“አንገነጠልም፣ ሞኛችሁን ፈልጉ” V ” የኦሮሞ ቅጂ ነው” ስውር ፖለቲካ ከትህነግ መንደር

አቶ ጄፍሪ ፌልትማን ኬንያ ከርመው አዲስ አበባ ከትመዋል። የቀድሞ የናይጀሪያ መሪ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆም አዲስ አበባ ናቸው። አሜሪካ በይፋ እንዳለችው ጦርነቱ የሚቆምበትን መንገድ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አድርጋ የሾመቻቸው ፌልትማን አበክረው እንደሚሰሩ በእንግሊዝኛ፣ በትግርኛና በኦሮምኛ ተናግራለች። ድግሱ ቢታወቅም በሰላም ከተጠቀለለው ሴራ ጎን ለጎን ” ሁላችሁም ተው፣ አማጺያን ወደ አዲስ አበባ ጉዞ አቁሙ” ሲሉ ሰላምን ከሽብር ዜና ጋር አዋህደው እየጋቱን ነው። ሚዲያዎቻቸውም የምድሩን ሽብር ጨርሰው አይሩን ማጠን ጀምረዋል።

አሜሪካ እንዲሆን የተጨነቀችለት ሰላምና ከሰላሙ በሁዋላ ኢትዮጵያ ምን እንደምትመስል ባይታወቅም፣ በኢትዮጵያ መንግስት አስወግዳ መንግስት ልትተክል እየሰራች መሆኑን በፕሬስ ክለብ ዘጠኝ የተተኪ መንግስት ስብሰቦችን አስተዋውቃለች። የስብሰባ ቦታውም “ዕውቅና ሰጥቻለሁ” ለማለት እንደሆነ ግልጽ ነው። እንዲህ ያለ አይንን በጨው ያጠበ ድርቅና ብርቃቸው አይደለምና የህንኑ ስብስብ በሚከፍሏቸው “ኢትዮጵያዊያን” በየቋንቋው እየተበለተ እንድንጎርስ ተድርጓል። እናም “ምርጫችሁን ወዲያ” ብላ ” እኔ መርጬላችኋለሁ ተቀበሉ” እያስባለች ያለችው አሜሪካ ነክሳናለች። ንክሻዋ ደግሞ በከራንቻዋ ነውና እየበሳሳን፣ እየዘለቀ አጥንታችንን ሊወጋ ተቃርቧል። ትህነግን እንደ ድመት ግልገል በፊት ጥርሷ አንጠልጥላ ከወዲያ ወዲህ የምትለው አሜሪካ፣ ራሱ ትህነግ ሊያምን በማይችለው ደረጃ እንደ አራስ ስትነከባከበው መገንጠሉን ረስቶ ሌላ ታሪክ ውስጥም ሊገባ ከጃጅሎታል።

መንግስት ለማፍረስ በግልጽ እየሰራች፣ በምታፈርሰው አገር ቤተመንግስት እንዳሻት የመንጎራደድ ስልጣንና ጉልበት ያላት አሜሪካ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባርን ማየት እንደማይፈልግ በገሃድ እየተናገረች መልሳ እነሱኑ ህዝብ ጫንቃ ላይ ለመትከል የምታደርገው ፈርጀ ብዙ ትንቅንቅ ከማስገረምም በላይ ህሊናን የሚፈታተን ሆኗል። ይህ ህሊናን የሚሞግተው የመጠቃት ስሜት እጅግ እየከረረ በአይነቁራኛ መጠባበቅ አምርቷል። በመንግስት ደረጃ በገሃድ ” ከፍለጋችሁ ሂዱ” የተባለበት ደረጃ ተድርሷል። ይህን የመንግስት አቋም ሕዝብ በአብዛኛው የደገፈው ለመሆኑ የማህበራዊ ሚዲያዎች ግብረ መልስ ምስክር ነው። ከትህነግ ወገን ግን እንደሱ ለማለት ” ጊዜው ረፍዷል” የሚል አቋምና ጦርነቱን የመግፋት አሳብ ተጠናክሮ ቀጥሏል። እንደውም ” ሞኛችሁን ፈልጉ የምን መገንጠል ነው” ብለዋል።

