የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ – ሰርጎ ገቦችን ሕዝብ እየጠቆመ ነው

ልክ በደሴና ኮምቦልቻ እንደሆነው አስቀድመው ሰላማዊ በመምስለና በዓላማ ወዳጆቻቸው በመሸሸግ ወደ ከተሞች ያመሩ የትህነግ የሰራዊት አባላት መኖራቸው እንደታወቀ ተገልጿል። የአገር ደህንነትና ፖሊስ እነዚህ አካላት ላይም ሆነ በተመሳሳይ ከእነዚህ አካላት ጋር በድጋፍ በሚሰሩ ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ አመልክተዋል። ሕዝብም ዙሪያውን እየተከታተለ በመጠቆም ላይ ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ አስቸኳይ አዋጅ ታውጇል።

የትህነግ ሃይል ወደ መቀለ ከመለሱ በፊት አስቀድሞ ሃይሉ በሲቪል መልክ ወደ ከተማ ገብቶ በየመኖሪያ ቤቱ መመሪያ ይጠብቅ እንደነበር ያስታወቁ እንዳሉት አሁንም በጥቂት ሃይል እዛና እዚህ ብጥብጥ ፈጥሮ አዲስ አበባና ተመሳሳይ ከተሞችን ለመቆጣጠር ሃይል ማሰማራቱ ታውቋል። በደሴና ኮምቦልቻ የሆነው በገሃድ ከተገለጸ ወዲህ ሕዝብ ቁጣው እያየለ በመሄዱ ወደ ሌላ ግጭት እንዳያመራ መንግስት አስቸኳይ አዋጅ ማወጁ ደግ መሆኑንን ያመለከቱ አሉ።

ከመላው አማራ ሰፊ ቁጥር ያለው ሃይል ወደ ግንባር በየአቅጣጫው መዝመቱ፣ ተጨማሪ ሃይልም ለመዝመት ትራንስፖርት እየተጠባበቀ መሆኑ፣ ትህነግ በገባባቸው ቦታዎች አማሮችን እየመረጠ መጭፍጨፉ ተዳምሮ ቀጣዩን ትግል ” የመኖርና ያለመኖር” እንዳደርገው በመራር ቋንቋ እየተገለጸ መሆኑ ቀጣዩን ጦርነት ከቀደሙት ጊዚያቶች ሁሉ የመረረ እንዳያደርገው የፈሩም አሉ። ” ከለኩ አያልፍም፣ ያለቀው አልቆ ነጻነት” በሚል ፍርሃት ሳይሆን እልህ የሚያንበለብላቸው ” አሁን ፉከራ የለም” ሲሉ እየተደመጡ ነው።

ከአጎዋ ከዛሬ ነገ አግዳለሁ ስትል የቆየችው አሜሪካ በኮምቦልቻ ክ120 በላይ ንጹህ ዜጎች መረሸናቸውን በወጉ ሳይቃወም መላው አማራና ክልሎች ” ኢትዮጵያ ወይም ሞት፣ ትህነግን ዳግም መሸከም አንችልም” በሚል አቋማቸውን በመግለጽ ” ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር” ማለታቸው ሲታወቅ አሜሪካ ” ከአጎዋ ታግዳችኋል” ማለቷ ድራማውን በግልጽ ያሳየ ሆኗል።

ፌልትስ አማን የሚባሉት የምስራቅ አፍሪቃ ፊት አውራሪ ትህነግ ወደ አዲስ አበባ የሚያደርገውን ጉዞ እንደሚቃወሙ፣ ተቀባይነትም እንደሌለው አውስተው በነካ አፋቸው ኢትዮጵያዊያን የመረጡትን መንግስት ” ስልጣን ልቀቅ” የሚል ዓይነት መግለጫ ሰጥተዋል። ስትጠቃ ዝምታ፣ ስታጠቃ ወይም ለማጥቃት ጥርሷን ስትስል ማነቆ የሚጠብቅባት ኢትዮጵያ ዛሬ ልጆቿ በማምረራቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ለማሰብ ከባድ ሆኗል። በዚህ ሁሉ ችግር የተከበበው መንግስት ዛሬ አዋጅ አውጇል። ክተቱም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በመላ ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ምን ማድረግ ይችላል ?

