ሁሉም የብልጽግና ስራ አስፈጻሚ “አገር ወይም ሞት” ሲሉ ወሰኑ፤ ወደ ግንባር ያመራሉ

“ትህነግ 2 ሚሊዮን ሃይል አሰልፏል። ውጊያው የተለመደው ዓይነት ባለመሆኑ እየተሹለከለክ የሚመጣውን ሃይል በመጣበት አግባብ መመለስ እግባብ ነው። ሃያላን አገራት በቁስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በኢኮኖሚ፣ በሚዲያ፣ በረቀቀ ሃይል የሚረዱት ይህ ወራሪ አገር ሳያጠፋ እነሱ መጫትና ሕጻናት ሳይቀር አሰማርተው ወረራን እንደከፈቱ ሕዝብ በያለበት እርምጃ ሊወስድ ይገባል። አሁን ጦርነቱ ያልገባቸው ሕጻናትን እየማገደ ያለውን ሃይል ሕዝብ የአገሩን ክብር ለማስጠበቅ እንዲነሳ… የፓርቲው ስራ አስፈጻሚም ግንባር ለመግባት ወስነናል”

” ከፓርቲው ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጀምሮ አተቃላይ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ወደ ግንባር በማምራት መስእዋት ሆነው ኢትዮጵያን ለማዳን መወሰናቸውን ዶ/ር አለሙ ስሜ አስታወቁ። ” መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፀጥታ አካላት በቅንጅት ተዘጋጅተው ወደተለየ እርምጃ ይገባሉ ፤ ይህ ምንም ጥያቄ የለውም፤ ለውጥ ይኖራል ” ሲሉ የመከላከያ ሚንስተሩ አስታውቀዋል።

ዳንኤል ክብረት የጠላት ትዕቢት እያየለ ሄዶ፣ የሕዝብ ትዕግስት እያለቀ በአንድነት የሚገናኝበት የጋራ ነጥብ ላይ መድረሱን በማስታወስ ነገሮች እንደሚቀየሩ ቀደም ሲል መግለጻቸው ይታወሳል። ሕዝብ በያለበት ተደራጅቶ፣ በክተት የተመመው አንድ ሆኖ፣ ከየክልሉ የተነሳው ተሳስሮ ከመከላከያ ጋር የተናበበ ሁሉ አቀፍ ጥቃት የማይወስዱት ለምንድን ነው? የሚለውን ወቅታዊ ጉዳይ በሚመለስ መልኩ የመከላከያ ሚኒስትሩ እንደጠቆሙት በሁሉም አቅጣጫ ኦፕሬሽን በይፋ ይከፈታል።

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክሮ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን የመንግስት መገናኛዎች አመልክተዋል። “ሊጠፉ ሻንጣ ይዘው ተነስተዋል” የሚለው የትህነግ የተቀናጀ ቅስቀሳ በተጀመረበት ዕለት ስራ አስፈጻሚው ” ቅድሚያ አገር፣ ከአገር በላይ ምንም የለም። መስዋዕት ሆንነ አገር እናድናለን” ሲሉ ከፊት እንደሚሰለፉ ለሕዝብ ይፋ አድርገዋል።

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት በውስጥም በውጭም የተከፈተባት ጥቃት የተቀናጀ መሆኑን ገልጾ፤ ሽብረተኛ ተብሎ የተፈረጀው ትህነግናና ግብረአበሮቹ በኢትዮጵያ እስካሁን ለደረሰው ጥፋት ተጠያቂ መሆናቸውን አስታውቋል። ማስታወቅ ብቻ ሳይሆን ተጠያቂነታቸው ተግባራዊ እንደሚሆን አመልክቷል። ውጊው አሁን ካለው የበለጠ ኪሳራ እንዳያደርስ ከነገ ጀምሮ ሁሉም የፀጥታ አካላት ወደተለየ እርምጃ እንደሚሸጋገሩ ተመልክቷል።

