የሰብዓዊ መብት ኮሚሽኖቹ ሪፖርት በኢትዮጵያ ጠንካራ ተቋማት እየተገነቡ የመሆናቸው ማሳያ ነው – ምሁራን

የኢትዮጵያ እና ተመድ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽኖች በጋራ ያወጡት ሪፖርት የኢትዮጵያን እውነት አለም እንዲረዳው ከማድረግ ባሻገር በኢትዮጵያ ጠንካራ ተቋማት እየተገነቡ የመሆናቸው ማሳያ መሆኑን ምሁራን ገለጹ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ ዶክተር ንጉስ በላይ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በቆይታቸውም ÷ ህወሓት ሀገር ሲመራ እንደዛሬው ከኢትዮጵያ ፖለቲካ መገለሉ እንደማይቀር ቀድሞ ስለገመተ በተለያዩ ተቋማት የሰገሰጋቸው አባላቱ የሚያስጮሁለት ተራ የውሸት ወሬ እንደነበር ዛሬ አለም ተመልክቷል ብለዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ በቃሉ አጭሶ በበኩላቸው ÷ በኢትዮጵያ የተፈጠረውን የህግ ማስከበር ተከትሎ ተፈጥሯል የተባሉ ችግሮችን ለማጣራት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከተመድ ጋር በመተባበር ያደረጉት ጥናት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ማግኘት እየተገነቡ ያሉ ተቋማት ውጤታማ እንደሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

“ሪፖርቱ ከሀገሩ አልፎ በተለያዩ ሀገራት የተፈጠሩ ግጭቶችን ለማርገብ በሚሰራው ተመስጋኙ መከላከያ ሰራዊታችንን የኖረ ስነ-ምግባር ባጎደፈ መልኩ ሲቀርቡ የነበሩ ክሶችንም ያፋለሰ ነው” ብለዋል።

በአፈወርቅ አለሙ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

FBC

Leave a Reply