የሁለት ከበባዎች ወግ ! መንግስትም ትህነግም ተከበዋል!!

መንግስትም ትህነግም ተከበዋል። ነገሩ የሁለት ከበባ ወግ ሆኗል። ደጋፊዎች በየፊናቸው ይጮሃሉ። ሆን ብለው ሽብር የሚረጩ አስበውና በተዋረድ የሚነገራቸውን እያደረጉ ነው። ሁኔታውን የሚከታተሉ እንደሚሉት ግን መንግስት በውጭ ሃይሎችና በሚዲያ ዘመቻ ተቀስፏል። ሚዲያውን ለማመጣጠን የሚሰሩ ታግደዋል። አራት ኪሎን በሚያዩት መሪዎቹ መመሪያ ያለ አቅሙ የተለጠጠው የትህነግ ሰራዊትም በሁሉም አቅጣጫ እሳት ጎርሶ በሚተመው ሃይል ተቀስፏል። የአገር መከላከያ ሰራዊት ቀሪ የትህነግ አመራሮችን ለመያዝ ገደል ለገደል ሲባዝን እንደሆነው የትህነግ ሰራዊት ከደጀኑ ርቋል። ለመሸሽም በሚያመች አቋም ላይ አይደለም። “ጥያቄው ማን ቀድሞ ይተነፍሳል? ነው። የውጩ ጫናና የሚዲያው ሽብር ያነቀው መንግስት ይተንፍሳል? ወይስ “ኢትዮጵያ” ብሎ የተመመውና እሳት ጎርሶ ግንባር ላይ እየቀናው እንደሆነ የሚነገርለት መከላከያ ያተነፍሳል?
ከበባውን የሚያሳየው ካርታ – በርካታ ቦታዎች መለቀቃቸው ቢነገርም መንግስት ማረጋገጫ ባለመስተቱ አልታተመም

ኢትዮጵያ በክተት ዘመቻ ስራ በዝቶባታል። በወሎ ግንባር ብቻ ሳይሆን ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰሙ የጦርነቱ መልክና የዛሬ ማለዳው የአቶ ጌታቸው ረዳ “ኮምቦልቻንና ደሴን ለስልት ሲባል ለቀናል ወይም ልንለቅ ነው” የሚል ቲዊት ከፌልትስማን የአዲስ አበባ መገኘት ጋር ተያይዞ ወቅታዊውን ጉዳይ አጡዞታል።

“ከሰሜንና ደቡብ ጎንደር ከተት ያለው ሃይልብዛቱ ሳይሆን እልሁ ያስፈራል። በዚህ ነበልባል ስሜት ትህነግ ቀደም ሲል ለወረራ የገባበትን መስመር ተከትሎ ወደ ግንባር እየበረረ ነው። ግንባር ደርሶም ስራውን የጀመረ አለ” ሲሉ ለጊዜው ስም ሳይጠቅሱ የድል ዜና ስለመኖሩ የሚናገሩ አሉ።

ድፍን ሸዋ ወደ ከሚሴ ጎራ ” ሳይቃጠል” ብሎ እየተመመ መሆኑ በዜናና በምስል ይፋ ሆኗል። ከሁሉም አቅጣጫ የሚሰማው ክተቱ ተጀመረ እንጂ ገና በሚፈለገው ደረጃ ሊደርስ ቀርቶ አልተጋመሰም። መኪና አንሶ በእግር ጉዞ የጀመሩ እንዳሉ ጉዞእ የጀመሩት ሲናገሩ ተሰምተዋል። “ሊያፈናቅል የሚመጣውን ሳይመጣ አለበት ድረስ” በሚል መኪና ሳይጠብቁ በእግር ወደ ግንባር ጉዞ መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

የቀድሞ ሰራዊት ባለሙያዎች ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ጥሪ ተደርጎላቸዋል። በወሎ ” እንደገና” የሚባለውን አዲስ ንቅናቄ ጨምሮ ፋኖ በልዩ አደረጃጀት ማጥቃት መጀመራቸውን እያስታወቁ ነው። ምርኮ ማሳየት ጀምረዋል። ወደፊት እንደሚዘረጉም አመክተዋል።

የአብኑ ዩሱፍ ኢብራሂም በቲውተር ገጹ እንዳለው ” በቅርቡ ( በቀናት የድል በድል ዜና ላይ በላይ እንደሚሰማ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነኝ” ሲል አትሟል። እንዲህ ያለው መረጃና በመከላከያ የሚመራው የማጥቃት እርምጃ መቀጠሉ እየተነገረ ባለበት ወቅት አቶ ጌታቸው አትመው ወዲያው ያጠፉት መረጃ በሁሉም ወገን መነጋገሪያ ሆኗል።