ዶ/ር አብርሃም በላይ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ፥ ” መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፀጥታ አካላት በቅንጅት ተዘጋጅተው ወደተለየ እርምጃ ይገባሉ ፤ ይህ ምንም ጥያቄ የለውም፤ ለውጥ ይኖራል ” ሲሉ መናገራቸውን ቲክቨሃ ዶክተር አለሙ ስሜን ጠቅሶ አስታውቋል።የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በስብሰባው ላይ ከዚህ በኃላ ሁሉም አመራር በየጦር ግንባር እየተገኘ የህልውና አደጋውን ለመቀልበስ ከፊት ሆኖ እንደሚሰለፍ አሳውቋል።

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ዶክተር አለሙ ስሜ ” የብልፅግና ስራ አስፈፃሚ ከፓርቲያችን ፕሬዜዳንት (ከሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር) ጀምሮ ወደ ግንባር መግባት እንዳለብን በእርግጥ ሌሎች ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ የተወሰነ የልማቱን ስራ ፣ የዲፕሎማሲውን ስራ፣ ከቢሮ የሚሰራውን ስራ እንድንሰራ ሌሎች ከዚህ ውጭ ያለን ከፓርቲያችን ፕሬዜዳንት ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ጨምሮ ወደ ግንባር ሄደን እኛ መስእዋት ሆነን ኢትዮጵያን ለማዳን ወስነናል፤ ይሄንንም በተግባር ከነገ ጀምሮ በመንቀሳቀስ የምናሳየው ይሆናል ” ብለዋል።

ትህነግ በገባባቸው ከተሞች ሕዝብ የከተማ ውስጥ ትግል እያደረገና ሲመቸውም እርምጃ እየወሰደ መሆኑንን ከየአቅጣጫው እየተሰማ ነው። ከከሚሴ የተበተነ የተባለው የትህነግ ሃይል አስጊ እንዳልሆነ፣ ይልቁኑም አሁን የተንቀሳቀሰውን የክተት ዘማች በማስተባበር አደን ቢጀመር ሊቋቋም እንደማይችልም አስተአየት እየተሰጠ ነው። ከነገ ጀምሮ በሁለኡም አቅጣጫ ዘመቻው በይፋ እንደሚጀመር ሲገለጽ ቴክኒካል ጉዳይ ባይገለጽም በየስፋርው የገባውን ሃይል ማደን የዘመቻው አንዱ አካል እንደሚሆን ግምት አለ።

ግንባር ያሉት የአብን ስራ አስፈጻሚ ” በግንባር ያለው አሰልካለፍ ተስተካክሏል። እመኑኝ በቅርቡ ድል አለ” ሲሉ ስለ ግንባሩ ሁኔታና መከላከያ ላይ ዘር የቆጠሩ ነዋሪዎች በከተማ ውስጥ ሆነው ስለፈጸሙት ክህደት ማስረዳታቸው የሚታወስ ነው። ሰሞኑንን ተማርከው ቃላቸው ሲሰጡ የታዩት የትህነግ ታጣቂዎች ” በገባንበት ሁሉ በታዘዝነው መሰረት ሴቶችን በቡድን ደፍረናል። ከተማ አውድመናል። የቻልነውን ዘርፈን አግዘናል። የተረፈ ነገር የለም። ያልደረሰ ዕህል ጨፍጭፈናል። አማራው ቀና እንዳይል አድርጉ በተባለው መሰረት አድርገናል” ሲሉ የተሰማበት ቪዲዮ በህዝብ ዘንዳ ክፉ ስሜት ፈጥሯል። በውጭና በአገር ውስጥ የሚነገረውም ይህ ነው። ቁጣው ወደ ሃይል እንዳይቀየር አስቀድሞ የሚዲያ ዘመቻ ለመጀመረ ዝግጅት ያደረገው የትህነግ ሃይል ከወዲሁ ” አዲስ አበባ ልንገባ ነው” እያለ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ጦርነት ላይ መሆናቸውን በመርሳትና እነሱ እየገደሉ ሌላው እንዳይነካቸው ራሳቸውን የመከላከል ጥሪ በሚዲያ እያሰሙ መሆኑንን ዜጎች በንዴት እየገለጹ ነው።

ዜናው ቲክቫህን ጨምሮ ከተለያዩ ሚዲያዎች የተቀናጀ ነው

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2661 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply