ኤፍ ኤም ጣቢያዎች የውጭ አገር ፕሮግራሞችን ሊንክ አድርጎ ማሰራጨት ተከለከሉ

በሀገር ውስጥ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የውጭ አገር ፕሮግራሞችን ሊንክ አድርጎ ማስተላላፍ ከዛሬ ጀምሮ መከልከሉን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በሀገር ውስጥ ፈቃድ ያልተሰጣቸው የውጭ ሀገር የሬዲዮ ጣቢያዎች ፈቃድ ባላቸው የአገር ውስጥ የኤፍ ኤም ማሰራጫ ጣቢያዎች አማካኝነት ፕሮግራሞቻቸውን ሲያስተላልፉ መቆየታቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ እድሪስ በሀገር ውስጥ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የውጭ ሀገር ፕሮግራሞችን ሊንክ አድርጎ ማስተላላፍ ከዛሬ ጀምሮ ተከልክሏል።

በውጭ ሀገራት የሚሰሩ የሬዲዮ ጣቢያዎች የሚተላለፉ ፕሮግራሞች የሀገር ውስጥ ህግና ስርዓትን ተከትለው አይካሄዱም፡፡

“በፕሮግራሞቹ የአንዳንድ ሀገራት አቋም መግለጫ ሲተለለፍ የሚታይበት እና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ግምት ውስጥ ያላስገባ ሲሆን ተስተውሏል” ብለዋል።

በተጨማሪም የሀገሪቷን ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያላስገቡ ፕሮግራሞችም ሲተላላፉ እንደነበርም አስታውሰዋል።

እነዚህ አካላት በሀገር ውስጥ ፈቃድ ያላገኙ በመሆናቸው የሚተላለፉ መርሃ ግብሮችን በመከታተል ግብረ መልስና የማስተካከያ ሃሳብ ለመስጠት የሚቻልበት ሁኔታ አለመኖሩንም ገልጸዋል፡፡

በሀገር ውስጥ የሚያስተላልፉ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎችም ፕሮግራሞቹ ላይ የሚያደርጉት ቁጥጥር አነስተኛ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የተጠቀሱትን ሃሳቦች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ባለስልጣኑ ከዛሬ ጀምሮ ከውጭ ሚዲያዎች ወደ ሀገር ውስጥ የኤፍ ኤም ጣቢያዎች ሊንክ አድርጎ ማስተላለፍን ከልክሏል። ፋና እንደዘገበው


ተጨማሪ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሊደረግ ነው
የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ክፍተት በማጥበብ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ የሚያስችል ተጨማሪ …
ከአርሰናልና ከሲቲ የተሻለ ዕድል ለማን? አሃዛዊ መረጃዎች ወዴት ያደላሉ
ከሚታወቅበት ጥለዛ በየጊዜው መሻሻል እያሳየ ውብ ኳስ ባምስኮምኮም ላይ ያለው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር …
የበዓሉ ግርማ ኦሮማይ – ዛሬ ለምን?
ትህነግ የሚመራው ኢህአዴግ በውስጡ በተፈጥሩ ሃይሎችና በህዝብ ተቃውሞ ተደጋጋፊነት ከስልጣን ሲወርድ በቅጽበት …
የበታችነትና የበላይነት ስቃይ “እኩል የኢትዮጵያ ስጋት ናቸው”መባሉ ጫጫታ አስነሳ?
ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በግልጽ አላፊነት የማይወሰድበትና ባለቤቱ ግልጽ ወጥቶ የማይመራው መተራመስ ህዝብን …
ሩሲያ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቿን ቤላሩስ ውስጥ ልታጠምድ ነው
ሩሲያ ስልታዊ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቿን በአጋሯ እና በጎረቤቷ ቤላሩስ ውስጥ በማንኛው ጊዜ …
ኦሮሚያ በአራት ወር መቶ ሺህ ዘመናዊ የገጠር መኖሪያ ቤቶች ሊገነባ ነው
በቀጣዮቹ አራት ወራት በኦሮሚያ ክልል 100 ሺህ ዘመናዊ የገጠር መኖሪያ ቤቶች ግንባታ …

Leave a Reply