የሕዝብ ጎርፍ ትህነግን እንደማይፈልግ አጥብቆ አስጠነቀቀ፤ “እጃችሁን አንሱ” ሲል ተማጸነ

በአገር ቤት በተለያዩ ከተሞች አዲስ አበባን ጨምሮ ጠጠር መጣያ እስኪጠፋ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባርን ” አንፈልግም” ሲል በተደጋጋሚ አውግዟል። በውጭ አገር ያሉ ዜጎችም በተለያዩ ቀናት ይህንኑ ሲያደረጉ ነበር። ዛሬ ግን በሎንደን፣ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ፣ ካናዳና እስራኤል ለተቃውሞ የወጣው ሰው ብዛት እጅግ ሰፊ የተባለ ነው።

ሁሉም ድምጻቸው አንድ ሲሆን መፍክራቸውም ” አንገፈገፈን ወይም በቃ፣ በቃን ” የሚል “no more” ነበር። በዚህ መፈክራቸው በርካታ የውጭ ዜጎች ድጋፍ መስተታቸውን ተመልክተናል። የምዕራብ አገራት ሚዲያዎችና ሲ ኤን ኤን በተናበበና በተጠና መንገድ ኢትዮጵያ ላይ እያካሄዱ ያሉትን ፈር የለቀቀ ዘመቻ አበክረው በመረረ ቃል ያወገዙት ኢትዮጵያዊያኑ ” ተውን” ሲሉ አስጠንቀቀዋል።

ህጋዊ የኢትዮጵያ ፓርላማ በአሸባሪነት የፈረጀውን ድርጅት፣ ሕዝብ ” በቃኝ” ብሎ ያነቀለውን ድርጅት መልሶ ወደ ስልጣን ማምጣት መዘዙ ብዙ እንደሆነ፣ በአሜሪካና በምዕራብ አገራቱ የሃሰት ስብከትና ዕርዳታ ይህ አሸባሪ ድርጅት ጉዞው ካልቆመ መጨረሻው የተበላሸ ሊሆን እንደሚችል በሚያሳይ መልኩ የተዘጋጀው ሰላማዊ ስልግ እጅግ የተሳካ እንደነበር አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

በማይካድራ ጭፍጨፋ የተሳተፉ ወደ እስሬኤል መግባታቸውን ስም በመጠቀስ ያስታወቁ የቴላቪቭ ሰለፈኞች እጅግ ቁጣ ይታይባቸው እንደነበር ከስፍራው የተገኘ ገልጿል። መንግስትም ጉዳዩን እንደሚያጣራው ቃል መግባቱን አመልክቷል።

ይህ ከነገ ጀምሮ በሚዲያ ፕሮፓጋንዳ ኢትዮጵያን ለማስጨነቅ የተነሳው ሃይል ሱዳን ላይ መከተሙ በተጋለጠበት ቀን የተደረገው ሁሉ አቀፍ ሰልፍ ዜጎች በወሬ እንዳይፈቱ እንደሚያስችላቸው ተመልክቷል።

“በፈተና ዉስጥ እያለፍን አንድነታችን ግን ከብረት እየጠነከረ ነው” ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለወገኖቻቸው ክብር ሰጥተዋል። “ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱን ነብርም ዥንጉርጉርነቱን ከቶ ሊለዉጥ አይቻለውም” ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ፤ “በአራቱም የዓለም ክፍል የምትገኙ የኢትዮጵያ ልጆች አንዳንድ ምዕራባዉያን ሀገራት እና ሚዲያዎቻቸዉ ከሀገር ዉስጥ የእናት ጡት ነካሽ ባንዳዎች ጋር ሕብረት በመፍጠር ኢትዮጵያን ለማፍረስ የከፈቱብንን የዉክልና ጦርነትና በቀደምቶቻችን ደምና አጥንት የቆመዉን የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና ክብር የሚነካ ጣልቃ ገብነት ተቃዉማችሁ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ከያላችሁበት ተሰባስባችሁ በአንድነት በአደባባይ ድምፃችሁን በማሰማታችሁ ኮርተንባችኃል” ሲሉ አወድሰዋል።

በህልውና ዘመቻው “በፈተና ዉስጥ እያለፍን አንድነታችን ግን ከብረት እየጠነከረ ነው ፤ አሁንም እንበረታ !እንፅና!” ሲሉም ከንቲባዋ በማህበራዊ ገጽ አምዳቸው ጥሪ አሰምተዋል።

