ምንም ይሁን ምን ኢትዮጵያ በክህደት የታረዱ ልጆቿን አስባለች – አይረሳም!

የዛሬ ዓመት በትዕቢት ” አመድ አደረግናቸው” ሲሉ የተዛበቱ የሉም። ልክ የዛሬ ዓመት የአገር ክብር መሶሶ የሆነው መከላከያ ሰራዊታችን ለሁለት አስርት ዓመታት ከተኛበት ምሽግ ውስጥ እንዲታረድ ካዘዙት ውስጥ ይበልጦቹ አፈር ሆነዋል። የተቀሩትም ” የሞተው ሞቶ” በሚል የህዝብ ማዕበል አጉርፈው መንግስት እንደፈረሰ፣ አገር እንዳበቃላት እያወጁ ባለበት ወቅት ኢትዮጵያ ልጆቿን ” ነብስ ይማር ስትል” አክብራ አስባቸዋለች። አገር በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም ኢትዮጵያ ልጆቿን አልረሳችም። አትረሳም። ልትረሳም አይቻላትም። እስከወዲያኛው ይህ ታሪክ ይኖራል።

ክህደትና ውንብድና የተጣባው የትህነግ ሃይል የአገር መከላከያን በአርባ አምስት ሰዓት ከጥቅም ውጭ አድርጎ መሳሪያውን በሙሉ መረከቡን የተናገረበትና ይህንን የክህደት ጭፍጨፋ ሰብረው የወጡ አናብስቶች በአስራ አምስት ቀን እሳት እየተፉ የፈጸሙት ገድል በክህደት ከተፈጸመባቸው ግፍ ይበልጥ የሚያበራ ነውና ኢትዮጵያ አታዝንም። ግን በክብር ትዘክራቸዋለች። ሕዝብ ሁሉም ዜጋ ” አንረሳም” ብሏል። አይረሳም።

የክህደት ጭፍጨፋው ብቻ ሳይሆን፣ እድሜውን ሙሉ ሲጥበቃቸው ሲያገለግላቸውና እንደ ቤተሰብ ሲታዘዛቸው የነበረው መከላከያ ሲጨፈጨፍ የጨፈሩና እስክስታ የወረዱ ሁሉ ቀሪው ትውልድ ያስባቸዋል።መጪው ትውልድም ታሪካቸውን ሲማርበት ይኖራል።

ዛሬ ኢትዮጵያ በከሃጂዎች የዥዋዥዌ ጨዋታ ስቃይ ውስጥ ብትሆንም ቅን ፈራጅ አምላክ ብይን እንደሚሰጣት፣ የንጹሃን ደምና ነፍስ አምላክ ደጅ ጩኸት እንደሚሰማ፣ ሲሰማም እንደ መብረቅ የሚሆን ዋጋ እንደሚያስከፍል፣ ፍርዱ ሲደርስ እንጂ ለጊዜው ለተዘጋ ልብና አዕምሮ የአምላክ ፍርድ ልክን እንደ ተረት እንደሚመስል የታወቀ ነው።

መላው ኢትዮጵያ ሳያታሰር፣ ሳይገፋ፣ ሳይነዳ፣ ማስፈራሪያ ሳይደርስበት አምርሮ ወደ ግንባር እየተመመ ያለበትና ቁርጠኛነቱን ያሳየበት ቀን መሆኑም ” አንረሳችሁም ጀግኖቻችን” በሚል የተሰየወምውን የክህደት ቀን ልዩ ያደርገዋል። ኢትዮጵያን ለማፍረስ ብዙ ርቀት የተጓዙ ከሃጂዎች ይቅናቹህ!! አገር በማፍረስ ምን እንደምትጠቀሙ ወደፊት ልጅ ልጆቻቹህ ያስረዱናል። እናንተ ለማስረዳት ካልደረሰችሁ!! ሁሉንም እድሜ የሰጠው ያየዋል።

“የኢትዮጵያ አምላክ እንደ ወትሮው ከእኛ ጋር ነበር ” ዐቢይ አህመድ ወደ ቢሮ መመለሳቸውን ገለጹ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የመጀመሪያውን ምእራፍ ዘመቻ አጠናቀው ወደ ቢሮ መመለሳቸውን ገለጹ …
ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ በወራሪው ቡድን የተፈጸሙ ወንጀሎችን አይቶ እንዳላየ ሆኗል፤
መንግስት ከወራሪው ቡድን ነጻ በወጡ አካባቢዎች ለሚገኙ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ እያቀረበ መሆኑ …
የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ለ1 ሚሊየን ወደ አገር ቤት” ዘመቻ ተሳታፊዎች የ30 በመቶ የዋጋ ቅናሽ አደረገ፤ ቅድመ ዝግጅቱ ቀጥሏል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ለ1 ሚሊየን ወደ አገር ቤት” ዘመቻ ለሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን እና …
ሽፍታው ወራሪ ኮምቦልቻን አጠባት፤ ከነጻ መውጣት ብሁዋላ ምን?
" ኢትዮጵያ አትደፈርም ያልነው እናንተን ተማምነን ነው። ይህ ባንዲራችን በሌቦችና በሽፍቶች አይደፍረም። …
ትህነግ ላይ ማዕቀብ አንዲጣል ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥያቄ ቀረበ
አሸባሪው ትህነግ በፈጸመውና እየፈጸመ ለሚገኘው ከባድ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ማዕቀብ እንዲጣልበት ለአሜሪካ የውጭ …
ከውጭ ወደ አገር ቤት ቶሎ ቶሎ የሚመላለሱ አልባሳትና ጫማ ጨምሮ ገደብ የሚጥል መመሪያ ማብራሪያ ቀረበበት
የዚህ ክልከላ ምክንያትም ለንግድ የማይዉሉ የግል መገልገያ ዕቃዎችን ዝርዝር ለመወሰን የወጣዉን መመሪያ …

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2661 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply