“እኛም እንረፍ እነሱም ይረፉ እንለያይ” – መግለጫ በዛ ግልጽነት የለም

ሰሞኑንን በስፋት የሚወራውና ሕዝብ መንግስትን ወደ ማስገደድ መዛወር አለበት የሚል ድምዳሜ ያላቸው ወገኖች ” እኛም እንረፍ እነሱም ይረፉ” የሚለው ጉዳይ ነው። ላለፉት ሃምሳ ዓመታት አቋም የማይወሰድበት፣ ነገር ግን የ”ቀብድ” ፖለቲካ የሆነው ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ሆና የምትቆይበት አግባብ ነው። አሁን እየመረረ የመጣው የትግራይ ጉዳይ ወደ አንድ ጠርዝ እንደሄደ የሚስማሙ በርካታ ናቸው። ሆኖም ግን ስጋታቸው ትግራይ እንድትለይ የሚፈለገው ኢትዮጵያ ላይ ከፈረደች በሁዋላ የመሆኑ ጉዳይ ነው።

ዛሬም ሆነ በፊት በትግራይ የመገንተል ጥያቄ መጨነቅና መጠበብ የማይታይባቸው ልሂቃኖችም ሆኑ ተራው ሕዝብ፣ እንዲሁም ከምር የመገንተል ሃሳብ ካለ ትህነግ ሁሉንም የማስፈጸም አቅምና ቁመና እየለው ዝም ማለቱ አንድ ላይ ተዳምሮ ብዙም ቁብ ያላገኘው የትግራይ አገር መሆን ጉዳይ፣ አሁን መሰማት ሲጀመር ” አድርጉት፣ በናታችሁ፣ ቶሎ፣ ስንት ላዋጣ..” የሚሉ ምላሾችን የሚያስተናግድ ተራ የቀልድና የፊስ ብ ኡክ ወሬ ሆኗል።

“እንፋታ፣ ትግራይ ትሂድና እኛም እነሱም በሰላም እንኑር፣ ወደፊት ሰክኖ መነጋገር የሚችል ትውልድ ሲመጣ የሚሆነው ይሆናል” የሚሉ ድምጾች እያየሉ ባሉበት በአሁኑ ሰዓት ዶክተር ደብረጽዮን ” የትግራይ ህዝብ ሪፈረንደም ያደርጋል” ሲሉ መሰማታቸው የምርጫው ሰሞን አብሮ ሪፈረንዶም መካሄዱ ሲገለጽ ነበርና ግራ የሚያጋባ ሆኗል። ከምንም በላይ ትግራይ ነጻ ለማውጣት እየታገሉ መሆናቸውን በይፋ እየገለጹ ኢትዮጵያ ላይ መንግስት አፍርሰው ሌላ መንግስት ለመትከል ኮሚቴ ማቋቋማቸውን ለማብራራት ሞክረዋል።

በመግለጫቸው ደጋግመው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲሉ የተደመጡት፣ የማራን ህዝብ እንደሚወዱ የገለጹት ዶክተር ደብረጽዮን ” የአብይ” የሚሉት የኢትትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ መደምሠሱንና አሁን አርሶ አደር እያስጨረሱ መሆኑንን በሃዘኔታ አመልክተዋል። በአማራ ክልል በተጠራ ክተት በርካታ ትህነግ የያዛቸው ስፍራዎች ስለመለቀቃቸውና የግንባር ዜና መልኩን ስለመቀየሩ የሚነገረውን ዜና ጭራሽ አላነሱም። በቀናት ወይም ግፋ ቢል በሳምንታት ያልቃል የተባለውና አዲስ አበባ ዙሪያ አለ ስለተባለው የትህነግ ሃይልም አላነሱም። ግን መንግስት ሞቱ እንደቀረበ ደጋግመው ተናግረዋል። ቢሞትም ግን ለሰላም ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል በትግራይ ህዝብ ላይ « የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል» ሲሉ በመግለጫቸው ጠቁመዋል። “አሸባሪ” የተባለው ቡድናቸው በየጦር ግንባሩ ለደረሰበት ወታደራዊ ሽንፈት ሕዝቡን ለመዋሸት የተጠቀመበት ስልት ነው” ሲሉ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ ምላሽ ሰጥተዋል። ለትግራይ ካሳ እንደሚጠየቅላት ለተገለጸው ደግሞ ” ሕዝቡን ከድል በሁዋላ ካሳ አለህ በሚል ለመሙላት ነው” ሲሉ አቶ አለባቸው ሃይሌ ተናግረዋል።

