የሚሌ ቀጠሮ – የባቲ ዘመቻ

ሰሞኑንን በተለይም ዛሬ ሚሌ የቲውተር ተዋጊዎች ጥይታ ሆና ውላለች። ዛሬ ረፋዱ ላይ ጸጋዬ አራርሳ “ሚሌ ትጃችን ወዳቃለች” ሲሉ በሁለት ወገን የተሰለፉ ሲሞግቱ የኖርዌይ ተወላጁ ሺትል ” ያልተረጋገጠ ግን ሚሌ ነጻ አውጪው እጅ ገባች” አሉ። እንደወትሮም ባይሆን ልብ ተቸራቸው። በቲወተር ሰፈር የአፋርን ጉዳይ በመዘገብና የጠራ መረጃ በመስጠት የሚታወቁት ሰው “አዲስ ነገር የለም። ግን ከባድ ውጊያ አለ” ሲሉ በተዛባ መረጃ አትናጡ ሲሉ ገለጹ።

Image

ከላይ የተገለጸው ወቅታዊ የሚሌ ግንባር እንደሚያስረዳው እስከ ረፋዱ ድረሰ ውጊያ ከመፋፋሙ በቀር ሚሌ በትህነግ እጅ አልገባችም ነበር። ይህንኑ ” ምንም አዲስ ነገር የለም።

ያው እንደ ሰሞኑ ነው” በሚል እንደምታ ቲውተር ካደረጉ በሁዋላ አዲሱ ” ሰበር” ፈጠራ የተባለ ዜና ተሰማ።

ተቀማጭነታቸው ኬንያ እንደሆነ የሚነገርላቸው “የምስራቅ አፍሪካ አጥኚና ተንታኝ” ከሳምንታት ውጊያ በሁዋላ ሚሌ በትህነግ እጅ መውደቋን በገጻቸው አተሙ። ይህ አዲስ አበባን ከአቅርቦት የሚገድባትና የጅቡቲን መንገድ መቁረጥ የሚያስችለው መስመር በትህነግ እጅ መግባቱን ረሺድ ሲናገሩ አንድ የቲውተር ደንበናቸው በቅጽበት አንድ ገሃድ አስታወሳቸው።

በዚህ ወር 4 እጅግ ድንቅና ታሪካዊ ቀን በመሆኑ ትህነግ በ4 አራት ኪሎን እንደሚቆጣጠር ረሺድ በቲውተር ገጻቸው በይፋ ማስታወቃቸውንና ዛሬ ቀኑ 15 መሆኑንን በምሰት ነበር ባልደረባቸው ያስታወሳቸው።

ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ እኚህ ሰው የኢትዮጵያንና የምስራቅ አፍሪቃን የፖለቲካ እንደምታ እንዲመረመሩ፣ እንዲተቹና አማራጭ ሃሳብ እንዲሰጡ፣ ፖሊሢ እንዲያመላክቱ የጀርመን ና የአሜሪካ ሬዲዮ ቋሚ ደንበኛ መሆናቸውን በመጥቀስ ጥንቃቄ በሁሉም ዘንድ ሊኖር እንደሚገባ ጠቆሙ።

አቶ ጸጋዬ አራርሳን ተከትለው የትህነግ ሚሌን ያዘ ዜና በስፋት ለማሰራጨት ” ግን ተረጋግጧል?” የሚል ጥያቄ የጠየቁ በርካታ ነበሩ። አቶ ጸጋዬ ” ሚሊ ትህነግ እጅ ወደቀች” ካሉ በሁዋላ በስፍራው ያሉ ግን አይመስልም። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ በተለምዶ የትህነግን ድል ከፍ አድርገው ሲያጎሉና ሲያራቡ የሚታወቁም ዝምታን የመረጡበት የሚሌ ግትንባር ዜና ሰበር ሊሆን ቀርቶ ጭርፍራፊ መሬ ሆኖ አልተሰማቸውም።

የትህነግ ሃይል በቡርካ በኩል ወደ ሚሌ ለመግባት ከኮምቦልቻ፣ ደሴና ከተለያዩ ግንባሮች ያለውን ሃይል አሰባስቦ በሙሉ ሃይሉ ከፍተኛ ትንቅንቅ ፈጥሮ እንደነበር በመግለጽ አሁን ላይ ተመቶ ወደ የአፋር የጸጥታና ደህንነት ሃላፊ ቢላይ አህመድ ከጋሳኪታ ወደ ቡርቃ እየተገፋ ወደ ባቲ ለመግባት መዳረሳቸውን እዛው ግንባር ሆነው አስታውቀዋል። የፋር ልዩ ሃይል፣ የአማራ ሚሊሻና ልዩ ሃይል፣ መከላከያ የተቀናጀ ጥቃት ማድረጋቸውን አመልክተው በቀሪ ሁለት ቀኖች ወደ ባቲ በመግፋት የሚፈጸም ጉዳይ እንዳለ አመልክተዋል። ምን እንደሆነ ግን አላብራሩም።

