የሶማሌ ክልል – ያለፈውን ስቃይና ሰቆቃ አንረሳም፤አይረሳም

ህወሓት አገር ለማፍረስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማክሸፍ በትጋት እንሰራለን-የሶማሌ ክልል ብልጽግና ፓርቲ

የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኢንጂነር መሐመድ ሻሌ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በዛሬው ዕልት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል፡-

አሸባሪው ህውሓት ኢትዮጵያን እኔ እስካልመራዃት ድረስ መፍረስ አለባት የሚል ከንቱ ቅዠቱን እውን ለማድረግ ከህፃን እስከ ሽማግሌ በማሰለፍ ጦርነት ከፍቶ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ይገኛል።

ይህ አሸባሪ ቡድን ከአመት በፊት በመከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ካደረሰ ጊዜ ጀምሮ አጠቃላይ የሶማሌ ክልል ሕዝብና የክልሉ ፀጥታ ሀይል በጋራ በመሆን መከላከያን በመተካት በድንበር አካባቢ ያለውን የአልሸባብ ሰርጎ ገብ በአስተማማኝ ሁኔታ በመመከት አኩሪ ተግባር ሲፈፅም ቆይቷል።

አሁንም አሸባሪ ቡድኑ ከውስጥ ባንዳና ከውጪ ጠላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር አገር ለማፍረስና ለማተራመስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማክሸፍ በትጋት መስራታችንን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል።

በተጨማሪም አሸባሪው ህወሓት ለ27 አመታት በሶማሌ ክልል ዘርግቶት የነበረው የሞግዚት አስተዳደርና በሕዝቡ ላይ ሲያደርሰው የነበረው ስቃይና ሰቆቃ ዳግመኛ በሕዝባችን ላይ ለመጫን የሚያደርገውን መፍጨርጨር ሕዝባችን ከሌሎች ሰላም ወዳድ ሕዝቦች ጋር በአንድነት በመሰለፍ መመከቱን ይቀጥላል።

አሸባሪው ህወሓት በግንባር ከከፈተው ጦርነት በተጨማሪም በውጪና በውስጥ የሚገኙ አልሻባብን የመሰሉ አሸባሪ ሀይሎች በመጠቀም ክልሉን ለማበጣበጥ ያደረገው ሙከራ በሶማሌ ልዩ ሀይልና በክልሉ ሕዝብ የጋራ ጥረት ከንቱ ምኞቱ እንዲከሽፍ ማድረግ ተችሏል።

የሶማሌ ክልል የውስጥ ሰላሙን ጠብቆ የአገሪቱን ሰፊ ድንበር በመጠበቅ እስካሁን ሲያደርግ የነበረውን ተጋድሎ አሁንም አጠናክሮ መቀጠሉ እንደተጠበቀ ሆኖ አሸባሪው ቡድን በአማራ እና አፋር ክልል ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ወረራ ፣ ጭፍጨፋ ፣ ግድያ ፣ ማፈናቀልና የንብረት ዘረፋ ለማስወገድ ከክልሉ ሕዝብ ጎን የምንሰለፍ መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ።

በመጨረሻም መላው የክልላችን ሕዝብ በአሸባሪው ሀይል የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ሳይደናገር የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ ከዚህ በፊት እንዳደረገው ሁሉ ለመከላከያ ሰራዊት ያለውን የደጀንነት ሚና አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ጥቅምት 22 ቀን 2014 ዓ.ም

ጅግጅጋ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

FBC

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2650 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply