“መከላከያ ሲገፋ የዕርዳታ ካርዶች ተመዘዙ” ሰቆጣ በቁጥጥር ስር ውላለች ! አርብ ገጠመ

“እሪ በል ሰቆጣ፥ እሪ በል ኮረም
አርብ አርብ ይሸበራል እየሩሳሌም። አርብ ገጠመ!!

-ህወሃትንየማስጨነቅዘመቻቴዎድሮስበመጪውሳምንትይጀመራል !

“የአገር መከላከያ ሰራዊት ሲያጠቃና ሲገፋ የረህብና እርዳታ ካርድ ከየአቅጣጫው ይመዘዛል” ሲሉ ሰሞኑንን የታዘቡትን ዜጎች እየገለጹ ነው። እንደተባለውም አቶ ፊልትማን መንግስትን ወጥረው ይዘው ይህንኑ ፈቃድ እጃቸው አድርገዋል። ትህነግ ያተቃ በነበረበት ወቅት እሳቸውም ሆኑ ሌሎች አካላት፣ ተቋማትና ሚዲያዎች ረሃብና ችግር ፍጹም አጀንዳቸው አልነበረም።

በደሴ ከተማ ተፈጸመ በተባለ ክህደት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከሁዋላው ተውግቶ ትህነግ ከተማዋን ከተቆጣጠረና ወደፊት መግፋቱን ካስታወቀ በሁዋላ አዲሱ ዜና የነበረው አጣዬ ላይ ከኦነግ ሸኔ ጋር መግጠሙ ነበር።

ይህን ተከትሎ የትህነግ ሃይል አዲስ አበባ ለመግባት በአርባ ኪሎሜትር እርቀት ላይ እንዳለ እነ ማርቲን ፓውትን ጨምሮ በረካታ የውጭ ሚዲያዎች በስፋት ዘግበዋል። ዛሬም ድረስ አዲስ አበባ ተከባና ከነገ ዛሬ በአማጽያን ውስጥ እንደምትገባ እያስታወቁ ነው። ትህነግም በመሪዎቹ አማካይነት ” እጅ ስጡ፣ አማር ወዳጃችን ነው” የሚሉና የሽግግር መንግስት የማቋቋም ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ባልተለመደ ሁኔታ በተደጋጋሚ ማወጅ ጀመሩ።

በሰበር ዜና “እዚህ ደርሰናል” በምስል ” ይህ ከተማ ተያዘ” የሚለው ወሬና የውጮቹ የተናበበ መረጃ ተዳምሮ የዚሁ ስሌት መሪ አገራት ” ዜጎቻችን፣ ሰራተኞቻችን፣ ዲፕሎማቶቻችን…” እያሉ አዲስ አበባን ለቀው እንዲወጡ መወሰናቸውን አወጁ። አሁንም እያወጁ ነው። ዜጎቻቸው እንዲወጡ ባዘዙበት ከተማ ባለስልጣኖቻቸው እየተመላለሱ መንግስት ለመቀየር እየቆመሩ ነው። ይሁን እንጂ እስካሁን ትህነግ ከመግለጫ መዝለል አልቻለም። በተፈለገው ደረጃ ወደ አዲስ አበባ ቀርቶ የያዛቸውን ስፍራዎች እየለቀቀ መሆኑንን ነው መረጃዎች የሚያሳዩት። መረጃዎቹን እሱም ማስተባበል አልቻለም።

የሃሰት ዜና እንዴት እንደሚመረት ሲያስተምር በገሃድ በቪዲዮ የተጋለጠው ማርቲን ፕላውት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች ሚሌን ለመያዝ እየተመመ እንደሆነና” ሚሌን እንደሚይዙ እርግጠኞች ናቸው” ሲል ያሰራጨው ዜና በአፋር ልዩ ሃይል፣ በሚሊሻውና በድፍን ሕዝብ፣ በአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ እንዲሁም በመከላከያ ሃይል የጥምረት ጥቃት ተቀልብሶ ” ባቲ የመግባት ፍቃድ ከማንም አንጣብቅም፣ ያም ህዝባችን ነው” ያሉት የአፋር ሕዝባዊ ሃይል ባቲ ደርሷል።

