በከተማ አስተዳደሩ ከ10 ሺህ በላይ የጦር መሳሪያ ተመዝግቧል፤

በአዲስ አበባ ከተማ በነገው ዕለት አሸባሪዎቹን ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ ይካሄዳል

– በከተማ አስተዳደሩ ከ10 ሺህ በላይ የጦር መሳሪያ ተመዝግቧል፤

በአዲስ አበባ ከተማ በነገው ዕለት አሸባሪዎቹን ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ፣ የሀገር ህልውናና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚገኙት የአገር መከላከያ ስራዊትና ሌሎች የጸጥታ አካላትን ለመደገፍ ህዝባዊ ሰልፍ
እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሰታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የተመዘገበም ሆነ ያልተመዘገበ የጦር መሳሪያ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች መሳሪያቸውን እንዲያስመዘግቡ በቀረበው ጥሪ መሰረት ከ10 ሺህ በላይ የጦር መሳሪያ መመዝገብ ተገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ ዮናስ ዘውዴ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ” አባቶቻችን አልተንበረከኩም እኛም አንበረከክም”። ኢትዮጵያ በዘመናት መካክል የገጠማትን ፈተና በህዝቦቿ የተባበረ ክንድ አልፋልች። ከጥንት እስክ አሁን ይህንስ አልታልፈውም የተባለችውን ችግር እንደ ውቅያኖስ መርክብ በድል ያሸነፈች አገር ናት ብለዋል።

ባለፉት 27 አመታት በህዝብ ላይ ሰቆቃ ሲያደርስ የነበረውን ህወሃት የአሁኑ አሸባሪ ቡድን ግፍና በጋላቢዎቹ ምእራባውያን ጫና እየደረሰባት ያሉት አቶ ዮናስ፣ ሀገሪቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ በመገኘቷ ሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች መታወቂያ፣ ፓስፖርት ይዘው መንቀሳቀስ አለባቸው።

በከተማ አስተዳደሩ ከ10 ሺህ በላይ የጦር መሳሪያ ተመዝግቧል ያሉት ኃላፊው መላ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የመከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀርቧል።

በሞገስ ተስፋ- (ኢ ፕ ድ)

Leave a Reply