አፍሪካ የወከለቻቸውን ኦባሳንጆ “ቺምፓንዚ” በሚል መዘለፋቸው በጥቁር አክፍቲቪስቶች ዘንዳ ቅሬታ አስነሳ፤


የትግሬ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር አፈ ቀለጤ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ካስታወቁ በሁዋላ የአፍሪካ ሕዝብረት በምስራቅ አፍሪቃ ከፍተኛ ተወካይ የሆኑት  ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ላይ የትህነግ ደጋፊዎችና የሚዲያ አንቂዎች ዘመቻ ከፍተዋል። “ቺምፓንዚ” በሚል አስነዋሪ ስድብም እየሰደቧቸው ነው።

Image

የትህነግ ተቃዋሚ ይል የነበረውና አሁን ላይ ግንባር ቀደም የትህነግ ደጋፊና የፕሮፓጋንዳ ሰራተና ሆኖ እያገለገለ ያለው አበበ በላይ በቲወተር ገጹ “ማስጠንቀቂያ” ሲል እንዳሰራጨው ለሰላም ተልዕኮ ወደ መቀለ ያመራው የልዑክ ቡድን ምን አልባትም ለድሮን ጥቃት መረጃ የሚያቀብል ወይም ጠቋሚ የስለላ መሳሪያ ይዘው ሄደው ሊሆን እንደሚችል ተላዝቦ አመላክቷል።

ሌላው የትህነግ ደጋፊና ግንባር ቀደም አቀንቃኝ በመሆን የሚታወቀው ገብረሚካኤል “ኦባሳንጆ የሚባል ቺምባንዚ ወደ መቀሌ ሄዶ እንደተመለሰ ብልጽግና መቀሌን እንደመታ እየተወራ ነው። ይህ እውነት ከሆነ ኦባሳንጆ እጁ ላይ ዳታ ያለው ሰአት አስሮ እንዳይሆን እጠራጠራለሁ።” ሲል በቲውተር ገጹ ላይ አስፍሯል።

ለወትሮው የአየር ትቃት ሲሰነዘር በምስል አስደግፈው የሚያሰራጩት የትህነግ ቃል አቀባይ የድሮን ጥቃት ስለመፈጸሙ፣ የተፈጸመውም በሲቪል መኖሪታ አካባቢ መሆኑንን ከመግለጻቸው ሌላ ያሉት ስለደረሰ አደጋ በዝርዝር ያሉት ነገር የለም።

ዛሬ ማለዳ ላይ አቶ ጌታቸው ይህን ያስታውቁ እንጂ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎትም ሆነ ከሌላ አካል እኩለ ለሌት ላይ ተፈጸመ ስለተባለው የድሮን ጥቃት ምንም አልተደመጠም።

መቀለ በትክክል ስሙ ባልተጠቀሰ ቦታ ተፈጸመ ስለተባለው የአየር ጥቃት እዛው የሚገኘው የጀርመን ድምጽ ሪፖርተር ደረሰ ስለተባለው ጥቃት ዝርዝር መረጃ አልሰጠም። አቶ ጌታቸውን ወይም ሌሎች የሚመለከታቸውን አየያም የራሱን እያታ አላሰማም። አንድ የከተማ ነዋሪ በስክል ምስክርነት መስጠታቸው ተሰምቷል። ምስክሩ ሲናገሩ እየተተረጎመ በቀረበው ሪፖርት ድምጽ ሲሰሙ ከተኙበት መነሳታቸውን፣ አካባቢው የወታደራዊ አለመሆኑና፣ ደጋሚ ለማጥቃት ስጥመጣ ድሮን መሆኗን እንዳዩ፣ ድምጿ የሚረብሽ እንደሆነ፣ ልጆች ድምጿን ሲሰሙ መውደቃቸውን አስታውቅዋል። ምስክሩም ሆኑ ማንም አካል የጉዳቱን መጠን ይህ እስከታተመ ድረስ የገለጸ የለም።

የቀድሞ የናይጀሪያ መሪ የጀመሩትን የሰላም ሂደት አስመልክቶ ያሉት ምንም ነገር ሳይኖር እየተሰነዘረባቸው ያለው ክብረነክ ስድብና አስተያየት፣ አቶ ጌታቸውም ” አብይን ለማዳን እንደመጡ ነግረናቸዋል” በማለት በትግርኛ ያሰራጩት ሃሳብ ተዳምሮ ቅሬታ ማስነሳቱን አሜሪካ የሚገኘው ተባባሪያችን አመልክቷል። በአሜሪካ የሚገኙ ጥቁር አክቲቪስቶች ይህንን ጉዳኡ ሰምተውና ጽሁፉ ተተርጉሞላቸው ከአፍሪካ ሕዝብረት ጋር ግንኙነት መጀመራቸው ታውቋል።

Image

ኦባሳንጆን በዚህ ደረጃ አውርዶ መስደብና መዝለፍ ለምን እንደተመረጠ ግልጽ እንዳልሆነላቸው ያመለከቱት አክቲቪስቶቹ ” ተሳዳቢዎቹ ከናይጀሪያም ሆነ ከኦባሳንጆ ተሽለው የሚገኙበት ነገር ቢኖር ዓለም የሚያውቀው አንድ ሃቅ ነው። እሱንም ያውቁታል” ሲሉ በብስጭት አስተያየት የሰጡት አክቲቪስቶች ጉዳዩ ለናይጀሪያ የስራ አገሮቻቸውም እንደተላከ አስታውቀዋል።

ለጊዜው ስማቸውን ያልገለጹ ታዋቂ የመብት ተሟጋች፣ እንዲህ ያለውን ጸያፍ ንግግር ማረቅ እንደሚገባ አመልክተው በጉዳዩ ላይ ደውለው መረጃ የጠየቋቸው አካላት መኖራቸውን አመልክተዋል።

የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ኦባንሳጆ ገና ለዚህ ተግባር ሲሾሙ የትህነግ አመራሮች አቶ ጌታቸውን ጨምሮ እንደማይቀበሏቸው ማመልከታቸው አይዘነጋም። ከጅምሩ “አንቀበላቸውም” ከተባሉት ሰው ጋር ስለተደረገው ውይይት ዛሬ ረፋዱ ላይ በትግርኛ “እንድታውቁት” በሚል በቲውተር ገጻቸው ላይ የሰላም ድርድሩ ተስፋ የሌለው እንደሆነና መንግስትን መገልበጥ ብቻ አማራጭ ሆኖ እየገፉበት እንደሆነ አቶ ጌታቸው ለትህነግ ደጋፊዎች ገልጸዋል።

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2661 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply