“እንደ ትህነግ ማሰብ ቀጣዩን ትግል ውጤታማ እንደሚያደርገው ጠ/ሚሩ ጠቆሙ “

እንደ ትህነግ ማሰብ ወይም ከዛ ብሶ ማሰብ የወቅቱ ጥያቄ መሆኑንን፣ በዚህ ዘርፍ ያልተቃኙ ጉዳዮች ተስተካክለው ቀጣዩ ትግል አቅጣጫ እንደሚይዘ፣ በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች መሳተፋቸውና የትህነግ ሃይል ከፍተኛ ቴክኖሎጂ በሚጠቀሙ አገሮች እንደሚደገፍ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አመለከቱ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ካቤኔ ሰብሰብው መመሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት ማብራሪያ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች‼

  • በጦርነቱ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ እና ኢትዮጵያዊ ዝርያ የሌላቸው ነጮች እና ጥቁሮች ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተሳትፈው መስዋዕትነት ከፍለዋል፤
  • ኢትዮጵያ የገጠመችው ጦርነት ከአንድ ወገን ጋር ብቻ እንዳልሆነ በመረዳት ህዝቡ ዋጋ በመክፈል ያለውን ፍቅር በተግባር ሊገልጽ ይገባል፤
  • ጦርነት ማለት የፖለቲካ ማስፈጸሚያ የመጨረሻው ጫፍ ነው፤
  • የትኛውም ሁኔታ ሊኖር ይችላል ጦርነቱን ግን ኢትዮጵያ እንደምታሸንፍ አትጠራጠሩ ፤
  • ሚኒስትሮች እና ሚኒስተር ዲኤታዎች መስራት ያለባቸው ጉዳዮች ከጦርነት ትርጉምና ሂደት ጋር የሚያያዝ መሆን አለበት፣
  • የበላይነት የገዢነት የአዛዥነት በሽታ የተጠናወተው ቡድን በምርጫ እንደማይሳካለት አይቶታል ፣ በዴሞክራሲ መንገድም አይቶታል፣ አሁን የመጨረሻ መንገድ የሚከፈለውን ዋጋ ከፍለን ማዘዝ መግባት ማፍረስ አለብን በሚል የገባበት መማገድ ነው፤
  • ይህ ቡድን ሌባ ነው፣ ታሪክ ይሰርቃል ፣ቅርሰ ይሰርቃል፤ የሌብነት ሂደቱ አዲስ አይደለም፣
  • የዛሬዋ ኢትዮጵያ ምንም ጦርነት ሳታደርግ ይህንን ኃይል ብትቀበለው የትላንቱን ህወሓት ሳይሆን የዘመነውን ለመሸከም ጫንቃዋ አይችልም ፣
  • የኢትዮጵያ ህዝብ ባርነትን አልቀበልም ማለቱ መልካም ነው፣
  • በወሎ ግምባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያዊያን ያልሆኑ ኃይሎች ተሳትፈውበታል፣ መስዋትነት ከፍለዋል፣ ነጮች ጥቁሮች በደሴ ውጊያ ሞተዋል፣
  • ኢትዮጵያዊ የሆነው ሰው ሀገሩን ለማዳን ምን ያህል ዝግጁ ነው፣

“በጦርነቱ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ እና የኢትዮጵያ ዝርያ የሌላቸው ነጮች እና ጥቁሮች ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተሳትፈው መስዋትነት ከፍለዋል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከየት አገር እንደሆኑ አላብራሩም። ግን የውጭ ፓስፖርት ያላቸው እንደሆኑ ግልጽ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ የገጠመችው ጦርነት ከአንድ ወገን ጋር ብቻ እንዳልሆነ በመረዳት አግባብ መሆኑን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ” ኢትዮጵያን የማፍረሱ ተነሳሽነትና ቃል ኪዳን እጅግ ከፍተኛ ነው” ብለዋል። ይህን መመከት የሚቻለው በዛው ደረጃ ቃል ኪዳን በመግባት እንደሆነ አመልክተዋል።

ከዚህ ቀደም አንድ አስተያየት ሰጪ ” እንደ ትህነግ ካላሰብን ማሸነፍ አንችልም። እኛ እንደ ሰው ማሰባችን ዋጋ እያስከፍለን ስለሆነ ከትህነግ ጋር በእነሱ ደረጃ ማሰብ መቻል አለብን” ሲሉ መደመጣቸው ይታወሳል። አስተያየቱ አሁን ላይ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ መሆኑም ታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ሲያብራሩ በጎርፍ የመጣውን ሃይል ለማስተናገድ በቂ ዝግጅት እንዳልነበር ጠቁመው ሶስት ዓመት ሙሉ ግን ሕዝቡ የጸጥታ ሃይሉን እንዲ

ቀደሞ ከነበረው በተለየ ሁኔታ እርምት ተወስዶ ስትራቴጂካዊ በሆነ መልኩ እየተሰራበት መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስር ዐቢይ ገልጸዋል፡፡አጠቃላይ ህዝቡ ለሠራዊቱ ያለው ድጋፍ አሁን ካለው በላይ ሊጠናከር ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ የገጠመችው ጦርነት ከአንድ ወገን ጋር ብቻ እንዳልሆነ በመረዳት ዋጋ ለመክፈል ያለውን ፍቅር በተግባር ሊገልጽ እንደሚገባ አሳስበዋል።


Leave a Reply