ሂውማን ራይትስ ዎች በአማራና አፋር ክልል የተፈጸመውን ግፍ ይፋ ሊያደርግ ነው፣ ሪፖርቱ ለትህነግ ማስተባበያ እንዳይሆን ተሰግቷል

  • የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር አማጺዎች በአማራ ክልል የጦር ወንጀል መፈጸማቸው ተመሰከረ

ሂውማን ራይትስ ዎች ትግራይ ነጻ ለማውጣት እንደሚንቀሳቀስ አስታውቆ በስፋት ወረራ እያከአሄደ ያለው ትህነግ በአማራና በአፋር ክልል ፈጽሞታል የተባለውን ኢሰብአዊ ተግባርና የፈጸመውን በህግ የጦር ወንጀል የሚባል ግፍ ሪፖርት አጠናቆ በቀናት ውስጥ ይፋ እንደሚያደርግ ለድርጅቱ ቅርብ የሆኑ ለዝግጅት ክፍላችን አመለከቱ። ሪፖርቱ አምነስቲ ተህነግን ካጋለጠ በሁዋላ በፍጥነት እንዲወጣ መታሰቡ አጓጊ ሆኗል።

እንደ መረጃ ምንጮቹ ከሆነ ድርጅቱ ትህነግ የአማራ ክልል ወሮ በነበረበት ወቅት የፈጸማቸው፣ በአፋር በተመሳሳይ ያከናወናቸው ጸረ ሰው ተግባራት በሪፖርቱ ይካተታል። በተመሳሳይ ትግራይ ውስጥ ተፈጽሟል የተባለው ድርጊትም በሪፖርቱ ይካተታል። የትግራይ ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ይፋ የሆነ ሆኖ ሳለ ከአማራና ከአፋር ጋር እንደ አዲስ አያይዞ ለማቅረብ የተፈለገበትን ምክንያት አልታወቀም።

የተባበሩት መንግስትታ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በጣምራ ያወጡት የምርመራ ሪፖርት ተቀባይነት ማግኘቱ በተረጋገጠበት፣ አምነስቲ በአማራ ክልል በዘጠኝ ቀን ብቻ በነፋስ መውጫ ብቻ ከሰባ በላይ ሰዎች መደፈራቸው፣ አስራ ስድስቱ ቃላቸውን መስጠታቸውን፣ የድርግቱ የኬንያ ተወካይ አቶ ፍስሃ ተክሌ ለጀርመን ሲናገሩ አዛዦች በአሰቃቂው የሴቶች መደፈር ላይ ተሳታፊ መሆናቸው አስታውቀዋል። ለተጠቂዎቹ የስነል ልቦና እርዳታም ሆነ ህክምና አለምደረጉንም አመልክተዋል።

ይህ ከአንድ ቦታ ብቻ ተመዝግቦ የወጣው፣ የኮምቦላቻ፣ ቆቦ፣ ደሴ፣ ሺናና የጅምላ ግድያዎች፣ ዘረፋዎች፣ አስገድዶ መድፈር፣ የመንግስት ንብረት ማውደምና የምስኪን አርሶ አደሮችን ማሳ እየወረሩ ማጨድና ማጋጋዝ የመሳሰሉት የትህነግ ተግባራት ያልተካተተበት የአምነስቲ ሪፖርት ” ትህነግ እንደለመደው በገለልተኛ አካላት ይጣራ ሲል በአቶ ጌታቸው አማካይነት ምላሽ ይሰጥበታል ብለን እንጠብቃለን” ሲሉ መረጃውን ያካፈሉን አመልክተዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ትህነግ ላይ ምስክር የሆኑት አቶ ፍስሃ ተክሌ የትህነግ ታጣቂዎች በርበሬ፣ ሽሮ፣ ዱቄትና ሊጥ መስረቃቸውን ይፋ አድርገዋል። የዘረፉትም ጦርነቱ ከማይመለክታቸው ከምስኪኖች ላይ እንደሆነ አመልክተዋል።

መንግስት ዘርን ለይቶ ጥቃት እንዳልፈጸመ፣ የጄኖሳይድ ምልክት አለመታየቱ፣ ጦርነቱ ትህነግ የአገር መከላከያ ሰራዊትን ካጠቃ በሁዋላ መጀመሩና መንግስት ረሃብን ለጦርነት እንዳላዋለ በዓለም ከፍተኛ በተባለው አካል ከተረጋገጠ በሁዋላ፣ አምነስቲ ጠንካራ የተሰኘ ሪፖርት ካሰራጨ በሁዋላ ሂውማን ራይትስ ዎች ቀደም ሲል የተፈጸመውንና በተደጋጋሚ አንድ ወገን ላይ የተንጠለጠለ፣ ነገር ግን የተባበሩት የስብአዊ መብት ኮሚሽን በሪፖርቱ አቋሙን አስተካክሎ ውድቅ ያደረገውን ክስ ሪፖርቱን እርማት እንደሚያደርግና እንደማያደርግ የዜናው ባለቤቶች አላስታወቁም።

See also  ትህነግ አማራ በተጨፈጨፈ ማግስት አዲስ አሳብ ያልያዘ ስልታዊ የድርድር መግለጫ ሰጠ

እጅግ በቅርብ የሶስቱንም ክልሎች ያካተተ ሪፖርት ለማውጣት ዶክመንቱን እያጠናቀቀ መሆኑንን የሚያውቁ ” ሰሞኑንን የመንግስት ለውጥ የጠየቀው አምነስቲ እስካሁን ቆይቶ ዛሬ ሁሉንም ያካተተ ሪፖርት ለማውጣት መሯሯጡ በጥንቃቄ የሚታይ ነው። ምን አልባትም ማሻሻያ ሊያደርግ ይችላል” ሲሉ ተናግረዋል። «ከሞት ከተረፉ ሰዎች የሰማነው ምስክርነት የህወሓት ታጣቂዎች የፈጸሟቸው አፀያፊ ድርጊቶች የጦር ወንጀል እና በሰው ልጆች ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች መሆናቸውን ያሳያሉ።» ሲል አምነስቲ ያቀረበው ሪፖርት ዲ ድብሊው እንደሚከተለው ተርጉሞታል። ከስር ያንብቡ

ህወሓት በኃይል በያዛቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች በርካታ ግፍ መፈፀሙን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለፀ።
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በኃይል ከያዛቸው የአማራ ክልል ቦታዎች አንዱ በሆነው የነፋስ መውጫ ከተማ ሴቶች በህወሓት ታጣቂዎች በቡድን መደፈር፣ ዘረፋ እና አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው የጥቃቱ ሰለባዎች ለድርጅቱ ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሴቶች ጠመንጃ ተደቅኖባቸው አፈ ሙዝ ስር ተደፍረዋል፣ ተዘርፈዋል፣ ተደብድበዋልም።
አምነስቲ ካነጋገራቸው የጥቃት ሰለባ 16 ሴቶች መካከል 14ቱ በህወሓት ታጣቂዎች በቡድን የተደፈሩ፣ የተዘረፉ እና የአካልና የስነ-ልቡና ጥቃት የደረሰባቸው ናቸው።
በከተማው የሚገኙ የህክምና ተቋማትን በህወሓት ታጣቂዎች ውደማቸውንና መዘረፉንም ገልጸዋል።
በአማራ ክልል ጋይንት ወረዳ ስር በሚገኘው የፋስ መውጫ ከተማ የህወሓት ታጣቂዎች ከነሐሴ 12 እስከ 21 ቀን 2021 ዓ/ም ድረስ ለዘጠኝ ቀናት የቆዩ ሲሆን፤ በእነዚህ ቀናት በከተማዋ ከ 70 የሚበልጡ ሴቶች መደፈራቸውን ለክልሉ ባለስልጣናት ሪፖርት ማድረጋቸውን ባለስልጣናቱ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ገልፀዋል።
ከተጎጅዎቹ መካከል በከተማዋ ምግብ በመሸጥ የምትተዳደረው የ30 ዓመቷ ገበያነሽ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል እንዲህ ብላለች።
“በእኔ ላይ ያደረጉትን መናገር ቀላል አይደለም። ደፈሩኝ። ልጆቼ እያለቀሱ ለሦስት ደፈሩኝ። ታላቁ ልጄ 10 ነው፣ ሌላው ዘጠኝ ዓመት ሆኖታል፣ ሲደፍሩኝ ልጆቼ እያለቀሱ ነበር። ታጣቂዎቹ የፈለጉትን አደረጉና ሄዱ። በአካልም ጥቃት ፈጸሙብኝ። ሽሮ እና በርበሬም ወሰዱ። በጥፊ መቱኝ እና ረገጡኝ። ጠበንጃቸውንም ልክ እንደሚገሉኝ አነጣጥረውብኝ ነበር።»
ሌላኛዋ የጥቃቱ ሰለባ በከተማዋ እንጄራ በመሸጥ የምትተዳደረው የ28 ዓመቷ ሃመልማል ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደተናገረችው፤ አራት የህወሓት ታጣቂዎች በቤቷ ውስጥ ነሐሴ 13 ቀን ምሽት ላይ ሲደፍሯት ሴት ልጇ ትመለከት ነበር።-
«ልጆች አሉኝ የ10 እና የሁለት ዓመት ሴት ልጆች። ልጆቼን ሊገድሏቸው ይችላሉ ብዬ ፈራሁ። ‘ልጆቼን አትግደሉ፣ የፈለጋችሁትን አድርጉኝ’ አልኳቸው። ታናሿ ተኝታ ነበር፣ ነገር ግን ትልቋ ነቅታ የሆነውን አየች። ያየችውን ልነግርህ የሚያስችል ጥንካሬ የለኝም።» ብላለች።
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ፀሃፊ አግነስ ካላማርድ ጥቃቱ ሥነ ምግባርን ወይም የትኛውንም የሰው ልጅ ክብር የሚፃረር ነው ብለዋል። ፀሐፊው አያይዘውም «ከሞት ከተረፉ ሰዎች የሰማነው ምስክርነት የህወሓት ታጣቂዎች የፈጸሟቸው አፀያፊ ድርጊቶች የጦር ወንጀል እና በሰው ልጆች ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች መሆናቸውን ያሳያሉ።» ነው።
“የህወሓት ታጣቂዎች ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ጨምሮ ሁሉንም የሰብዓዊ መብት ረገጣ እና የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በአስቸኳይ ማቆም አለባቸው።»ብለዋል። እንደ ዋና ፀሐፊው የህወሓት አመራርም መሰል የመብት ጥሰቶችን እንደማይታገስ ግልፅ ማድረግ እና ተጠርጣሪዎችንም ከድርጅቱ ማስወገድ አለበት።
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ፀሐፊ አግነስ ካላማርድ ጥቃቱ ሥነ-ምግባርን ወይም የትኛውንም የሰው ልጅ ክብር የሚፃረር ነው ብለዋል። ፀሐፊው አያይዘውም «ከሞት ከተረፉ ሰዎች የሰማነው ምስክርነት የህወሓት ታጣቂዎች የፈጸሟቸው አፀያፊ ድርጊቶች የጦር ወንጀል እና በሰው ልጆች ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች መሆናቸውን ያሳያሉ።» ነው።

See also  ዐቃቤ ሕግ በእነ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል መዝገብ በ62 ሰዎች ላይ ክስ መሰረተ

Leave a Reply