በሕዝባዊ ማዕበል ድል እየተመዘገበ ነው፤ ሲኤን ኤን በገሃድ ማጭበርበሩ ተጋለጠ 

መንግስት ቃል በቃል ባይናገርም የዋግ አካባቢዎች በሕዝብ ማዕበል ነጻ መውጣታቸውን ምስክሮች ቀርበው ሲናገሩ በምስል ታይተዋል። በአካባቢውም የተፈጸመው ዝርፊያና ውድመት በገሃድ እንዲታይ ተደርጓል። ሲ ኤን ኤን የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት አባላት በአዲስ አበባ ቅርብ ረቀት መዳረሳቸውን በምስል አስደግፎ ያሰራቸው ዜና ቅጥፈት መሆኑ ተረጋገጠ።

ሲኤን ኤን በሜይ 12 2021 በእነሱና በወታደሮች መካከል አለመግባባት እንደነበር ለማሳየት የተተቀመበትን ምስል የትህነግ ሃይሎች አዲስ አበባ ዙሪያ ደርሰዋል ለማለት የተጠቀመበት የሃሰት ዘገባ ቅጥፈት መሆኑንን ያሳየው ፎቶ በንፅር

በአማራ ክልል የዋግና አካባቢው ነዋሪዎች ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገናቸው ጋር በመሆን በአካባቢው የገባውን ጠላት እየደመሰሱ መሆናቸውን ማስታወቃቸውን የዘገበው የአማራ ቴሌቪዥን ዘገባውን ያሰራጨው እዛው እስፍራው ላይ ሆኖ ነው። “አሸባሪው ሕወሓት በዋግ ሕዝብ ላይ ያልፈጸመበት የበደል ዓይነት የለም” በሚል ነዋሪዎቹ በምሬትና በሃዘን ስሜት ፍርስራሽ እያሳዩ ተነግረዋል።

“የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት የሆነውን የሽብር ኃይል ዛሬም እንደትናንቱ በከፍተኛ ወኔ እየተፋለምን ወደፊት እየገፋን ነው” ሲሉ በግንባር ድል እየተገኘ መሆኑንን አመልክተዋል። የአበርገሌ፣ የፃግብጂ፣ የዳህና፣ የሳህላ ሰየምት፣ የዝቋላ፣ የሰቆጣ እና የጋዝጊብላ ወረዳ ነዋሪዎች በየአቅጣጫው እየተመመ ከሚገኘው ወገን ጋር በመሆን አሸባሪውን ኃይል እየቀጡት መሆናቸውንም አስታውቀዋል። የተጠቀሱት ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ነጻ እንደወጡና አሁን ላይ ስጋት እንደሌለባቸው አመልክተዋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የትህነግ ሃይል ከበባ ውስጥ እንደሆነ ቢገለጽም የትኛውም የመንግስት አካል በይፋ አላስታወቀም። ይሁን እንጂ እነዚህብ የዋግ አካባቢ ነዋሪዎች በቃለ ምልልሳቸው ወቅት “የአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ኃይል በአሁኑ ወቅት በከበባ ውስጥ ገብቷል፡፡ ምርጫው እጅ መስጠት ወይም ባለበት ማለቅ ነው” ሲሉ ተሰምተዋል።

“ወራሪው ትህነግ የመጨረሻ እስትንፋሱን ለመዝጋት በገባባቸው ቦታዎች ሁሉ ሕዝቡ በከፍተኛ ቁጣ ባገኘው መሳሪያ ሁሉ አንድም እንዳይተርፍ አድርጎ እየደመሰሰ ነው” በማለት ለአሚኮ ሲያስረዱ መስማት ትችሏል።

ሲኤን ኤን የትህነግ ሰራዊት አዲስ አበባ መዳረሻ ተቃርቦ መንግስት ለመገልበጥ ከጫፍ መድረሱን ዘግቧል። ሚዲያው መንግስትን በጄኖሳይድ፣ ረሃብን ለጦር መሳሪያ መጠቀምና በጅምላ ጭፍጨፋ በተደጋጋሚ ሲከስና ሲወነጅል ቢቆየም መንግስት ከዚህ ክስ ነጻ መሆኑ በጣምራ በተደረገ ምርመራ ተረጋግጧል።

ዛሬ ሲኤን ኤን የቀድሞ ምስል ከመዝገብ ቤት አውጥቶ የትህነግ ሃይል አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ቀርቧል ብሎ ዜና መስራቱ በቲውተር መሳቂያና መዛበቻ አድርጎታል። ይሁን እንጂ ይህ እስከተጻፈ ድረስ ይቅርታ አልጠየቀም።

See also  «…የሽብር ቡድኑ ወደደም ጠላም ወደ ሰላም አማራጭ እንዲመጣ ለማድረግ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳል» መንግስት

ሕዝብን የማሸበርና የማስጨነቅ ዓላማ ላነገበችው አሜሪካን ዋና መገለገያ የሆነው ሲ ኤን ኤን እንዳለው ሳይሆን ምስሉ ከላይ በመግለጫ እንደተገለጸው የቆየና አሁን ካለው ታሪክ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው መሆኑ ትረጋግጧል። መንግስትም በነጭ ወሬ የሚፈርስ አገር የለም ሲል አስታውቋል። መንግስት ” ነጭ ወሬ” ሲል “ሃሰተኛ” ለማለት ፈልጎ እንደሆነ አማርናው ግልጽ ቢሆንም፤ ለነጮች አጣመው በመተርጎም የትህነግ ቁልፍ ሰዎች ለሰዎቻቸው ባሰራጩት መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “ዘረና ጽሁፍ አሰራጭተዋል” በሚል ዘመቻ ከፍተውባቸዋል።

ይህበእንዲህ እንዳለ አዲስ አበባ ዙሪያ ደርሷል የተባለው የትህነግ ሃይል አዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮሚያ ከተሞች እጅግ ሰፊ ቁጥር ባለው የሰላማዊ ሰልፍ ” እንዳታስበው፣ የተረፈ መሬት የለንም” በሚል ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተቃውመውታል። ለውጭ አገር ሚዲያዎችና በውጭ አገር ለሚደገፉ ሚድያዎች ተቀጥረው የሚሰሩ “ኢትዮጵያዊያን ሪፖርተሮች” ሳይቀር ይህንን ሰልፍና በሰልፉ የተነሳውን ሃሳብ ሽፋን ለመስጠት ተቸግረው መታየታቸውን አስተያየት የሰጡ አመልክተዋል።

በሰለፉ ” እስኪ ማን እሺ ብሎ በግድ በትህነግ እንድንተዳደር የሚያድርግ ካለ እናያለን። እኛ መንግስት መርጠናል። ችግሩ ኦሮሞ ተቅላይ ሚኒስትር ከመሆኑ ጋር ከሆነ እንመክርበታለን” ሲሉ ተደምጠዋል። የራሳቸው ኮድና ሰንሰለት ዘርግተው አካባቢያቸውን እየተበቊ እንደሆነ አመልክተዋል።

Leave a Reply