በቤኒሻንጉል ጠረፋማ አካባቢዎች ሰርገው የገቡ የትህነግ አስፈጻሚዎች ተደመሰሱ፤በሱዳን የሰብዓዊ ተቋም መታወቂያ ያላቸው ተማርከዋል

ሀገር የማፍረስ እቅድ ይዞ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠረፍ በኩል የገቡ በርካታ የአሸባሪው ህወሃት ተላላኪዎች ሲደመሰሱ፥ ብዛት ያላቸው የጥፋት ታጣቂዎች ከያዙት የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

አሸባሪዎቹን ለመደምሰስና በቁጥጥር ስር ለማዋል ህብረተሰቡ ለፀጥታ ሀይሎች መረጃ በመስጠት ቁልፍ ሚና ተጫውቷል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ በሱዳን ካርቱም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋም በሚል መታወቂያ የያዙ ግለሰቦች እንዳሉበት ጠቁመዋል፡፡

የአሸባሪው ህወሃት ተላላኪ ከሆኑት እነዚህ ግለሰቦች ጋር ክላሽንኮቭ ጠብ መንጃዎች ከመሰል ተተኳሽ ጥይቶች፣ “አርፒጂ” መሳሪያ ፣ ፀረ-ሰው እና ተሸከርካሪ ፈንጂዎች፣ የእጅ ቦምቦች፣ መገናኛ ሬዲዮኖች፣ ተንቀሳቃሽ ስልኮችና የጦር ሜዳ መነጽሮችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አመልክተዋል።

እንዲሁም ብዛት ያለው የሱዳን ፓውንድ፣ የሱዳን ጦር ዩኒፎርሞች እና ሌሎችም በጸጥታ ሃይሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ያስታወቁት፡፡

ከተደመሰሱት መካከል በሱዳን ስልጠና ወስደው ወደ ክልሉ የገቡና እራሱን ቤህነን ብሎ የሚጠራውን አሸባሪ ቡድን አርማ የያዙ እንደሚገኙበትም አስረድተዋል፡፡

የክልሉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መምሪያ ዕዝ አብይ ኮሚቴ አባልና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሃመድ ለኢዜአ እንደገለጹትት፤ ሰሞኑን እርምጃ የተወሰደባቸውና በቁጥጥር ስር የዋሉት የሽብር ቡድን አባላት፣ በክልሉ ጠረፋማ አካባቢ በሆነው አሶሳ ዞን ኩርሙክ፣ ሸርቆሌ እና መንጌ ወረዳዎች የገቡ ናቸው።

ከህወሓት ጋር በማበር ሽብር እየፈፀሙ ያሉ የጥፋት ቡድኖች ዓላማ ኢትዮጵያን ማፍረስ መሆኑን ህዝቡ ሊረዳው ይገባል ያሉት ኮሚሽር አብዱልአዚም፤ ከጥፋቱ ጀርባ የአሸባሪው ህወሃት እና ኢትዮጵያን ለማዳከም የሚጥሩ የውጭ አካላት መኖራቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ህዝብ እና መንግስት የሃገር መከለከያ ሠራዊት እንዲሁም በየደረጃው በሚገኙ አካላት በቅንጅት ባደረጉት ኦፕሬሽን የአሸባሪው ተላላኪዎችን በመደምሰስ የጥፋት እቅዳቸውን ማክሸፍ መቻሉንም አስታውቀዋል፡፡

በተያያዘ መረጃ፥ የተደመሰሱትን እና በቁጥጥር ስር የዋሉትን የአሸባሪው ህወሃት የጥፋት አስፈጻሚዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋልና ለመደምሰስ ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት መረጃ በመስጠት ቁልፍ ሚና መጫወቱን የመከላከያ ምንጮች ለኢዜአ አረጋግጠዋል።

የመከላከያ ምንጮቹ እንዳሉት፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የጸጥታ አስከባሪ ሃይሎች በቁርጠኝት ድጋፍ ማድጋቸውን ጠቁመው፥ ይህም ቡድኑ እንዲደመሰስ ከፍተኛ አቅም ፈጥሯል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ሠራዊቱ በየቦታው የተበተነውን የጥፋት ቡድን ርዝራዦች አድኖ የመደምሰስ ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉም ታውቋል፡፡

የክልሉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መምሪያ ዕዝ አብይ ኮሚቴ አባልና የሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሙሳ ሃሚድ በበኩላቸው፤ የተደመሰሱ የጥፋት ተላላኪዎች ትኩረት ያደረጉት ንጹሃን ላይ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የጥፋት ቡድኑን ከአካባቢው ሙሉ ለሙሉ ለማጽዳት የሃገር መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻ እና ህብረተሰቡ ተቀናጅተው እየሰሩ መሆናቸውንም ጠቅሶ ፋና ዘግቧል።

Related posts:

መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ
ፊንላንድ 3.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሚይዙ ዋሻዎች አዘጋጀች - ለኢትዮጵያውያን ጠቃሚ የጥንቃቄ መረጃ
"አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንና የጥፋት ኃይል ዳግም ከሞከረ የማያዳግም ቅጣት ይጠብቀዋልʺ
ሻዕቢያና ትህነግ - ሰሞኑን ይህ ሆነ
ትህነግ ጦርነት እንደሚከፍት ይፋ አደረገ፤ አማራ ክልል "ለክተት ተዘጋጁ"አለ፤ መከላከያ በተጠንቀቅ ላይ ነው
ወልቃይት "የወር ስንቅህን አዘጋጅተህ ለክትተ ጥሪ ተዘጋጅ”
በሶማሊያ በሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የሽብር ተልዕኮ የተሰጣቸው ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አማራ ክልል ትህነግ ዳግም ጦርነት ስላወጀ የ"ዝግጁነትን" አዋጅ አወጣ
ኡጋንዳ ፀረ-ኢትዮጵያ ለሆኑ ሃይሎች ከለላና ድጋፍ እንደማታደርግ አስታወቀች፤ የሚወራው ሃሰት ነው አለች
በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ
በዳኝነት ስርአቱ ላይ የሚታዩ የሙስና ተግባራትን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

Leave a Reply