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የሃገርን ህልውና እና ሉዐላዊነት፣ እንዲሁም የሰላማዊ ዜጎችን ደህነንት ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን ፦

 • በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል መከላከያ ኃይልን ወይም የትኛውንም ሌላ የጸጥታ አካል በማሰማራት ሰላምና ፀጥታ እንዲያስክብሩ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
 • እድሜያቸው ለወታደራዊ አገልግሎት የደረሱ እና የጦር መሳርያ የታጠቁ ዜጎች ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱ፣ ወታደራዊ ግዳጅ እንዲቀበሉ፣ ወይም ይህን ማድረግ የማይችሉ ሲሆን በአማራጭ ትጥቃቸውን ለመንግስት እንዲያስረክቡ ሊያዝ ይችላል።
 • የሰዓት ዕላፊ ገደብ ሊወሰን ይችላል።
 • ማናቸውም የህዝብ የመገናኛ እና የህዝብ መጓጓዥ ዘዴ እንዲዘጋ ወይም እንዲቋረጥ ሊያዝ ይችላል።
 • ከሽብር ቡድኖች ጋር ይተባበራል ብሎ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ የተጠረጠረ ማንኛውንም ሰው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ሥር ለማድረግ፣ ይህ አዋጅ ተፈፃሚ ሆኖ ባለበት ጊዜ ድረስ ይዞ ለማቆየት ወይም በመደበኛ ሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ይችላል።
 • ከሽብር ቡድኖች ጋር ይተባበራል ብሎ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ የተጠረጠረ ማንኛውንም ሰው ወይም ድርጅት ንብረት የሆነን ማኛውንም ቤት፣ ህንፃ፣ ቦታ፣ መጓጓዣ ለመበርበርና እንዲሁም ማንኛውንም ሰው ለማስቆም ማንነቱን ለመጠየቅ፣ ለመፈተሽ ይችላል፤ በብርበራ ወይም በፍተሻ የተያዙ የጦር መሳሪያዎችን መውረስ ይችላል።
 • ለተወሰነ ጊዜ መንገዶችን፣ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለመዝጋት እንዲሁም ሰዎች ለጊዜው በተወሰነ ቦታ እንዲቆዩ፣ ወደ ተወሰነ አካባቢ እንዳይገቡ ወይም ከተወሰነ ቦታ እንዲለቀቁ ለማዘዝ ይችላል።
 • ከፍተኛ የፀጥት ችግር እና ስጋት በተፈጠረባቸው የሃገሪቱ ክፍሎች የአካባቢ አመራር መዋቅርን በከፊልም ሆነ በሙሉ፣ ማገድ፣ መለወጥ እና በሲቪልም ሆነ በወታደራዊ አመራር መተካት ይችላል።
 • በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የሞራልም ሆነ የቁስ ድጋፍ ያደርጋል ብሎ የሚጠረጥረውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት እንቅስቃሴ በሚመለከተው ባለስልጣን በኩል እንዲታገድ ወይም ፍቃዱ እንዲሰረዝ ሊያዝ ይችላል።
 • በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የሞራል ድጋፍ ያደርጋል ብሎ የሚያምነውን የመገናኛ ብዙሃንን ወይም ጋዜጠኛ በሚመለከተው ባለስልጣን በኩል እንዲታገድ ወይም ፍቃዱ እንዲሰረዝ ሊያዝ ይችላል።

የተከለከሉ ተግባራት እና ግዴታዎች ፦

 • ሁሉም ሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በአዋጁ መሰረት የሚያወጣቸውን መመሪያዎችና የሚሰጣቸውን ትዕዛዞች የመቀበል ግዴታ አለበት።
 • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙን እንቅስቃሴ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ዓላማ የሚቃረን፣ የሚቃወም እና ለሽብር ቡድኖች ዓላማ መሳካት አስተዋፅዖ የሚያደርግ፣ የሽብር ቡድኖችን የሚያበረታታ፣ ሰላማዊ ዜጎችን የሚያሸብር ንግግር በማንኛውም መንገድ ማድረግ ወይም ማሰራጨት የተከለከለ ነው።
 • በየትኛውም መንገድ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የገንዘብ፣ የመረጃ፣ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ማድረግ የተከለከለ ነው።
 • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙ በተዋረድ ውክልና ከሰጣቸው አካላት ፈቃድ ውጭ ማንኛውንም የአደባባይ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የተከለከለ ነው።
 • ከመከላከያ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ወይም ሌሎች ፈቃድ ከሚሰጣቸው የፀጥታ አካላት ወይም ከነዚህ አካላት እውቅናና ፈቃድ ውጭ ማናቸውንም የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።
 • በከተሞች አካባቢ የነዋሪ መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የሰራተኛ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም ከነዚህ ተመጣጣኝ የሆነ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።
 • ማንኛውም ወሳኝ በሆነ የአገልግሎት ዘርፍም ሆነ በምርት ሂደት ላይ የስራ ማስተጓጎል ወይም የኢኮኖሚ አሻጥር መፈፀም የተከለከለ ነው።
 • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ሰበብ በማድረግ የግል ጥቅም ለማግኘት ስልጣንን አላግባብ መጠቀም፣ ምክንያታዊ የሆነ ጥርጣሬ ሳይኖር ሆን ብሎ ዜጎችን ማሰር ወይም መሰል እርምጃ መውሰድ የተከለከለ ነው።

Leave a Reply