ዶ/ር ደብረጽዮን በሳምንት ውስጥ ተደጋጋሚ መግለጫ የተባለ ማብራሪያ ሲያሰሙ አዲስ የተስተዋለው የካሳ ጉዳይ፣ ኢትዮጵያ ላይ ያላቸውን ፍላጎት ሸፋፍኖ ማቅረብ፣ የጦር ሜዳ ውሎን በሚጨበጥ መልኩ ከማስረዳት ይልቅ ሰራዊታቸውን የማድነቅና ለደጋፊዎች ሞራል የማሰባሰብ ይዘት ላይ ማተኮራቸው ነው።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መሪ የትግራይ ሕዝብ የራሱን ውሳኔ በድምጹ ሪፈረንደም እንደሚያደርግ ካወሱ በሁውላ የሽግግር መንግስት የማቋቋም እቅድ መኖሩን በድጋሚ አስታውቀዋል። ከኦነግ ጋር የቆየ ግንኙነት እንዳላቸው አምልጧቸው ይፋ ባደረጉበት ድግምግሞሽ የበዛበት ንግግራቸው ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሌሎች አገራት ለትግራይ ካሳ እንዲከፍሉ እንደሚያስደርጉ ገልጸዋል።

ጦርነቱን የጀመረው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መሆኑ በተባበሩት መንግስትታ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ በአሜሪካ፣ በተለያዩ ተቋማትና በድርጅታቸው አመራሮች በጀብድ የተገለጸ መሆኑ ተገልጾ መከራከሪያ ቢቀርብ በምን መልኩና በየትኛው ህግ ካሳ መጠየቅ እንደሚያስችላቸው ደብረጽዮን አላብራሩም። በትግራይ ጂኖሳይድ የፈጸጸሙ ለህግ እንደሚቀርቡና የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ሞት እያመራ መሆኑንን ያስታወቁት የትህነግ መሪ፣ ዓላማቸው ትግራይን ነጻ ማውጣት ከሆነ ለምን አፋርን፣ አማራን እንደወረሩና “ከሰው ልጅ የማይጠበቀ” የተባለውን ጥፋት እንደፈጸሙና እየፈጸሙ ስለመሆናቸው አልገለጹም። “አልፈልግም ብሎ” ያሰናበተ ህዝብ መኖሪያ ድረስ ለመትመም አቅደው የተነሱበትን ዋና ምክንያትም ይፋ አላደረጉም።

በሙያቸው መምህር የሆኑት አቶ አለባቸው ሃይሌ እንደሚሉት ዶክተር ደብረጽዮን የካሳን ጉዳይ ያነሱት የትግራይ ተወላጆች ወደፊት ከፍተኛ ካሳ እንደሚያገኙ ተስፋ ለመስተት እንጂ ህጉ እንደማይፈቅድላቸው ይታወቃል። ምክንያቱም ጦርነቱን ራሳቸው ለመቀስቀሳቸው ራሳቸው፣ ሃያላን አገራት፣ የተባበሩት መንግስታትና የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች አረጋግጠዋል። ካሳ የሚጠየቁት አገሮች ይህን መከራከሪያ ያቀርባሉ።

Advertisements

“ጨውታው ሌላ ነው” የሚሉት አቶ አለባቸው፣ “ልክ ድሮ እንዳደረጉት የሰበሰቧቸውን ድርጅቶች ፈቃጅ በማድርፈግ በመልሶ ማቋቋም ስም ኢትዮጵያን ለማለብ ከሚነሳው ቅዠት የሚቀዳ ድርሰት ነው። ስሙ ተሻሽሎ ካሳ ተባለ እንጂ ያው ነው” ሲሉ ተናግረዋል። አያይዘውም የሃሳቡን መነሻ ለማሳየት እንጂ ” ቅዠት ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

ሕወሃት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲነሳ ከሚጠቀምባቸው አንዱ የትግራይን ህዝብ «የውሸት መረጃ መጋት» መሆኑን በጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ስረዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚንስትሩ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ ይገልጻሉ። ለዶይቼ ቬለ ቃላቸውን የሰጡት ዶ/ር ቢቂላ እንዳሉት «አሸባሪው ሕወሓት በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ካወጀ እና ኢትዮጵያ መበታተን አለባት ብሎ ከወሰነበት ጊዜ ጀምሮ እንደ አንድ መሳርያ አድርጎ የሚጠቀመው ውሸትን ነው። በፍጹም መሬት ላይ የሌለ ያልተነገረ ፣ የትግራይን ህዝብ የሚያጭበረብርበት እና የሚዋሽበት አንዱ መሳርያው በፍጹም ውሸት ላይ የተመሰረተ መረጃ መጋት ነው» ሲሉ ለመግለጫው ምላሽ ሰጥተዋል።

“ትህነግ በጥላቻ ስሜት አስክሮ የሚያመጣቸው ታዳጊ ህጻናት በየጦር ግንባሩ እየረገፉ ነው” ያሉት ዶ/ር ቢቂላ ቡድኑ « ትህነግ በተቆጣጠራቸው የአማራና የአፋር ክልሎች ህዝቡ የእግር እሳት ሆኖ ማቃጣል ሲጀምር፣ እጅግ በጣም ከፍተኛ አጣብቂኝና ከበባ ውስጥ ሲገባ ለትግራይ ህዝብ መንግስት ለመውደቅ ተቃርቧል የሚል ፍጹም ሀሰት የሆነ ምኞት እያንጸባረቀ ነው » ሲሉ የትህነግ መሪ መግለጫ ዓላማ ምን እንደሆነ አመልክተዋል።

“በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ተፈጽሟል” በሚል በህወሃት ሊቀመንበር የቀረበውን ክስ በተመለከተም ለዶይቼ ቬለ ምላሽ የሰጡት ሚንስትሩ «በትግራይ ክልል የዘር ማጥፋት ወንጀል ደርሷል ብሎ የሚናገረው እንደ የፕሮፖጋንዳ መሳርያ አድርጎ ሕዝብን ለማነሳሳት ነው ፤ ተጨማሪ ወጣቶችን ወደ ግንባር እየሄዱ እንዲረግፉ ለማድረግ ነው » ሲሉ አስታውቀዋል።

የዘር ማጥፋት ወንጀልም ፕሮፌሽናልና ገለልተኛ የሆኑ ተቋማት አጥንተው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል አልተፈጸመም የሚለው መረጃ በመሰብሰብና መሬት ላይ ያለውን እውነት በመተንተን የሚደረስበት ነው” ያሉት ዶ/ር ቢቂላ « አንድ ግለሰብ እንዲሁ ተነስቶ ጄኖሳይድ ተፈጽሟል ስለተባለ የሚሆን አይደለም።ይልቁንም በአማራና በአፋር ክልሎች በሰብአዊነት ላይ የደረሰው ግፍና ሰቆቃ የጦር ወንጀል ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል እጅግ በጣም አደገኛ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ዜጎችን በጅምላ የመረሸን ወንጀል ተፈጽሟል” ሲሉ አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንና የተባበሩት መንግስታት የሰባዊ መበት ኮሚሽን በጋር ባካሄዱት ምርመራ በትግራይ ጄኖሳይድ ስለመፈጸሙ የሚያሳይ ምልክት


Leave a Reply