አቶ ጌታቸው ዛሬ ከኮምቦልቻና ደሴ ለስልት ሲባል እንዲልቅ ወይም እንዲያፈገፍግ መወሰኑንን፣ ሲፈልጉ ደግሞ እንደሚቆጣጠሩት ማለዳ ላይ በቲውተር ገጻቸው አስፍረው ነበር። ከትንሽ ቆይታ በሁዋላ ወዲያው አንስተውት እንደ ማስተባበያ አይነት ” በግንባር የተሸነፉ” ሲሉ አዲስ ምትክ ሃሳብ አትመዋል።

ሲኤን ኤን በበኩሉ በርካታ ያልተመጣተኑ ዜናዎችን የሚያትም ቢሆንም ዛሬ የትህነግ ሃይሎች ከአዲስ አበባ ውጭ እንደሚገኙ በግልጽ የማይታይ ፎቶ አስደግፎ ዜና አሰራጭቷል። ሚዲያው ይህን ሲያሰራጭ አዲስ አበባ ዙሪያ ጭምሮ በመላው ኦሮሚያ ስፍር ቁጥር የሌውለውን የተቃውሞ ሰልፍ እንዳልሰማ ሆኖ አልፎታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ዳግም በትህነግ የመመራት ፍላጎት እንደሌለው አሜሪካ ጠንቅቃ እንደምታውቅ ያስታወቁት ፌልትስማን አዲስ አበባ በሚገኙበት ወቅት ሲኤን ኤን፣ ቢቢሲ አማርኛ፣ ቪኦኤና የጀርመን ድምጽ ራዲዮን እያሰራጩ ያሉት ዜና የተናበበና አንድ ዓላማ ያነገበ ስለመሆኑ በየአቅጣጫው እየተነገረ ነው

ይህ እየሆነ ነው ትህነግ ለታክቲክ ብሎ የሚለቀው ከተማ እንደሌል የተገለጸው። ጌታቸው ረዳ ደሴና ኮምቦልቻ ኬሚሴን ለቀን ልንወጣ እንችላለን ብለው ከተለጠፉ ቡሁዋላ መልሰው አንስተውታል። ይህ የሆነው በአፋር ግንባር እና በዳሸና በኩል በተከፈተው ማጥቃት የትህነግ ሃይል ጥቃት እንደደረሰበትና ከአቅሙ በላይ መለጠጡ ለኪሳራ እንደዳረገው፣ በርካታ ሃይል ወድ ግንባር ለመቀላቀል እየገሰገሰ መሆኑንን ከግምት በማስገባትና ቆቦ በመከላከያ እጅ ገብታ የግንኙነት መስመር በመቆረጡ እንደሆነ ስለ ሁኔታው የሚያውቁ እየገለጹ ነው።

ትህነግ አዲስ አበባ እንዲገባ ያለ የሌለ ሃይላቸውን እየተጠቀሙ ያሉት አገራትና ሚዲያዎች ሕዝብን በሚያስጨንቁና መንግስትን በሚያዝሉ፣ ሰራዊቱን ተስፋ ለማስቆረጥ እየሰሩ ቢሆንም የክተት አዋጁ በማንኛውም መልኩ በመደለያ፣ በቅስቀሳና በማሸበር ሊገታ የማይችል የሕዝብ ማዕበል በመሆኑ የጸጥታ ሃይሉን ለማፍረስ የተሞከረውንና እየተሞከረ ያለውን ጥረት እንዳመከነው የሚናገሩ፣ ዛሬ ጊዜው የመጨረሻ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ወደሁዋላ አለመኖሩን ነው። “ትህነግ ትግራይ ድረስ መጥተው ወረሩኝ” በሚል ለሚከሰሰበት ወረራው ምክንያት እንዳቀረበው ሁሉ አሁንም የአማራ ሕዝብ ቀዬው ድረስ ዘልቀው በገቡ ወራሪዎች ክፉኛ በመጎዳቱ፣ በመሰቃየቱና የመኖር ህልውናው ያከተመ በመሆኑ አሁን የገባበትን ጦርነት በድል ከማጠናቀቅ ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለ መተማመን ላይ ደርሷል። ሌሎች ክልሎችም “ዳግም ለባርነት አንፈቅድም” በሚል አቋማቸውን ይፋ አድርገዋል።

