ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ውጭ አማራጭ ገበያ እየፈለገች ነው

አሜሪካ የኢንዱስትሪ ምርቶች ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገሯ ገበያ እንዲገባ ይፈቀድ የነበረው ስምምነት (AGOA) እንዲቋረጠ በፕሬዜዳንቷ ጆ ባይደን አማካኝነት ውሳኔ ማሳለፏ ይታወሳል። ይህ የአሜሪካ ውሳኔ በርካቶችን ከስራ ውጭ የሚያደርግ ውሳኔ መሆኑ በተደጋጋሚ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በAGOA ምክንያት ይገኝ የነበረው የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት አማራጭ ገበያ እየፈለገች መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ፥ ” የገበያ መዳረሻዎቻችን በሪፎርም ስራዎች ውስጥ አንዱ ዋና ስራ ተደርጎ ከተወሰዱት የገበያ መዳረሻዎች ማስፋት ነው። ከዚህ አኳያ AGOA በተሰጠን እድል መሰረት አሜሪካ ያለንን የገበያ እድል ሌላ ጋር መፈለግ ማለት ነው። ሌሎች ሀገራት በዚህ አይነት ሁኔታ የተጠቀሙ ብዙ አሉ። ጫናና ማዕቀብ ሲጣልባቸው ከሌሎች ሀገራት ጋር ተደራድረው ያንን ምርቶቻቸውን ሌሎች ሀገራት የተቀበሏቸው አሉ። ኢትዮጵያም ያንን እያሰበችበት ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ አክለው ፤ በኮቪድ-19 ጊዜ የአለም ገበያ ሲዘጋ ለኤክስፖርት ተብለው የተመረቱ እቃዎች በሀገር ውስጥ መሸጥ እንዲችሉ እድሉን መንግስት አመቻችቶ ነበር ይሄም አንዱ መታየት ያለበት መሆኑን አንስተዋል።

ዶክተር ፍፁም አሰፋ ፥ ጦርነቱ ኢትዮጵያ ልማት ላይ ልታውል ያቀደችውን ገንዘብ ለጦርነት እንዲውል ስለሚደረግ ኢኮኖሚያዊ ጉዳቱ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ዜጎች ኢኮኖሚውን ለመደገፍ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ግኝት ለማሳደግ በህጋዊ መንገድ ገንዘብ እንዲልኩ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia

ኢትዮጵያ የጤናማ አመጋገብ መመሪያን ይፋ ልታደርግ ነው
በኢትዮጵያ የጤናማ አመጋገብ መመሪያ [dietary guideline] ከአንድ ወይም ከሁለት ወር በኋላ ይፋ …
Gunmen burn eight Lapsset road construction vehicles in Lamu
In Summary •Officials said the gang fired and detonated explosives at the …
Violence triggers diplomatic push to save Sudan
Summary At least 72 people have so far been killed and 2,300 …
“የምንወዳደረው ከብዙ ሯጮች ጋር ነው” አብይ አሕመድ ለታላቁ ሩጫ
… የኢትዮጵያ ሩጫ አሸናፊ ሆኖ ብቻ እንዲጠናቀቅ አንፈልግም። ኢትዮጵያችን ሪከርድ እንድትሰብር ጭምር …
ዳያስፖራው ያሰባሰበውን ገንዘብ በማጭበርበር ወደ ሌላ አካውንት ያዘዋወሩ የንግድ ባንክ ሰራተኞች ተያዙ
ለተፈናቀሉ ወገኖች የተሰበሰበን ገንዘብ በማጭበርበር የተጠረጠሩ የንግድ ባንክ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን …
ሱዳንና ኢትዮጵያ በቁልፍ ጉዳዮች መስማማታቸው ተሰማ- “የትህነግ መጨረሻ ግልጽ እየሆነ ነው”
ኢትዮጵያ የሱዳንን ቀውስ ለማስታገስና የሲቪል መንግስት እንዲቋቋም በዝርዝር ያልተቀመጠ ድጋፍ እንድታደርግ ጥያቄ …

Leave a Reply