በራማ በኩል የኤርትራ ልዩ ሃይል ወደፊት ማጥቃት ወደ አድዋ ጉዞ ጀምሯል

መላውን የትግራይ ሕዝብ ወታደር እንዳደረገ ያስታወቀው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በራማ በኩል በኤርትራ ሰራዊት ላይ የጀመረውን ማጥቃት በማክሸፍ ወደፊት እያጠቁ መሆኑ ተመለከተ። የቀድሞ ሌተናል ጀነራል ጻድቃን “ኢሳያስ መወገድ አለበት” ሲሉ በቅርቡ መናገራቸው ይታወሳል። በደሴ ኤርትራዊያን መገደላቸው እየተሰማ ነው።

ኤርትራ ምንግዜም ትህነግ ስጋቷ እንደሆነ ስታስታውቅ መቆየቷ ይታወሳል። በቅርቡ ኢሳያስ “ኤርትራ ወያኔንን ለማጥፋ የትም ቦታ ሄደን እርምጃ እንወስዳለን” ማለታቸውም አይዘነጋም። በይፋ ኤርትራ በራማ ግንባር ጦርነት መጀመሩን አላስታወቀችም። የትህነግ አመራሮችም ቢሆኑ ለጊዜው ያሉት ነገር የለም። ይሁን እንጂ ከፊል ኤርትራን ተቆጣጥሮ የትግራይ አካል የማድረግ እቅድ ለመተግበር ዝግጅት እንዳላቸው ይታወቃል።

ነዋሪነታቸው በአውሮፓ የሆኑ እንዳስታወቁት የኤርትራ ሰራዊት በራማ በኩል የተከፈተበትን ጥቃት መክቶ ሙሉ በሙሉ ማጥቃት ወደ አድዋ አቅጣጫ እንዳቀና አስታውቀዋል። በትክክል ወደየትኛው ከተማ እንደሚያቀና ባይገልጹም ከሰሜን ወደ ደቡብ እያመራ እንደሆነ አመልክተዋል። የጎግል ካርታ እንደሚያሳየው አክሱምና አድዋ ይቀርቡታል።

መንግስት እንዳስታወቀው በተለያዩ ግንባሮች ይዞታውን እያሰፋ ማጥቃት የጀመረው የአገር መከላከያ ከጀመረው ጉዞ ጋር ተናቦ የሚደረግ ጥቃት ስለመሆኑ ግን ዜናውን ያስታወቁት ክፍሎች አልገለጹም።

ደሴና ኮምቦልቻ ሰርጎ በመግባትና በከተማዎቹ ከፍተኛ ዝርፊያና ግድያ እያካሄደ እንደሆነ የተነገረለት ” የትግሬ ወራሪ” በኮምቦልቻ ከመቶ ሃያ በላይ ወጣቶችን አሰልፎ መረሸኑ ተገልጿል። በደሴ ኤርትራዊያንን መግደሉ ቢገለጽም መንግስት ይፋ አላደረገም። ከኤርትራ ወገንም የተባለ ነገር የለም።

ትህነግ “የኢርትራን ህዝብ ስም አታንሱ” በሚል አዲስ በያዘው የፕሮፓጋንዳ ስልት መሰረት ደጋፊዎቹም ሆኑ አመራሩ ለይተው ፕሬዚዳንት ኢሳያስን ብቻ እንደሚያጠቁ ስለጉዳዩ የሚያውቁ ጠቅሰን መዘገባችን የሚታወስ ነው። ትህነግ የኤርትራን ደጋማ ክፍል አካሉ አድርጎ የሁለት ወደብ ባለቤት አገር ለመሆን እቅድ ይዞ ወይም ሁለት አገር ፍራሽ ላይ ” ታላቋን ትግራይ” ለመግንባት ውጥን እንዳለው በገሃድ ደጋፊዎቹን አንቂዎቹ በተደጋጋሚ የሚናገሩት ነው።

የኢትዮጵያን መንግስት ከታሉ በሁዋላ ኢሳያስን ለማውረድ ፊታቸውን ወደ ኤርትራ እንደሚያዞሩ አቶ ጌታቸውም ባገኙት አጋጣሚ ሲያስታውቁ እንደነበር ይታወሳል። ይህ ዜና እስከተጻፈ ድረስ ከትህነግ ዘንዳም ሆነ ከኤርትራ ወገን የተባለ ነገር የለም። ጦርነቱ ግን በተለያዩ አቅጣጫዎች መቀጠሉ በይፋ ተመልክቷል።


DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2657 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply