ምዕራባውያን የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት የችግር አባባሽነት ዘመቻ ላይ ናቸው

በኢትዮጵያ ያለው ችግር መፍትሄ እንዳያገኝ አንዳንድ ምዕራባውያን የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት የአባባሽነት ዘመቻ ላይ መሆናቸውን ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ ገለጸች።

የህወሓት ሽብር ቡድን “አዲስ አበባን ለመቆጣጠር እየተቃረበ ነው” የሚለው የምዕራባውያኑ መገናኛ ብዙሃን የተለመደ በሀሰተኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ዘገባ እና ፕሮፓጋንዳ መሆኑንም ትናገራለች፡፡

ጋዜጠኛዋ ዘ ሬይ ዞን ከተባለ የዜና ድረ-ገጽ ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ እንዳስረዳችው ከእነዚህ ተቋማት ድጋፍ የሚያገኘው አሸባሪው የህወሃት ቡድንም ለኢትዮጵያ ቀርቶ ላለፉት በርካታ ዓመታት ላስተዳደረው የትግራይ ህዝብም እንደማይጠቅም በተግባር አሳይቷል።

የህዝብ ይሁንታን አግኝቶ በህግ የተመረጠን መንግስት በሀሰተኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ መተቸት እና መክሰስ በቀጥታ ህዝብን መክሰስ ነው ብላለች።

በመሆኑም አንዳንድ የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን እና ሀገራት ከዚህ ድርጊታቸው መቆጠብ ይገባቸዋል ነው ያለችው፡፡

ጋዜጠኛ ሄርሜላ ለግጭቱ መቀስቀስ ምክንያት የሆነው ራሱ የሽብር ቡድኑ መሆኑን ጠቅሳ፤ ለዚህም ቡድኑ አስቀድሞ የራሱ ታጣቂዎቹን ሲያሰለጥን በመቆየት በክልሉ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ማጥቃቱን ገልጻለች።

የህወሓት ሽብር ቡድኑ በዚሁ በመቀጠል ወደ ኤርትራ እና አማራ ክልል ተደጋጋሚ ከባድ መሳሪያ መተኮሱን አስታውሳለች፡፡

ሀገሪቱን ለ27 ዓመታት የመራው የሽብር ቡድኑ ራሱ ያወጣውን ህገ-መንግስትና ሌሎች ህጎችን በመጣስ የፌዴራል መንግስቱ በዓለም አቀፉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲራዘም ያደረገውን ምርጫ በህገ-ወጥ ውሳኔውን በመጣስ ለይስሙላ ምርጫ ማካሔዱ አንዱ የስርዓት አልበኛነቱ ማሳያ እንደሆነም ጠቅሳለች።

ጋዜጠኛ ሄርሜላ ከህግ ማስከበር ዘመቻው በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ትግራይ ክልል የዕርዳታ ቁሳቁስ እንዳይገባ ከልክሏል በሚል ለቀረበላት ጥያቄም መንግስት ለዜጎቹ የሚቆረቆር እና ሀላፊነት የሚሰማው መሆኑን ጠቅሳ ውንጀላው በተጨባጭ እውነታውን የማያሳይ ከንቱ ወቀሳ ስለመሆኑም አስረድታለች።

መንግስት ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የዕርዳታ ቁሳቁስ እንዲያደርሱ ወደ ትግራይ ክልል የላኳቸው ተሽከርካሪዎች መመለስ እንዳልቻሉ በተደጋጋሚ መግለጹንም አክላለች።

የህወሓት አሸባሪ ቡድን ተሽከርካሪዎቹን ለወታደራዊ እንቅስቃሴ እየተገለገለባቸው መሆኑን በርካታ ማስረጃዎች መውጣታቸውን አስረድታለች።

የሽብር ቡድኑ እያደረገ ያለው ጥረት በህግ የተመሰረተውን መንግስት ለመናድና ሀገሪቱን ለመበታተን መሆኑን ጋዜጠኛዋ ገልጻለች።

ይህን ዕኩይ ሴራ በሚገባ የተረዱት ኢትዮጵያውያን አሻንጉሊት መንግስት በላያቸው እንዲጫንባቸው እንደማይፈልጉ እና እንደማይፈቅዱም ጭምር በተደጋጋሚ እየገለጹ ነው፡፡

አሜሪካ ባለፉት 30 ዓመታት ከሽብር ቡድኑ ጋር የነበራትን የጥቅም ግንኙነት ለማስቀጠል የሚያስችሏትን አካሄዶች እየተከተለች ነው።

ለበርካታ ዓመታት ንጹሃንን በጅምላ በማሰር፣ በመግደል፣ በማሳደድ፣ በማሰደድ፣ በመድፈር፣ በመዝረፍ የሽብር ተግባር ላይ የቆየን የሽብር ቡድን ዳግም ወደ ስልጣን ለመመለስ በማሰብ ንጹሃን የትግራይ ተወላጆች እንደቅጠል መርገፍ የለባቸውም ብላለች፡፡

የሽብር ቡድኑን ወደ ስልጣን መመለስ የኢትዮጵያ እንዲሁም ራሱ የትግራይ ህዝብ ዳግም ባለፉት 30 ዓመታት ወደ ነበረበት የግፍ አገዛዝ እንዲመለስ መፍቀድ በመሆኑ የሽብር ቡድኑን የሚደግፉ የትግራይ ተወላጆችም ሆኑ ሌሎች የውጭ እና የውስጥ አካላት ቆም ብለው ማሰብ ይጠበቅባቸዋል ነው ያለችው፡፡

ህዳር 10/2014 (ኢዜአ)

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2654 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply