“ደሴ፣ ወልዲያና ቆቦ በቀናት ነጻ ይወጣሉ” ከድርድሩ ጦርነቱ እንዳይፈጥን

በሁሉም ወገን አንድ የማይካድ ሃቅ አለ። ኢትዮጵያ በጦርነት፣ በዲፕሎማሲ ጫና፣ በሚዲያ ዘመቻና በማህበራዊ ሚድያ ትርክት እየታሸች ነው። ከሁሉም በላይ በችጋርና በሰላምና በድርድር ስም ክንዷን ለመጠምዘዝ ወከባው ከሩቅ ትዕዛዝ ሰጪነት ወደ ጎረቤት አገር በመምጣት ከሯል። ይህ ሁሉ እየሆነ መንግስት ” አልንበረከክም” ሲል ሕዝብ ደግሞ ” በነጻነቴ አምቢኝ” ብሏል።

ከሁሉም አይነት መንግስትን የመንቀል ሩጫ ጎን ለጎን የድርድር አቅም ለማጎልበት እየተካሄደ ያለው ጦርነት ትህነግ ይፋ እንዳደረገው በአራት ግንባር እየተካሄደ ነው። በመንግስት በኩል በይፋ ባይነገርም የአማራ ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ ዘገባዎቹ ውጊያው በአምስት ግንባር መከፈቱን የሚያመላከቱ ዘገባዎች እያሰሙ ነው። ትህነግ “ተስፋፊ” የሚለውን የአማራ ጦርና ሚሊሻ፣ እንዲሁም ” የአብይ ሰራዊት፣ ይፈርሳል” ሲል የሚያስፈራራውን የአገር መከላከያ ደምስሶ በአራት አቅጣጫ እየገሰገሰ መሆኑንን አትቶ መግለጫ ካወጣ በሁዋላ በሰዓት ልዩነት ” አማራ ትጥቅህን ሳትፈታ አካባቢህን ጠብቅ፤ እኛ ካንተ ጉዳይ የለንም፣ አማራና ትግሬ አንድ ነው…” የሚል መግለጫ አስከትሎ ነበር።

ኬንያ “ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ችግር ለመወጣን ሙሉ አቅም አላት” ስትል ብሊንከን ባሉበት የፕሬስ ኮንፍረንስ ላይ አመልክተዋል

ቀደም ሲል በማይካድራ፣ በቅርቡ በ በነፋስ መውጪያ፣ በሺና፣ በቆቦ፣ በኮምቦልቻ፣ በደሴ ፣ በመላው ዋግ፣ ላሊበላ … የፈጸመውንና ነጻ በወጡ አካባቢዎች አይጥ እንዳያጠፋላቸው ድመት፣ ጅብ ሲመጣ እንዳይጮህ ውሻ፣ አልበው እንዳይጠጡ ላሞቻቸውን፣ አርሰው እንዳይበሉ በልተው የተረፋቸውን ሰንጋ እየገደሉ፣ የነብሰጡር መታከሚያ ሆስፒታልና ጤና ኬላ እየዘረፉና አያፈራረሱ፣ ትምህርት ቤት ከጥቅም ውጪ ማድረጋቸው ሕዝብ ተናግሮ ሳይጨርስ ” ለአማራ ፍቅር አለን” የሚል መግለጫ ማውጣታቸው ቁጣ አስነስቷል።

በርካታ አስተያየትና ነቀፌታ የቅረበበት የትህነግ መግለጫ ትህነግ እያተቃና ግዛቱን እያሰፋ ወደ መንግስትነት ሲሮጥ አማራውን መሳሪያ እንደማያስፈታ፣ የመንግስትና የተለያዩ ተቁማት ሰራተኞችን እንደማይነካ ይልቁኑም ስራቸውን እንዲቀጥሉ ባሳሰበት መግለጫ ” ሰራዊታችን ምግባሩን በተቆጣጠረባቸው ቦታዎች ያሉ የሚመሰክሩት ነው” በሚል ሃረግ ማስከተሉ በማህበራዊ ገጽ ከመግለጫው ግርጌ ለዚህ ዘገባ በማይመጥን መልኩ ተወግዟል። ” እንዲህ እየተጠላ ወደ መንግስትነት ለመንደርደር ማሰቡ ይገርማል። ከአሁን በሁዋላ ትህነግና ኢትዮጵያ ምን የጋራ ጉዳይ አላቸው” ሲል የጠየቁም አሉ። “ትህነግ በየትኛው ሞራሉ ስለ አማራ ይናገራል? የአማራን ስም ሊጠራ እንኳን አይቻለውም” በሚል መፍትሄው በጉልበት እንደጀመረ በጀመረው መልኩ ማስቸረስ ነው” በሚል እሳት ሆነው ሃሳባቸውን የገለጹም ጥቂት አይደሉም።

በአራት ግንባር የድል ብስራት እያበሰረ ያለው ትህነግ፣ ብርጌድ ጨፍጭፎ ድል ማስመዘገቡን ጠቅሶ ላወታው መግለጫ የአብን ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ የሱፍ ኢብራሂም ” ትህነግ ለአማራ በጣም አስቂኝ የፍቅር ደብዳቤ ፃፈ። በጣም የተደበደበ / እየተሸነፈ፣ እየተበታተነ ነውና ይህን ማድረግ ነበረበት” ሲሉ በማህበራዊ ገጻቸው አስፍረዋል። አክለውም ” ትህነግ እየዋጀጀ ነው” ነው ሲሉ የሰሜን ጎንደርን ኦፕሬሽን አስታውሰዋል።

TPLF has written a very funny Billet Doux (Love Letter) for Amhara. It must do so for it is beaten heavily and in disarray (እየዋጀጁ ነው!)