ሰቦቃ በሪ የተባሉ የሰልፍ ተሳታፊ ” ዘራፊዎቹ በገቡበት ሁሉ የቻሉትን አግዘው፣ ያልቻሉትን አውድመዋል። አሁን የቀራቸው ደብረብርሃንና የኦሮሞ ከተሞችን መዝረፍ ነው። ሁሉም ሊነቃ ይገባል። ሕዝብ እንደማይፈልጋቸው ስለሚያውቁ ከዝርፊያና አገሪቱን አመድ ከማድረግ የዘለለ ህልም የላቸው። ሳይቃተል በቅጠል” ሲሉ ያለ ዩሉንታ በነሱ ክፋት መጠን መመከት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

“ሲገሉን ይጨፍራሉ፤ ሲነኩ ይጮኻሉ” ያለው አያሌው ሃይሉ ” ጦርነት ውስጥ ነን። አማራ ክልል አመድ ሆኗል። ህዝብ በጅምላና በተናተል ተጭፍጭፏል። በሁሉም አቅጣጫ ጥቃት ተከፍቶ ክልሉን ማጽዳት፣ ለዚህም የሚደረገውን ሁሉ ማድረግ ግድ ነው” ሲል በሚሰማው የምሬትና የለቅሶ ዜና መማረሩን አመልክቷል።

27 ከተሞችን የናጠው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያዊያን ተቃውሞ ከደቡብ አፍሪካ እስከ ዋሽንግተን ዲሲ ኋይት ሃውስ


ኢትዮጵያዊያን ፣ኤርትራዊን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች አሜሪካ የኢትዮጵያን እጅ ጠምዝዛ ህልውናዋን የሚፈታተን ፖሊሲ ለማጫን እያደረገች ያለውን ጥረት የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ በኋይት ሃውስ ቤተመንግስት ፊት ለፊት አድርገዋል።

ሰልፈኞቹ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ በተለይም የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦችን በመከፋፈል ላይ የተመሰረተ ፖሊሲዋን እንድታርም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያን እጅ ለመጠመዘዝ የሚደረግ ሙከራ የአፍሪካን ነጻነት መግፈፊያ ዳግም የቅኝ አገዛዝ ፖሊሲ አካል በመሆኑ “#NoMore” በሚለው መሪ መፈክራቸው ተቀባይነት እንደሌለው አስገንዝበዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ አደባባይ በርካቶች በተካፈሉበት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የኢትዮጵያን የአፍሪካ የነጻነት አርማነቷን፣ወራሪዎችን አሳፍራ የመለሰች የጀግኖች አገር መሆኗን ፣ከጥቁር ህዝቦች በብቸኝነት በቅኝ አገዛዝ ጥላ ስር ያልወደቀች አገር መሆኗን በማስታወስ አሜሪካ የተሳሳተ ፖሊሲዋን ከማራመድ እንድትቆጠብ ጠይቀዋል።

የህወሓት የሽብር ቡድንን መደገፍ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድን እና መላ አህጉሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል አካሄድ መሆኑን የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር እንዲገነዘብ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል

በዛሬው ዕለት ብቻ በአምስቱ አለማችን ክፍለ አህጉሮ በሚገኙ 27 የዓለማችን ከተሞች ከደቡብ አፍሪካ እስከ ዋሽንግተን ዲሲ ኋይት ሃውስ በርካቶች የተሳተፉበት ትዕይንተ ህዝብ መካሄዱ ትኩረትን የሳበ አጀንዳ ሆኗል።

ቀደም ብሎ በእስራኤል እና እንግሊዝ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎችም በተመሳሳይ ብዛት ያለው ህዝብ በመሳተፍ የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን የሀሰት ዘገባ እና መንግስታት በምርጫ ወደ ስልጣን የመጣ መንግስትን ለመጣል የሚያደርጉትን ጥረት ክፉኛ ኮንነዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም በውጭ የሚኖረው አገር ወዳዱ ህዝብ ለአገሩ አንድነት መጠበቅ እያሳየ ላለው አጋርነት በማህብራዊ ትስስር ገፃቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Leave a Reply