“ከሚሰጣቸው ዳረጎት ውጪ ተስፋ የሌላቸው አገር ሻጮች”

ጌቶቻቸው እግር ስር ለዘመናት ወድቀው ከሚሰጣቸው ዳረጎት ውጪ ተስፋ የሌላቸው አገር ሻጮች ጌቶቻቸውን ለማስደሰት ዛሬም በድን ሆነው ከተቀበሩበት የዳረጎት ጉድጓድ ብቅ ብለው ታይተዋል።

ከጊዜያት በፊት ማዕከላዊ መንግስትን ከስልጣን ለማባረር እና የጡት አባታቸው አሸባሪው ህወሃትን ወደ ስልጣን ለመመለስ አእምሮአቸውን በጭሰኛ ፖለቲካ፣ የጡረታ ጊዜአቸውን ደግሞ በአሸባሪው ድጎማ ላይ ተስፋ ጥለው የነበሩ አከላት “የኢትዮጲያ ፌዴራሊስት እና ኮንፌደራሊስት ሀይሎች” በማለት ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ ነበር።

ከአሸባሪው ህወሃት ጋር የቆየ ጋብቻቸውን አዲስ ለማስመሰልና የተልእኮ መሪያቸውን ጌቶች ምኞት ለማሳካትም በመቀሌ ከትመው አገርን ለማፍረስ ዶልተው እንደነበር የምናስታውሰው ነው።

በምንዳ የተገነባ ምንዳው ሲያልቅ እንደሚፈርስ አሸባሪው ተመልሶ ወደ ስልጣን ሊመጣ ቀርቶ ወደ መቃብሩ መጓዙን ያመኑት የምንዳ ስብስቦቹ የመቀሌውን ድግስ ሸምጥጠው፣ ዳረጎታቸውን ታቅፈው በደረቅ አይነ ሌባ አመል አንገት ደፍተው ታይተዋል።

ለኢዮቤልዩና ከዛ በላይ የታሰበው የዳረጎት ጋብቻም የሰርጉ ድግስ ሳያልቅ፣ ትዳሩም ሳይጸና በጫጉላው ተፈቶ ተበትኗል።

ወቅትን እየጠበቁ ብቅ የሚሉት “የምንዳ ጠባቂዎቹ” ዳረጎታቸው እስኪቀዘቅዝና ጋሪያቸውን የሚመራው ጋላቢ እስኪያዛቸው ድርስ ድምጻቸውን አጥፍተውም ነበር የቆዩት።

ጌቶቻቸው በዋሉበት የሚውሉት፣ ሲናገሩ ድምጽ የሚሆኑት እነዚህ ባንዳዎች የጭቃ ሹማቸው አሸባሪው ህወሃት እየተቀበረ መሆኑን ሲረዱ ዳረጎታቸው እንዳይቋረጥና ጌቶቻቸውን በጥፋት ለማስደሰት ከምንዳ ዋሻቸው ዋሽንግተን ሳይጠሩ አቤት ብለዋል።

በሚዲያዎቻቸው፣ በጀርባ በሚዘውሯቸው አለም አቀፍ ተቋማትና ግለሰቦች በኩል የኢትዮጵያን እጅ መጠምዘዝ ያቃታቸው ቁማርተኞቹ ምዕራባውያን ጊዜው ያለፈበትን መጫወቻ ካርድ ይዘው ብቅ ብለዋል።

በነሱ ሃሳብና ፍላጎት የሚመራ መንግስት ካላዩ እንቅልፍ የማይወስዳቸውና ጥፋትን በመተግበር ህልማቸውን ለማሳካት ዋጋ የሚከፍሉት አሜሪካና ምዕራባውያን በድጎማ ብቻ ያቆዩአቸውን “የኢትዮጲያ ፌዴራሊስት እና ኮንፌዴራሊስት ሀይሎች” አሸባሪው ህወሃትን ከመለሱልኝ ብለው ከተወሸቁበት የዳረጎት ጉድጓድ ጠርተዋቸዋል።

ምንደኞቹም ዘጠኝ በመሆን የኢትዮጵያን መንግስት ሃይልን ጨምሮ በሁሉም መንገድ አስወግደን የቀድሞ አለቃችንን ወደ መንበረ ስልጣን እንመልሰዋለን፤ ጌቶቻችንን ደግሞ አሻንጉሊት በመሆን የልባቸውን እንሞላለን ሲሉ ቃል ገብተዋል።

ይህም ባለፉት አመታት በአገሪቱ ተከስተው ከነበሩ 113 በላይ ግጭቶች ጀርባ የነዚህ አካላት ስውር እጅና የጌቶቻቸው ትዕዛዝ ስለመኖሩ የረቀቀ ሳይንሳዊ ምርመራን ማካሄድ አይጠይቅም።

ኢትዮጵያ ከውጭ በሚመጣ ወራሪም ሆነ በራሷ ባንዳ ልጆች ጥቃት ተሸንፋ እንደማታውቅና እንደማትሸነፍ ፋሽስት ጣልያን ሕያው ምስክር ነው።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣
_ ወደ ግንባር ዝመት፣
_ መከላከያን ደግፍ።

Ena

Leave a Reply