እውነታው ይህ መሆኑን የተረዱት ዳሂሎን ለአቶ ረሺድ ተአማኚነታቸውን እንደጣሉት በማስታወስ ለወደፊቱ የሁሉንም ወገን መረጃ እንዲመለከቱ ለማመልካት የሳቸውን ቲዊት በማያያዝ አሳጡዋቸውና የግል ገጻቸው ላይ ለጠፉ።

ቆየት ብለው የአፋር ልዩ ሃይል ያሰራጩትን ምስልና ቪዲዮ አጋሩ። ሚሌ ንግድ ባንክ አጠገብ ሆነው መረጃ ሲቀያየሩ የሚያሳይ ነበርና ከዛ በሁዋላ ሚሌ ከቲውተር ዜና በሌላ ዜና ተተካች።

የተረጋገጠ በሚል የአገር መከላከያ ጦርነቱን በበላይነት እየመራ፣ አየር ሃይል ከሰማይ እያገዘ፣ ሚሊሻና ልዩ ሃይል ተክለውበት፣ የአፋር ልጆች ክንድ ሆነው የትህነግን ሰራዊት ወደ ባቲ እየገፉት መሆኑንን የሚያሳየው ዜና ተከተለ።

የካሳጊታ የዞን አምስት የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ሃላፊ ” እነ ጌታቸው ረዳ ትናንት ሚሌ ላይ ቀተሮ እንዳላቸው ለውጭ ሃይሎች አስቀድመው አስታወቀው ነበር” ካሉ በሁዋላ ” ጠላት ከየአቅጣጫው ይዞት የመጣውን ሃይል ይዞ መጥቶ ያሰበውን ሳይሆን እኛ ያሰብነው ሆኗል” ብለዋል።

የሚሌን መስመር እንደያዘ አድርጎ የሚያወራው ትህነግ የተደመሰሰ መሆኑንን ያመልከቱት ኮማንደሩ በቀሪ ሁለት ቀኖች ጠላት ሙሉ በሙሉ ከአካባቢው እንደሚጸዳ አመልክተዋል።

በትላንትናው ዕለት የትግራይ ቲቪ ሰመራ ” በጀግኖቹ የትግራይ ሰራዊት እጅ ገባች” በሚል ዜና ዘግቦ ነበር። በዜናው ከተማ መሆኑ ባይለይም ተራራ ላይ የተነሱ የሚመስሉ ምስሎችም ታይተው ነበር። ሰመራን ከያዙ ለምን የዚዲዮ መረጃ አላቀረቡም በሚል ጥርጣሬ የነበረ ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት ግን ዜናው ሊቀጥል አልቻለም።

አካባቢው እጅግ ሞቃትና ውሃ የሚያስፈልገው ሲሆን የአገር መከላከያ የሎጅስቲክ በር ዘግቶ መያዙ የትህነግ ሃይል ላይ ትልቅ ፈተና እንደሆነበት፣ ከሁዋላ ተቸማሪ ሃይል ሲመጣ አየር ሃይል መስተንግዶ እነደሚአመቻቸ የተቆሙ ክፍሎች የጦርነቱ ውጤት እገሌ አሸነፈ ከሚለው በላይ እልቂቱ አሳዛኝ እንደሆነ አመልክተዋል። ይህ ሁሉ የሚሆነው ለምን እንደሆነ እንደማይገባቸው ገልጸዋል።

ይህን ዜና እያዘጋጀን ባለንበት ወቅት የአገር መከላከያና የአፋርና የአማራ ልዩ ሃይል እንዲሁክ ሚሊሻ አሰላለፋቸውን አስተካክለው ወደ ባቲ እየተጠጉ ነው። በሌላ አቅጣጫ ቆርጦ የገባ ሃይል መሆኒን እንደተቆጣጠር ታውቋል። መሆኒ ለመቀለ ቅርብ ከተማ ስትሆን ለምን መቆጣተር እንደተፈለገ ግልጽ አይደለም””

የአማራ መገናኛ ኤጀንሲ በበኩሉ በጋሽና ግንባር በርካታ ቦታዎች መለቀቃቸውን ስም ጠቅሶ ዘግቧል።


Leave a Reply