Image

በባቲ ካሳጊታ ግንባር ሁለት ከፍተኛ የተባሉ ምሽጎችን ሰብሮ የገባወ የተቀናጀ ሃይል ዛሬ ረፋዱ ላይ ሶስተኛውንና ዋና የተባለውን ምሽግ ሰብሮ መቆጣጠሩ ተገልጿል። የአፋር ሃይሎች ” ሶስተኛውና ከኮንክሪት በላይ የተባለላት የጁንታው ምሽግ በዛሬው እለት ተሰብሯል..ይሄን ምሽግ ለመስበር.የተሰራው አስደናቂ ኦፕሬሽን ዝርዝር ይፋ ይሆናል” ሲሉ አስታወቀዋል።

See also  ራሽያ ዶላር መጠቀምን ለማቆም ወሰነች

በወረኢሉና በዳንሻ ፣ በዋግ በተመሳሳይ የጋራ ሃይሉ የትህነግን ሃይል እያጠቃና በርካታ ስፍራዎችን እያስለቀቀ መሆኑንን የክልሉ ሚዲያዎች ከስፍራው እያዘገቡ ነው። ከሁሉም በላይ የተዋጊና የእልህ ስሜቱ እየነደደ ያለው የአማራ ሰራዊት ” ግፋ በለው” እያለ መሆኑም እየተሰማ፣ እየታየ ነው። የትህነግ ሃይል መንገድ ተቆራርጦበት መውጪያ በማጣት “እየዋጀጀ” እንደሆነም መረጃ እየወጣ ነው። ምርኮኞቹ እንዳስረዱት በስፋት ጉዳት ደርሶበታል።

እንግዲህ የጦር ሜዳ ውሎው በተፈለገው መጠን ድል ሊያስገኝ ባለመቻሉ ይመስላል ዕርዳታ አጣዳፊ አጀንዳ የሆነው። በመምህርነት ስራ የተሰማሩትና የፖለቲካ ሳይነስ መምህር የሆኑት አቶ ግሩም ሰጠኝ ከቀናት በፊት “የኢትዮጵያ ሰራዊት ሲያጠቃ ድርቅና ችጋር አጀንዳ ይሆናል” በሚል የግል አስተአየታቸውን ጽፈው ነበር።

በአዲስ አበባ በውጭ የእርዳታ ተቋም የሚሰሩ ኢትዮጵያዊ ስማቸው እንዳይጠቀስ ጠይቀው እንዳሉት ” አሁን መከለክያ እየገፋ ስለሆነ ማስታገሻውና ትህነግ እንዲያገግም ማድረጊያው ዋና ስልት እርዳታ ነው። እየሆነ ያለውም ይኸው ነው” ሲሉ አስታውቀዋል። ኮምቦልቻና ላሊበላ አየር ማረፊያዎች ለበረራ ክፍት እንዲሆኑ መንግስት መፍቀዱም አግባብ ቢሆንም በዋናነት ትህነግ እንዲያገግምና ፋታ እንዲያገኝ ለማስቻል ነው።

“በላሊበላ ለወራት ሕዝብ ተራበ ሲባል የት ነበሩ? ቤቲን አቀዋለሁ ” በማለት ሃዘናቸውን የገለጹት የርዳታ ድርጅት ሰራተኛ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያሻው አሳስበዋል። ማንም ይሁን ማን እርዳታ ፈላጊዎች ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚገባ በማሳሰብ፣ ” ሴራው ላይ ግን ትኩተር መስጠት ግድ ነው። ወጥመዱንም ማምከን ይበጃል” ብለዋል። ሲያጠናቅቁም ” ሰላም የሚፈጠርበትን መንገድ ከእልህ በመውጣት ማሰቡ ይበጃል። ውጊያው ከበርካታ እጅ ጋር ነውና ሰላም አውርዶ የፈረሰውን መጠገኑ ይሻላል” ሲሉ አስተያየታቸውን አጠናቀዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለ በአገር መከላከያ የሚመራው የቅንጅት ሃይል ወደፊት እየገፋና በከበባ ውስጥ ያሉና የተበተኑ ሃይሎችን እያጸዳ መሆኑ ተሰምቷል። በዚሁ መሰረት ሰቆጣን መቆጣጠሩ ታውቋል።

See also  የኦብነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ በአስቸኳይ ስብሰባ ውሣኔዎች በሙሉ ተቀባይነት እንደሌላቸው ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

Leave a Reply