‘ኦሮ-ፍሬሽ’ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለአዲስ አበባ ነዋሪዋች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ጀመረ

‘ኦሮ-ፍሬሽ’ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ አትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶችን ለአዲስ አበባ ነዋሪዋች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)‘ኦሮ-ፍሬሽ’ የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ አክስዮን ማህበር ዛሬ የተለያዪ አትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶችን ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ ማቅረብ ጀመረ።

አክሲዮን ማህበሩ አምራቹን ቀጥታ ከሸማቹ ጋር ለማገናኘት የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለአዲስ አበባ ገበያ እንደሚያቀርብ መግለጹ ይታወሳል።

በዛሬው እለትም የኦሮ ፍሬሽ የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ አክስዮን ማህበር በአዲስ አበባ ሳር ቤት የአትክልትና ፍራፍሬ ሽያጭ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እያካሄደ ይገኛል።

አላማው አምራቾች በቀላሉ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በቀጥታ ለሸማቹ ህብረተሰብ ለማድረስ ያለመ ነው።

ተቋሙ ምርቱን ለሸማቹ በቀጥታ በማቅረብ የገበያ ሰንሰለትን ማሳጠርና ገበያን የማረጋጋት ዓላማዎችን ይዟል።

የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን፣ መቂ ባቱ አትክልትና ፍራፍሬ ህብረት ስራ ዩኒየን እና ሌሎች ህብረት ስራ ማህበራት ተሳትፈዋል።

ገበያውም ቅዳሜ እና እሁድ በየአካባቢው የሚቀርብ ሲሆን ÷ ድንች፣ ሽንኩርት፣ ቡና፣ ቲማቲም፣ ሀባብ እና ሌሎች ምርቶች ናቸው ለግብይት የሚቀርቡት።

በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እና ሸማቾች መገኘታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

OBN

Leave a Reply