ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ሰላም እንዲመጣ ከፈለጉ አሸባሪው ህወሓት ላይ እርምጃ መውሰድ አለባቸው- ፕሮ. ፊትዝ ጌራልድ

ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ሰላም እንዲመጣ ጽኑ ፍላጎት ካላቸው አሸባሪው ሕወሓት ላይ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው በካናዳ ዊልፍሪድ ላውሪየር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር አን ፊትዝ -ጌራልድ ገለጹ።

አሜሪካን ጨምሮ አንዳንድ ምዕራባውያን አገራት በሕዝብ የተመረጠ መንግስትንና አሸባሪው ህወሓትን በእኩል ሚዛን ማስቀመጣቸው ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ድርጊት መሆኑን ነው ፕሮፌሰሯ የተናገሩት።

ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ሰላም እንዲመጣ ጽኑ ፍላጎት ካላቸው አሸባሪው ሕወሓት ላይ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸውም አመላክተዋል።

ፕሮፌሰር አን ፊትዝ-ጌራልድ ለኢዜአ እንደገለጹት ÷ በሰሜን ዕዝ ላይ አሰቃቂ ጥቃት በመፈጸም ኢትዮጵያ አሁን ለገባችበት የጸጥታ ችግር መንስኤ የሆነው አሸባሪው ህወሓት በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የክህደት ጥቃት የፈጸመ ቡድን ነው።

በመሆኑም ይህ ቡድን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ከተመረጠ መንግስት ጋር የሞራል እኩልነት መስጠት መሰረታዊ ስህተት መሆኑን አስገንዝበዋል።

“በዚህም አሜሪካን ጨምሮ አንዳንድ ምዕራባውያን አገራት ውግንና ያለውና ሚዛናዊ እይታ የጎደለው አካሄድ እየተከተሉ ነው” ብለዋል።

ይህ የተሳሳተ አካሄድ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለመፍታት እንደማያግዝም አመልክተዋል።

“በኢትዮጵያ አሁን ስልጣን ያለው መንግስት ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ ያለው ነው፤ ድምጽ ለመስጠት የወጣው ሕዝብ ቁጥር በቅርብ ጊዜ ዓለማችን ላይ ከተደረጉ ምርጫዎች የሚበልጥ ነው” ብለዋል ፕሮፌሰሯ።

ለግጭቱ መከሰት፣ መራዘምና መስፋፋት እንዲሁም ለዜጎች መከራና ስቃይ ተጠያቂ በሆነው አሸባሪው ህወሓት ላይ ምዕራባውያኑ እርምጃ አለመውሰዳቸው የተሳሳተ መንገድ እየተከተሉ እንደሆነ ማሳየቱን ገልጸው ÷ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና ማሳደራቸው ተገቢነት እንደሌለው ገልጸዋል።

ምዕራባውያኑ አሸባሪው ህወሓት የፈጸማቸው ድርጊቶች ላይ ተገቢውን እርምጃ አለመውሰዳቸው አስገራሚ መሆኑንም ተናግረዋል።

ይህ አካሄድ የባይደን አስተዳደርን ጨምሮ የምዕራባውያን አገራትን ለጦርነቱ መራዘመና እየደረሰ ላለው አስከፊ ሰብዓዊ ጉዳት ተጠያቂ የሚያደርግ መሆኑን ነው ፕሮፌሰር አን የገለጹት።

በመሆኑም ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ሰላም እንዲመጣ አሸባሪው ህወሓት ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድና ተጠያቂ ማድረግ እንዳላበቸው ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ምዕራባውያን በኢትዮጵያ እየተከተሉት ያለውን ፖሊሲ ዳግም በማጤን ገንቢ ሚና መጫወት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)

Related posts:

መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ
ፊንላንድ 3.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሚይዙ ዋሻዎች አዘጋጀች - ለኢትዮጵያውያን ጠቃሚ የጥንቃቄ መረጃ
"አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንና የጥፋት ኃይል ዳግም ከሞከረ የማያዳግም ቅጣት ይጠብቀዋልʺ
ሻዕቢያና ትህነግ - ሰሞኑን ይህ ሆነ
ትህነግ ጦርነት እንደሚከፍት ይፋ አደረገ፤ አማራ ክልል "ለክተት ተዘጋጁ"አለ፤ መከላከያ በተጠንቀቅ ላይ ነው
ወልቃይት "የወር ስንቅህን አዘጋጅተህ ለክትተ ጥሪ ተዘጋጅ”
በሶማሊያ በሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የሽብር ተልዕኮ የተሰጣቸው ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አማራ ክልል ትህነግ ዳግም ጦርነት ስላወጀ የ"ዝግጁነትን" አዋጅ አወጣ
ኡጋንዳ ፀረ-ኢትዮጵያ ለሆኑ ሃይሎች ከለላና ድጋፍ እንደማታደርግ አስታወቀች፤ የሚወራው ሃሰት ነው አለች
በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ
በዳኝነት ስርአቱ ላይ የሚታዩ የሙስና ተግባራትን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

Leave a Reply