በዋግኽምራ ግንባር የጦር ግንባሮች ትህነግ ጸሃይ እየጠለቀችበት ነው

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ እና የምዕራብ በለሳ ወረዳ አናብስቶች ከዋግ ጀግኖች ጋር በዋግኽምራ ግንባር ታላቅ ጀብድ እየፈጸሙ መሆናቸውን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) በቦታው ተገኝቶ አረጋግጧል።

አሚኮ ያነጋገራቸው መቶ አለቃ አወቀ ዋለ እንደገለጹት እሳቸውን ጨምሮ የበለሳ ሕዝብ በሕዝባዊ ማዕበል ሽብርተኛውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ለመቅበር ዝግጅት በማድረግ ግንባር ተገኝቷል። አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን ለማፍረስ ወረራ እየፈጸመ መሆኑን እያየን ዝም ማለት የለብንም፤ በማዕበል የመጣውን በማዕበል ለመመለስ በግንባር ተገኝተናል ብለዋል።

መቶ አለቃ አወቀ የበለሳ ሕዝብም ከቀደሙት ጀግና አባቶቹ የተረከበውን የአልበገር ባይነት ወኔንና ትጥቁን አሟልቶ በዋግ ግንባር ተገኝቶ ሽብርተኛውን የትግራይ ወራሪ ኃይል እየጠራረገው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በወልቃይት ጠገዴ በነበረው ውጊያ በመሳተፍ ከፍተኛ ድል ማስመዝባቸውን የገለጹት መቶ አለቃ አወቀ አሁንም ለታላቅ ድል እየተፋለሙ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሌላው ዘማች አበበ አበሬ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል ከዚህ በፊትም የተከዜን ወንዝ አቋርጦ ለመምጣት ሲሞክር የሚደመሰሰው ተደምስሶ የተበተነው ተመልሶ እንደፈረጠጠ ተናግረዋል።
በአሁኑ ዘመቻም ያላቸውን ሆቴል፣ በርካታ ከብቶች እና የእህል ወፍጮ ለቤተሰባቸው በማስረከብ የሽብር ኃይሉን ለማጥፋት በግንባር መገኘታቸውን ገልጸዋል።

የአማራ ሕዝብ ጠላትን ማሸነፍ የሚያስችል በቂ ዝግጅት አድርጎ ተነስቷል ብለዋል። በቅርብ ቀናት ሽብርተኛውን የትግራይ ወራሪ ኃይል በመጣበት እንደሚቀብሩት አረጋግጠዋል፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ በለሳ ብርጌድ አዛዥ መጋቢ አምሳ አለቃ ማሙሽ በለጠ እንደገለጹት አጠቃላይ የሕዝቡ እንቅስቃሴ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን ለመደምሰስ የሚያስችል ነው። በአሸባሪው ኃይል የውሸት ፕሮፖጋንዳ የሚሸበር ሕዝብ የለንም ብለዋል። ሕዝቡ የሽብር ኃይሉን እኩይ ድርጊት ለማስቆም በከፍተኛ ሕዝባዊ ንቅናቄ ተነስቷል፤ የበለሳ ሕዝብ ለጠላት እጅ አይሰጥም ጀግና ሕዝብ ነው፤ የአባቶቹን ታሪክ ይደግማል፤ በከፍተኛ ሞራል ታጥቆ ተነስቷል፤ አስተማማኝ የሆነ ደጀን ሕዝብም አለው ነው ያሉት።

Via – አማራ ኮሚዩኒኬሽን

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2654 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply