5 የውጭ መገናኛ ብዙኃን በ4 ቀናት ኢትዮጵያን የተመለከቱ 72 ሃሰተኛ ዜናዎች አሰራጭተዋል

ሲኤንኤን፣ አልጀዚራ፣ ቢቢሲ፣ አሶሼትድ ፕረስ እና ፍራንስ 24 የተሰኙ ዓለም ዐቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ባለፉት 4 ቀናት ብቻ ኢትዮጵያን የተመለከቱ 72 ሃሰተኛ ዜናዎች ማሰራጨታቸው ተገለፀ።

በቴክኖሎጂና ፈጠራዎች ላይ ትኩረት በሚያደርገው የኢቢኤስ ቴክቶክ መርሃ ግብሩ የሚታወቀው ሰለሞን ካሳ ዛሬም የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ በህይወት ስለመኖሩ አመላካች ነው ሲል በትዊተር ገፁ ባጋራው መረጃ በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን በሃሰት ወሬ ሕዝብ የማሸበር ሙከራ ለአብነት ጠቅሷል።

ሰለሞን ከቀናት በፊት ሲኤንኤን የቀድሞ ምስልን የአሁን አስመስሎ በመጠቀም ያሰራጨውን ሃሰተኛ ዘገባ በማስረጃ በማጋለጥ የመገናኛ ብዙኃኑን አገር የማፍረስ ድብቅ አጀንዳ ማሳየቱ ይታወሳል።

ከሰሞኑ የበረከተው የእነዚህ ሃሰተኛ ዘገባዎች ዋነኛ ዓላማ አዲስ አበባ በሽብር ቡድኖች እንደተከበበች በማስመሰል ሽብር መንዛት እና አለመረጋጋት በመፍጠር መንግሥትና ሕዝብ የተሸናፊነት ስሜት እንዲጫናቸው ማድረግ ነው።

በዚህም የሞት አፋፉ ላይ የሚገኘውን ሕወሓት የሽብር ቡድን በግርግር ወደ ድርድር እንዲመጣና ከመጥፋት እንዲተርፍ ማገዝ ነው።

ሆኖም ከሰሞኑ 30 ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያዊያን ባደረጓቸው የተቃውሞ ሰልፎች የተቀናጀውን የመገናኛ ብዙኃን ዘመቻ በመቃወም የሽብር ቡድኑን ለመደምሰስ ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

Via walta

See also  ፖለቲካ - የትህነግ ወኪሎች ስካይ ላይን ናቸው ፤ ጌታቸው ረዳ ወደ ኮሙኒከሽን ?

Leave a Reply