ከአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የተላለፈ የአስቸኳይ ጥሪ

የትህነግ አሸባሪና ወራሪ ኃይል በአማራ ክልል ሕዝቦች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት እየፈፀመ ህዝቡን እየገደለና እያዋረደ፤ ንብረቱን እየዘረፈ፣ እያወደመ እና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የመጨረሻ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ነው፡፡ ይህንን በተጨባጭ እየገጠመን ያለውን የሕልውና አደጋ ለመቀልበስ በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥርዓት ብቻ ማሸነፍ የማይቻል ሆኖ በመገኘቱ፤

የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ጥቅምት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ ዙር፣ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የሚከተሉትን የአስቸካይ ጥሪ ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡

1. ከሚሰጡት አገልግሎት አስፈላጊነት አኳያ እየተመዘነ የሚወሰን መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ማንኛውም የመንግስት ተቋም መደበኛ አገልግሎቱን አቋርጦ በጀቱን ጨምሮ ሁሉንም ነገር የገጠመንን የህልውና ዘመቻ ለመቀልበስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እንዲረባረብ ተወስኗል፣

2. ሁሉም የመንግስት ተሸከርካሪ ወደ አንድ ማዕከል በማሰባሰብ ለሕልውናው ዘመቻ አገልግሎት እንዲውል እንዲደረግ፣

3. የግል ተሸከርካሪ ባለቤቶች ለሕልውና ዘመቻው ስኬት ሲባል በተፈለገ ጊዜ ሁሉ ተሸከርካሪዎቻቸውን በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተወስኗል፣

4. በየደረጃው የሚገኝ አመራር የሕልውና ዘመቻውን ተቀብሎ የሚሰለፈውን ሕዝብ አደራጅቶ ከፊት ሆኖ እየመራ ወደ ግንባር እንዲዘምት ይህን በማያደርጉ አመራሮች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ተወስኗል፣

Leave a Reply