This image has an empty alt attribute; its file name is image-4.png

“የኢትዮጵያ የድንበር ላይ አጥር” የሚባለው የአፋር ክልል ሕዝብ በሙሉ ያለውን ይዞ አገሩን እንዲከላከል በተላለፍለት ጥሪ መሰረት በጥምር ከመከላከያ ጋር ማጥቃት መስነዘሩና የታሰበው እንዳይሆን ማድረጉን ዶክተር ኮንቴና በርካታ የአፋር የአደረጃጀት ሃላፊዎች እየተናገሩ ነው። መሬት ላይ አለ የሚባለው ሃቅ ይህ ቢሆንም እነ ቢቢሲን ጨምሮ አዲስ አበባ ያሉ መገናኛዎች የሚዘግቡት ትህነግ እየገፋ መሆኑን የሚያጠናክሩ የጅ አዙር ዜናዎች መሆናቸውን እውነቱን የሚያውቁ እየተናገሩ ነው።

ሲ ኤን ኤን ላይ ያላገጠው ታዋቂው የምርመራ ጋዜጠኛ ዳኔል ሉታያ በቲውት ገጹ ወደ አዲስ አበባ ከመብረሩ በፊት የሲ ኤን ኤን እና ሌሎች ሚዲያዎችን መመልከቱንና ማዳመጡን አመልክቶ፣ ” ወደ ጦርነት ቀጣና የምጓዝ ነበር የመሰለኝ” ብሏል። አያይዞም ትናንት አዲስ አበባ፣ ዛሬ አዳማ መሆኑንን ጠቁሞ፣ ” ጥይት የለም፣ የተዘጋ መንገድ የለም። ውጥረት የለም። ምን ነገር የለም” ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል። ምስክርነቱን ሲያጸና ” ከአዲስ አበባ ይልቅ በካምፓላ በርካታ ወታደሮች አሉ” ብሏል። ይህን ምስክርነት ለህሊናቸው ቅርብ የሆኑ የአሜሪካ ባለስልጣናትና የተቋም አመራሮች በአገራቸው ሚዲያ ማፈራቸውን በሸውራራ በመግለጽ አጋርተውታል።

የውጭ ሚዲያዎችና አዲስ አበባ ያሉት ትዮጵያዊያን ተቀጣሪዎቻቸው ጨምሮ ሚዛን ስተው እየለበለቧት ያለችው ኢትዮጵያ ክተት የሄደው ሃይል፣ ልዩ ሃይልና ሚሊሻው አንድ ሆኖ ከበባውን እያጠበበ መሆኑ ታውቋል። በካርታው እንደሚታየው ከአፋር፣ ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል አቅጣጫ የትህነግ ሃይል እየተጠቃ ቀለበቱ እየጠበበት መሆኑ ስጋት ፈጥሯል። አቶ የሱፍ ኢብራሂም በቲውተር ገጻቸው እንዳሉት ታላላቅ ዜናዎች በደጅ ናቸው።

ሁኔታውን የሚከታተሉ እንደሚሉት መንግስት በውጭ ሃይሎችና በሚዲያ ዘመቻ ተቀስፏል። ሚዲያውን ለማመጣጠን የሚሰሩ ታግደዋል። አራት ኪሎን በሚያዩት መሪዎቹ መመሪያ ያለ አቅሙ የተለጠጠው የትህነግ ሰራዊትም በሁሉም አቅጣጫ እሳት ጎርሶ በሚተመው ሃይል ተቀስፏል። የአገር መከላከያ ሰራዊት ቀሪ የትህነግ አመራሮችን ለመያዝ ገደል ለገደል ሲባዝን እንደሆነው የትህነግ ሰራዊት ከደጀኑ ርቋል። ለመሸሽም በሚያመች አቋም ላይ አይደለም። “ጥያቄው ማን ቀድሞ ይተነፍሳል? ነው። የውጩ ጫናና የሚዲያው ሽብር ያነቀው መንግስት የተንፍሳል? ወይስ ኢትዮጵያ ብሎ የተመመውና እሳት ጎርሶ ግንባር ላይ እየቀናው እንደሆነ የሚነገርለት መከላከያ ያተነፍሳል?

“የአማራና የአፋር ህዝብ እንደ ህዝብ የህወሓትን መመላለሻ መንገዶች እየዘጉ በጣምራ እያጠቁ ነው። መከላከያ ስራዊቱ አሉ የሚባሉ ማዕከላዊ ቦታዎች ይዞ እንዳይመለሱ አድርጎ ማሰናበት ጀምሯል። አየር ሃይል ሽፋን እየሰተ የተመረጡ ቦታዎችን ያጠቃል” ያሉ ሃላፊዎች አድረው ምን እንደሚሉ ይጠበቃል።

አቶ ጌታቸው ወዲያው ያነሱት የቲውተር መግለጫቸው

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2656 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply