በሀሰተኛ መረጃዎች ትምህርት አቁመው የነበሩ ት/ቤቶች ወደ ማስተማር ስራቸው መመለሳቸው ተገለፀ

ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት በአዲስ አበባ የሚገኙ የማህበረሰብና ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ጫና አድሮባቸው የመማር ማስተማር ስራቸውን እንዲያቆሙ ለማድረግ ጥረት ሲደረግ እንደነበር የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታውሷል።

በዚህ ጥረትም ጥቂት ት/ቤቶች የመማር ማስተማር ስራቸውን ለተወሰነ ጊዜ እንዲያቆሙ አድርጓቸው ነበር፤ ይህንንን ትምህርት ሚኒስቴር ባደረገው ምልከታ እና በወላጆች ጥቆማ ለመረዳት ተችሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር በተነዛው ሀሰተኛ መረጃ ላይ ተመስርተው የመማር ማስተማሩን ስራ ያቋረጡ 7 የማህበረሰብ ት/ቤቶች እና 19 ዓለም አቀፍ ት/ቤቶች ያለምንም በቂ ምክንያት ትምህርት ስራውን ማቆም እንደማይችሉ በይፋ አሳውቋቸዋል።

ሚኒስቴሩ የመማር ማስተማር ስራውን ያቋረጡ 3 ዓለም አቀፍ እና የማህበረስብ ትምህርት ቤቶች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንዲደርሳቸው አድርጓል።

ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ትምህርት ቤቶች ፦

– ሳንፎርድ ዓለም አቀፍ ት/ቤት

– ቤንግሃም ት/ቤት

– የዓለም አቀፍ ኮሚኒቲ (ICS) በተለምዶ የአሜሪካ ት/ ቤት ናቸው።

ትምህርት ቤቶቹ የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ወዲያው የፊት ለፊት የመማር ማስተማር ስራ እና በኦንላይን ከሀገር የወጡ መምህሮችን በመጠቀም ትምህርት መጀመራቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።

በህብረተሰቡ ላይ መደናገር ለመፍጠር እየተደረጉ ያሉት ጥረቶች የተቀናጀ ሀሰተኛ መረጃ የመንዛትና ዜጎችን ፍርሃት ውስጥ ለመክተት ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን የሚያሳዩና የሽብር ቡድኑ ህወሓት መጠቀሚያ መሆኑን በግልፅ የታየበት ነው ብሏል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ በሰጠው መግለጫ።

@tikvahethiopia

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2654 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply