበት ወቅት 267 ሚሊዮን ብር በወንዳምቸው ዳዊት ገብረ እግዚአብሄር ስም ንግድ ባንክ መግባቱን ጠንቅቀው ያውቃሉ። ጨዋታው የሚጀምረው እዚህ ላይ ነው።

አቶ ዳዊት ይህን ያክል ብር በአንዴ ንግድ ባንክ ሲያስቀምጡ ” ከየት አመጡ” አልተባለም። ገንዘቡ ረሽም ጊዜ ባንክ መቀመጡ ደግሞ “ለምን?” የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ቀጥሎ አቶ ቱሉ ጣፋ ድራማውን መሪ ሆነው ብቅ ይላሉ። አቶ ቱሉ ይህን ሁሉ ብር ለመውሰድ ሲመቻቹ አንድ በባለሙያዎችና በህግ ሰዎች የተመከረበት ሰንሰለት ይዘጋጃል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር እንደደረሰበትና እንዳመከነው የገለጸው የወንጀል ሪፖርት እንደሚያስረዳው ድራማው የተዋቀረው ከቀበሌ ጀምሮ ነው። ዋናው አስተኳሾች ግን የተደራጁ የባንክ ሰራተኞች ናቸው።

የፋይናንስና ንግድ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር ብርሃኑ ገለጻ አቶ ዳዊት 276 ሚሊዮን ብር ንግድ ባንክ እንዳላቸው መረጃውን ለሰነሰለቱ ሰዎች ያቀበሉት የባንክ ሰዎች ናቸው። የባንክ ሰዎቹ በሰጡት መረጃ መሰረት በህጋዊ መንገድ ብሩን ወደ አቶ ቱሉ አካውንት ለማዞር በቡና ባንክ አዲስ የሂሳብ ደብተር ይዘጋጃል።

አቶ ቱሉ 121 ሰዎች መታወቂያ እንዲወስዱ በተደረገበት ቤት ተመዝግበው የነዋሪነት ማረጋገጫ ያገኛሉ። በዛው መታወቂያ አድራሻ ህጋዊ ሆነው የህግ ሰዎች በሚያስቀምጡት የአሰራር ሂደት መሰረት ስራው ይጀመራል።

አቶ ቱሉ ከአቶ ዳዊት ጋር የስራ ውል እንደነበራቸው ተደርጎ የተቀናበረው ሰነድ በግልግል ዳኝነት ህጋዊ ውሳኔ እንደተሰጠው አስመስሎ በማቅረብና በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአፈፃፀም ችሎት እንዲከፈት በማድረግ በህገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ ለመውሰድ ጨዋታው ይጀመራል። ተጀምሮም አክተሮች እየጨመረ ወደ መገባደጃው ያመራል።

ክብሮም ወልዱ በሚባሉ በአካል በሌሉና በማይታወቁ ሰው ተወስኖ ቀርቧል የተባለው የግልግል ውሳኔ አግባብነት የሌለው መሆኑ እየታወቀ ” ቅድሚያ መደለያ 400 ሺህ ብር ተቀበሉ” የተባሉ ዳኛ አፈጻጸም እንዲከፈት ያዛሉ። ሂደቱ እዚህ ሲደርስ አቶ ቱሉ በተዘጋጀላቸው ደረቅ ቼክ ለሌሎች የሰንሰለቱ ተባባሪዎች ዳኞችን ጨምሮ ብሩ ሲለቀቅ የሚሰጡትን ገንዘብ በመጻፍ ቼክ ያድላሉ። ፖሊስ እንዳለው።

ትክክል አለመሆኑን እያወቁ በመምሳጠር “ትክክል ነው” በማለት በወንጀሉ የተሳተፉ ሌሎች ግብረ አበሮች ሐምሌ 16 ቀን 2013 ዓ.ም አፈፃፀም እንዲከፈት ፍርድ ቤት በጠየቁት መሰረት ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 11ኛ ወንጀል ችሎት ሲሆን የተጠየቀው ጥያቄ የፍርድ ባለመብት ተብሎ የቀረበው ቱሉ ጣፋ በዳዳ የሚባል ግለሰብ ሲሆን የፍርድ ባለ እዳ ሆኖ የቀረበው ተጠርጣሪ ዳዊት ገ/እግዝሐብሔር መሆናቸው ተዘርዝራል።

ረቂቅ ዜናዊ የምትባልና አሁን ለጊዜው አገር ቤት የለችም የተባለች ተጠርጣሪ የአቶ ዳዊት ወኪል በመሆን አቶ ቱሉ ላቀረቡት የበደል ጥያቄ ደጋፊና እማኝ መሆናቸውን ፖሊስ አውስቷል።

ከዚህ በፊት ሁለቱ ግለሰቦች የስራ ግንኙነት ያላቸው በማስመሰል የብድር ውል በማቅረብ ገንዘቡን አልከፈለልኝም በማለት ወደ ገላጋይ ዳኛ ወስደው ክርክር እንዳደረጉ፣ የተጠየቀው 276 ሚሊየን ብር አቶ ዳዊት ገ/እግዝሐብሔር በተባሉት ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚገኝ ገንዘብ በወንጀሉ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች ሌሎች መረጃ የሚሰጡ ግለሰቦችን በመጠቀም የባንክ ሂሳብ ደብተሩ ላይ ያለውን የገንዘብ መጠን ካጠኑ በኋላ ለመውሰድ ሙከራ ማድረጋቸውን፣ ይህንኑ የተቀነባበረ ወንጀል ፖሊስ ሲከታተለው እንደነበር፣ በመጨረሻም ከሚፈለጉት አስራ ሶስት ተጠርጣሪዎች አስሩ መያዝቸውን ረዳት ኮሚሽነሩ አስታወቀዋል።

ፖሊስ ይህን ያህል ብር በአንድ ጊዜ ባንክ ገብቶ ለረዥም ጊዜ መቀመጡና ንብረቱ ደግሞ የወይዘሮ ፈትለወርቅ ወንድም መሆኑ ፖሊስ ምርመራውን እንዲያሰፋ አስችሎታል። ፖሊስ እንዳለው አቶ ቱሉ ፊት ሆነው ድራማውን እንዲሰሩት ይደረጉ እንጂ ገንዘቡ ለትህነግ ሽብር ተግባር ሊተላለፍ እንደነበር ጥርጣሬው ሰፊ ነው። የአቶ ዳዊት ህጋዊ ወኪል የተባሉ ረቂቅ ዜናዊ ከአገር መውጣታቸው ሪፖርቱ ሲቀርብ ተመልክቷል።


Haroon Wancii naannawa turiizimii ta’uun filatame
Yaa’ii Waliigalaa Dhaabbata Turiizimii Adduunyaa 24fa Ispeen, Magaalaa Maadriiditti taa’ameen Haroon Wancii …
Qaamni hidhatee bosona jiru waamicha abbootii Gadaa kabajee hawaasatti deebi’uu qaba jedhame
Abbootiin Gadaa Sikkoo- Mandoo dargaggoota Godina Arsii miseensa Shanee ta’anii bosonatti galuun …
Ethiopians urge U.S. embassy to stop spreading false information
Ethiopians and Africans have commenced petition against the U.S. Embassy in Ethiopia …
Gov’t continues to provide assistance in conflict zones
Photo by fortune – Mamo Meheretu, chief trade negotiator and senior adviser …
ከ32 ቢሊየን ብር በላይ ሀሰተኛ ግብይት መፈጸሙ ተገለጸ
ህገ-ወጥ ድርጅቶች ሲጠቀሙባቸው ከነበሩ የካሽ ሬጂስተር ማሽኖች ከ32 ቢሊየን ብር በላይ ሀሰተኛ …
ፀረ ሰላም ኃይሎች በሱዳን ድንበር ሰርገው ለመግባት ያደረጉት ሙከራ ከሸፈ
ከኢትዮጵያ የውስጥና የውጭ ጠላቶች ተልዕኮ ተቀብለው በድንበር አካባቢ ሰርጎ ለመግባት በሞከሩ የአሸባሪዎቹ …

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2654 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply