ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታና በዓለም አቀፉ የመገናኛ ብዙሃን የምትገለጸው ኢትዮጵያና በመሬት ላይ ያለው ተጨባጭ እውነታ እጅጉን የተለያዩ መሆናቸውን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የመጡ አሜሪካዊያን የአሜሪካ ዜጎች ተናገሩ፡፡

ከአሜሪካ ኦሃዮ ግዛት የመጡት ሬይ ማክልስ እንደገለጹት፣ በምዕራቡ ዓለም ሚዲያ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ የምትሰማውና ቦታው ላይ ተገኝተህ የምታየው ነገር መሬት ላይ ካለው እውነት ይልቅ የሚዲያው ውሸት ይገዝፋል ብለዋል።

እኔም ሆንኩ ጋደኞቼ ተዘዋውረን ባየናቸው አከባቢዎች ምንም የገጠመን ችግር የለም ያሉት ሬይ የምዕራቡ ሚዲያ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ግጭት እንዳለና ሀገሪቷ ያልተረጋጋች አድርገው የሚያሰራጩት ዘገባ ተገቢነት የለውም። ለምን እንደሚዘግቡም ግልጽ አይደለም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን ላለፉት 20 ዓመታት ለመጎብኘት የተመላለሱት ሌላው አሜሪካዊ ፖል አንደርሰን በበኩላቸው ዓለም አቀፍ ሚዲያ ስለኢትዮጵያ የሚያሰራጫቸው መረጃዎ ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል፡፡

ከአንድ ሬስቶራንት ቁጭ ብዬ የሲኤንኤን ዘገባ ስመለከት በጣም አስቂኝ ነው የሆነብኝ፤ ምክንያቱም ሚዲያው በወቅቱ እያሰራጨ የነበረው መረጃ ኢትዮጵያ በግጭት ማዕበል እየተናጠች ነው ይላል፡፡ የት ብለህ እንድትጠይቅ ያደርግሃል፡፡

ኢትዮጵያ በሰኔ ወር 2013 ዓ. ም ላይ ያካሄደችውን ምርጫ አዲስ አበባ ከተማ በመገኘት የምርጫውን ሂደት የማየት እድል እንደነበራቸውም ገልጸዋል፡፡

(ኢ ፕ ድ)

Leave a Reply