ተናጋሪዋ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ኦሮሞ በመሆናቸው ” እኛ በሰጠንሽ ኢትዮጵያዊነት” ሲሉም ለኦሮሞ ያላቸውን ድብቅ አመለካከት ይፋ አድርገውታል። ኦሮሞን በደብዳቤ ኢትዮጵያዊ የሆነ፣ በቅጂ የደረሰው ሲል ቴድሮስ ጸጋዬ በቁጣ የደጋፊዎቹን አቋም አንጸባርቋል። ተሳድቧል። እንግዲህ ይህ ነው የትህነግና የሸኔ ጋብቻ!! ወደ መነሻዬ ልመለስ።

ገና ኦሮሚያ ሳይገባ ወለጋና ሸዋን በመለያየት “የመካከለኛው ኦሮምያ ወለጋዎችን እያሰረ ነው፤ ቤት አታከራዩአቸው ያላል” የሚል ኦሮሞን በኦሮም ለማባላት ሴራ እየጠመቀ ያለው ትህነግ የወደፊት እቅዱ እያፈሰሰበት ነው። በደጋፊ አባላቱና ” አጋሬ” በሚላቸው እያስነገረ ያለው መርዝ ቀጣይዋ የገሃነብ ሰልፈኛ ኦሮሚያ ላለመሆኗ ማረጋገጫ አይሰጥም። የመካከለኛው ኦሮሚያ ተወላጆችን ነቅሎ የወለጋ ኦሮሞዎችን ለመተካት የሚደረገው ሩጫ ገና ካሁኑ በቅኔ እያጋጨና በቲውተር እንደ እነ ጸጋዬ አራርሳ ባሉ ወገኖች ማስታወቂያ እየተሰራለት ነው። ከዚህ አንጻር መርምሮ ምርጫን ማስተካከል ግድ ነው።

“ኦሮሞ ኦሮሙማ” ኦሮሞሞ ኦሮሞ ነው ተብሎ፣ ሁሉም ኦሮሞ አንድ መሆኑ ተገልጾና ታምኖበት ተከባብሮ ያለ ልዩነት በስለም የሚኖረውን ሕዝብ በቀበሌ ከርትሰው ሊያጫርሱትና ትንንሽ ሊያደርጉት የጀመሩትን ሴራ ለውጡ ቀድሟቸው ቢከሽፍም አሁን ግና ለገና ስልጣን እንይዛለን በሚል ቅዠት ከወዲሁ ሊተገብሩት እያመቻቹ ነው። የኦነግ ሸኔና የትህነግትን ጥምረት የሚደግፉት እነ ሰጋዬ አራርሳ ስለምንና ስለማን ብለው ይህን ሃሳብ ገዝተው እየሸጡት እንደሆነ መረዳት ለጊዘው ግራ ቢያጋም ውጤቱ የሚቆጭ ከመሆን አይዘልም። ጉዳዩን ላለማስፋት እንጂ በርካታ የኦሮሞ ልሂቃን በዚህ ጉዳይ ተዘጋጅተውበታል። የሚመታም ነገር የለም።

አቶ ጸጋሬ አራርሳ በወለጋና በሌሎች ኦሮሞዎች መካከል ልዩነትን የሚያስነሳ ሃሳብ ማራመድ የፈለገው ለምንድን ነው? ምንስ ይጠቅማ? ማንን ያስደስታል? ነገ ወዲት ያመራል? ማን ይከተላል? ይሰልሳል … የመካከለኛው ኦሮሚያ ኦሮሞዎች የሚመሯት፣ የጊኒጪና ማቦ ወይም ሰላሌ፣ ወይም ጅማ፣ ወይም ሃረር፣ ወይም … የሚመሯት ኦሮሚያ አትፈለግም? ማንስ ነው ለኦሮሞ በልክ የተሰራ? የአንድ ሰፈርና ቀበሌ ሰዎችን አመራር ያደረገውና ዛሬ …ኦሮሞ ሊመክርበት የሚገባ ነጥብ

እስኪ ስለ አምቦ ስብሰባ ላንሳ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አምቦ አበበች መታፈሪያ ሆቴል ታዋቂና አንጋፋ ኦሮሞውችን፣ ከከተማዋ የተመረጡትን አካተው ስብሰባ አካሄደው ነበር። በዛ ስብሰባ ላይ ” ነዲ ገመዳ የት ነው? ነግረን” ተባለ።

ቤቱ ጸጥ አለ። ነዲ ገመዳ በርካቶችን ከመሰላና ግራዋ ከግድያ ያተረፉ፣ በደደርና ምስራቅ ሃረርጌ እልቂትን ያስቆሙና የሚቃወሙ፣ መምህራንን ሰብስበው በሰላም ወደ ድሬደዋ በክብር የሸኙ ምርጥ ሰው እንደነበሩ አውቃለሁ። አብይ አሕመድ ጸጥታውን መስበር አቃታቸው።

በዚህ ጥያቄ መነሻነት በድብቅ የተፈጸሙ ወንጀሎች፣ ትህነግ ኦሮሞ ላይ ምን እንደፈጸመ ተነገረ። ቤቱ በለቅሶ ሲቃ ተሞላ። የአምቦ አውራ ደራራ በጠራራ ጸሃይ የተገደሉባት አምቦ እለቱን በርክታ ሚስጢር ተገልጦላት አመሸች።

ከ45 ሺህ በላይ የኦሮሞ ልጆችን አስሮ ሲገርፍና ሲያሰቃይ፣ እንዲሁም የሞቱትን ቤታቸው ይቁጠራቸውና እነ ጸጋዬ አራርሳ እንመራዋለን ሲሉት በነበረው የለውጥ ትግል ውስጥ ስንቶች ተገደሉ? ስንቶች አካላቸው ጎደለ? ስንቶች ታሰሩ? ለመሆኑ የልጇ አስከሬን ላይ ተቀምጣ የተገረፈችው እናት የዛሬን አያድርገውና በቪኦኤ ስትጮህ፣ ስታነባና ማን ይህን ሁሉ እንደፈጸመባት ስትናገር የነበረው ተረሳ?

በማዕከላዊ ሲደርስ የነበረው ግፍና መከራ፣ በስውርና በግለሰብ ማጎሪያ ቤቶች ውስጥ ሲፈጸም የነበረው አሰቃቂ ተግባር በማን ይከናወን እንደነበር የኦሮሞ እናቶች ይረሱታል? ጥፍራቸው የተነቅለና ጀርባቸው የተተለተለ፣ እንዲሁም አካላቸው የጎደለ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ውሸታሞች ናቸው? ስንቱ ቤት በሃዘን ተመታ? ስንት ህጻናት ያለ አባት ቀሩ? ስንቱ ተሰደደ? ይህ ሁሉ ተረስቶ የኦሮሞ ልጆችን ገሎ ትህነግን ለማንገስ ሩጫ!! የዘመናችን አሳዛኝ ታሪክ። በኦሮሞ ላይ የተፈጸመ ታላቅ ክህደት። እንዴትና በምን መስፈርት ለኦሮሞ ሕዝብ እታገላለሁ የሚል ኦሮሞ ወይም ድርጅት ከትህነግ ጋር ሆኖ ወገኑን ይገላል? በዚህ ደረጃ “የድብዳቤ ውጤት ናቹህ” ብሎ በታወረ ልቡና ለሚሳደብ ድርጅት ኦሮሞ ተላልፎ ይሰታል? ከዛስ ምን ይከተላል? ቆም ብሎ ማሰብ ደግ ነው።

Hundreds killed since start of Oromo protests | Africa | DW | 12.11.2016
ጥቁር ጠባሳ የጣለው ኢሬቻ ሰላባዎች

ዛሬ ትህነግ “ከፍለክ መንገዱን ቸርቅ ያድርግልህ” ሲልባል ” አልገነጠልም፣ ሞኛችሁን ፈልጉ” ያለው ለምን ይሆን? ማንን ሊያልብ? ማንን ሌላጭ? ማን ላይ ማንን ይዞ እንደ መሽገር ሊጣበቅ አስቦ ይሆን? ኦሮሞንስ ካሁኑ ወለጋና ምናምን ብሎ መጀፋፈልን ምን አመጣው? “ቅጂ ኦሮሞ ነህ” የተባልከው አንተ ከማን አንሰህና ወርደህ ነው “ቅጂ” የምትሆነው? ቆምና አስብ። እናስብ።

ሁንዴ ደንደና – ከጥቁር

ጽሁፉ የጸሃፊ አቋም ብቻ ነው፤ መልስ ያላችሁ ብትልኩልን እናስተናግዳለን

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2650 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply