“ትህነግ የሚተማመንበት አርሚ 4 በሙሉ ተደመሰሰ የባቲ ካሳጊታ ግንባር የጠላት ምሽግ ተሰበረ”

“ሰበር የድል ዜና” በሚል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ይፋ እንዳደረገው በባቲ ካሳጊታ ግንባር የጠላት ምሽግ ሙሉ በሙሉ ተሰብሯል። አርሚ አራት የሚባለው ትህነግ የሚተማመንበት ሃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱንም አስታወቀ። አምባው ተደፈረ።

በባቲ ካሳጊታ ግንባር ያለ የሌለ ዐቅሙን ሰብስቦ የመጣው የጠላት ኃይል ለወሬ ነጋሪ እንዳይተርፍ ሆኖ መደምሰሱን የኮሚኒኬሽን አገልግሎቱ አስታውቋል። አያይዞም የጠላት “አርሚ አራት” የተባለው ሠራዊት ከነ ተደራቢ ኃይሉ ሳምንት ሙሉ ሲቀጠቀጥ ከርሞ በዛሬው ዕለት ቀኑን ሙሉ በፈጀ ውጊያ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና በአናብስቱ የአፋር ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አከርካሪው እንደተሰበረ ገልጿል።


በዚህ አስደናቂ ውጊያ ጀግኖቹ ባደረጉት ተጋድሎ፣ ጠላት ሲተማመንባቸው የነበሩትን ሁለት ስትራቴጂካዊ ተራሮች ምሽጎቹን በመስበር ተቆጣጥሯል። በዚህ ሰሞን ዉጊያ ጠላት ሚሌ እገባለሁ በሚል የሰበሰባቸው በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎቹና ጀሌዎቹ ተደምስሰውበታል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማርከዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች፣ በርካታ ስናይፐሮችና መትረየሶች ተማርከዋል። ጠላት በዚህ ግንባር ከደረሰበት ውድመት የዛሬው እጅግ ዘግናኝ መሆኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አምለክቷል።

የአፋር ልዩ ሃይል ኮማንደር ከሁለት ቀን በፊት ሚሌን ለመያዝ አስቦ የተነሳውን ሃይል አስመልክቶ “ከሁለት ቀን በሁዋላ የት እንደምንደርስ ለሕዝብ ይፋ እናደርጋለን” ማለታቸው ይታወሳል።

የትግራይ አክቲቪስትና ደጋፊዎች እንዲሁም ራሱ ደርጅቱም ሆነ አቶ ጌታቸው ሰሞኑንን ዝምታን መምረጣቸው በግንባር ለመሸነፋቸው አመላካች እንደሆነ ተመልክቷል።

You may also like...

Leave a Reply