“አሁን ጦርነቱ ባግባቡ እየተያዘ ነው፣ ስለሆነም በቅርቡ በድል ይጠናቀቃል!” ሲሉ ያስታወቁት አቶ የሱፍ፣ ደሴ፣ ወልደያና ቆቦ የምንገባበትን ቀን ጣቶቻችንን እየነካካን በመቁጠር ላይ ነን” ብለዋል። አቶ የሱፍ ” አይዞን ወሎ … የምናውቃቸው ሰዎች በተሰደደውና በተጨፈጨፈው ሕዝብ ላይ ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል” የሚል ሃረግ በመልዕክታቸው አሰራጭተዋል። ዝርዝሩን በፌስ ቡክ ገጻቸው ይከታተሉ።

አቶ የሱፍ ብቻ ሳይሆኑ ዋግ ሕምራ ላይ የማጥቃትና የማጽዳት ስራ እየተሰራ መሆኑንን የአካባቢውን አመራሮችና ዘማቾች ጠቅሶ የአማራ ማስ ሚዲያ እንዳለው አብዛኛው ዋግ ኽምራ ነጻ ወጥቷል።

በስፋት ወደ ግንባር እየተመመ ያለው የአማራ ሚሊሻ፣ ልዩ ሃይልና “የደርግ” ተብሎ የተበተነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲሁም አዲስ ምሩቅና የአካባቢ ሰልጣኞች ከትህነግ ጋር ድርድር እንደሌለ በግልጽ በማስታወቅ ወደ ዘመቻ እየገቡ እንደሆነ የመንግስት መገናኛዎች እያሰራጩ ነው።

አሜሪካ ቀደም ሲል አልፎ አልፎ ስለ ዕርቅ ብታወራም። እንደ አሁኑ ገፍታ አልሄደችም። ከወር በፊት ትህነግ ሰፊ ቦታዎችን በያዘና ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ አዲስ አበባ እየገሰገሰ እንደሆነና መንግስት ሊሆን ጫፍ ላይ መድረሱን የውጭ ሚዲያዎች ሲዘግቡ አሜሪካ በቁርጠኛነት ስለ እርቅ አልሰራችም ነበር። አሁን ላይ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የጦርነቱ አውድ በመቀየሩ፣ በተለይ አማራ ማምረሩ አሜሪካንን ብቻ ሳይሆን ትህነግን ጭንቀት ውስጥ እንደጣለ ነው። ትህነግም በመግለጫዎችና በማብራሪያዎች ተደራራቢ ጥሪ ለአማራ ሕዝብ እያሰማ ባለበት ሰዓት አሜሪካ ለዕርቅ መሮጧ በሃይል የሚሆን ነገር እንደሌለ በመረጋገጡ እንደሆነ ዜናዎች እየወጡ ነው። ዛሬ አቶ ጌታቸው ረዳ አሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃ ለመግባት ያላትን እቅድ መንግስት ማጣጣሉን አመልክተዋል። ይህ ገለጻቸው የሃይላቸውን መዳከም የሚያሳይ እንደሆነ ተመልክቷል።

“ምድራዊ ሃይል ያሻንን ከማድረግ አያግደነም” ሲሉ የነበሩት አቶ ጌታቸው ዛሬ “አብይ አህመድና አብረውት ያሉት ሎሌዎቹ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በአንድ ወገን ኢትዮጵያና በአፍሪካ ከምዕራቡ ዓለም ጋር የሚያድርጉት ጦርነት እንደሆነ አድርጎ ቅርጽ በማስያዝ ለማቅረብ እየሞከሩ ነው። አሜሪካ በወታደራዊ ጣልቃገብነት አቢይን ከሥልጣን ልታስወግድ ነው እያሉ በሌለ ዕቅድ የፈጠራ ወሬ ያወራሉ” ሲሉ እስካሁን ከሚደረገው በላይ የአሜሪካን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነትን መናፈቃቸው የሚያሳብቅና ወታደራዊ ሚዛኑ እንደተበላሸባቸው አመላካች እንደሆነ ተገልጿል። የግንባር ዜና እንደነጠፈባቸው አመላካች ሆኗል።

አሜሪካም ሆነ ራሱ ትህነግ አሁን በክተት እየተመመ ያለው ሃይል ከፍተኛ ስጋት በመፍጠሩ፣ መከላከያ በከፍተኛ ደረጃ መጠናከሩና ሕዝብ ሙሉ በሙሉ መነሳቱ ጦርነቱ የድርድር ሃሳቡን ሊቀደም እንደሚችል ግምት ያላቸው አሉ።


2 thoughts on ““ደሴ፣ ወልዲያና ቆቦ በቀናት ነጻ ይወጣሉ” ከድርድሩ ጦርነቱ እንዳይፈጥን

  1. አጣዬ ቢቀደም ኣይሻልም,,,?
    ኣሁን ይህን ኣምነህ ትጽፋለህ ወይ መረጃ ማሾለክህ ነው መጣን እየተባለ የሚዸረግ ጦርነት kkkk

Leave a Reply