በከሚሴ ትህነግ እየዘረፈ ነው፤ የኦሮሞ ታጣቂ የት ነው?

አቶ ጌታቸው ረዳ በውላቸው መሰረት ከኦነግ ሸኔ ሃይል ጋር መገናነታቸውን አመልክተዋል። እሳቸው ቦታውን ባይገልጹም የት ሊገናኙ እንደሚችል አስቀድሞ የሚታወቅ ስለነበር ቦታውን ለመረዳት አስቸጋሪ አልነበረም። በዚሁ መሰረት በአማራ ክልል ልዩ ዞን ከሚሴ የትህነግ ወራሪ ሃይል ዝርፊያ ላይ እንደሆነና ሕዝቡ ” ኦሮሞ ኦእሮሞን ቆሞ አዘረፈ” በሚል ቅሬታ ማሰምቱን በምስክር አረጋግጠናል።

ከሶስተኛ ወገን ማረጋገጫ አልተሰጠም እንጂ በርካታ የኦሮሞ ልጆች “ኦሮሞ ብልጽግና ናቹህ” ተብለው መገደላቸው ተሰምቷል። በዚህም ሳቢያ ሕዝቡ አምርሮ ተቃውሞ እያሰማ ነው። በመገናኛ ችግር ምስል ማሰራጨት አልተቻለም እንጂ በርካታ ክፉ ተገባራት መፈጸሙ ተሰምቷል።

በደሴ ” እንደገና ” በሚል መርህ የተደራጁ የወሎና አካባቢው ፋኖዎች ከከሚሴ አካባቢ ካለ መዋቅር ጋር ሆነው በመከላከያ ኦፕሬሽን ወደ ከሚሴ ለማጥቃት መነሳታቸው ታውቋል። የኦሮሚያ ልዩ ሃይልና መከላከያም የጥምር ማጥራት ዘመቻ ለማከሄድ ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተነግሯል።

በወሎ ግንባር የጦር ሜዳ ሚዛኑ እየተስተካከለና በግሸና ግንባር እስከ ወልደያ የተዘረጋ ዘመቻ ተከፍቶ ሁሉንም መስመር በሚባል ደረጃ የመንግስት ወታደሮች በመቆጣጠራቸው ዝርፊያ መጧጧፉን ያመለከቱ ወገኖች አየር ሃይል እየጠበቀ ተሽከረካሪዎችን እንደተጫኑ ማውደሙ ሌላ ስጋት ሆኗል።

ከአርባ ሺህ በላይ እስረኛ፣ በርካታ የተሰደዱ፣ እጅግ ብዙ ወገኖች የተገደሉበት፣ የተገረፉበትና የታፈኑበት የኦሮሞ ብሄረሰብ ከትህነግ ጋር አብሮ ኦሮሞን ዳግም ለማዘረፍና ለማስገደል አብሮ መስራቱ እጅግ አሳዛኝና በርካታ ኦሮሞ የሆኑትን በስፋት እያነጋገረ ነው።

Leave a Reply