የኦሮሞን ህዝብ ለማደናገር ሸኔ በሚል የተደራጀው አሸባሪ ቡድን እድል ተሰጥቶት ወደ ስልጣን ከመጣ በቀሉ የሚከፋው በዋናነት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ነው።
የሕወሓትና የሸኔ ጥምረትም የስም ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ሁለቱም አንድ ናቸው ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይና ደህንነት ቋሚ ኮሚቴ አባል እና የኦነግ መስራች የሆኑት ዲማ ነገዎ(ዶ/ር) አስታወቁ።
ዶ/ር ዲማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት አስተያየት፣ አሸባሪው ሕወሓትና ሸኔ የስም ልዩነት ካልሆነ በስተቀር በተግባርም በዓላማም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች በመሆናቸው ሁለቱን የተለያዩ አካላት አድርጎ ማየት አይገባም።
አሸባሪው ሕወሓት ዛሬ ህዝቡን ለማደናገር የኦሮሞ ህዝብ ወገንተኛ ለመምሰል ከፍተኛ መፍጨርጨር እያደረገ መሆኑን ያነሱት ዶ/ር ዲማ፣ ዳሩ ግን በታሪክም ሆነ በተግባር ወደኋላ መለስ ተብሎ ከተቃኘ ቡድኑ በማስተር ፕላን ምክንያት በርካታ የኦሮሞ ወጣቶች በጠራራ ፀሐይ ያለምንም ርህራሄ በጥይት የፈጀ፣ ይሄ ሳያንስ የእሬቻ በዓል ለማክበር የወጡ የኦሮሞ ንጹሃንን በመጨፍጨፍ ጥቁር ጠባሳና ዘግናኝ ድርጊቶችን ጥሎ ያለፈ ቡድን መሆኑን አስታውሰዋል ።
የሽብር ቡድኑ ፍላጎት ትናንትም ዛሬም ኦሮሞን በመስበር የኦሮሞን ሀብት መውረስ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ዲማ፣ ለዚህ ዓላማ ማሳኪያም እውነተኛ የኦነግ ታጋዮችን በመግደል እንዲሁም በማሰር በሕይወት የተረፉትን ከአገር በማባረር ከአሥር ዓመታት ወዲህ ደግሞ ተላላኪውን በማደራጀትና በኦሮሞ ስም አምሳያውን ቡድን በማቋቋም ኦሮሞን የማደናገር ሥራ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
ቡድኑ ኦሮሞን ለማደናገር በኦሮሞ ስም ሸኔ በሚል ስም ተደራጅቶ መምጣቱ ምናልባት ለማያውቁት ለአንዳንዶቹ ማደናገሪያ ቢሆንም እውነታው ግን የሕወሓት ትልቁ ዓላማ እንደ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለየ መልኩ ደግሞ የስልጣኑን እድሜ ያሳጠረውን ኦሮሞን ህዝብ ክፉኛ ለመበቀል መሆኑ መታወቅ አለበት ያሉት ዶ/ር ዲማ፣በቡድኑ አምባገነናዊ አገዛዝ በግፍ ያልተገደለ፣ያልተሰቃየና አገር ጥሎ ያልጠፋ ብሔር ባለመኖሩ የቡድኑ ዳግም ወደ ስልጣን የመመለስ ቅዠት ከንቱ ለማድረግ በጋራ መቆም ጊዜው አሁን ነው ብለዋል።
አሸባሪው ሕወሓት ትንሽ ቀዳዳ አገኝቶ ወደ ስልጣን የመመለስ እድል ካገኘ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንገቱን ደፍቶ የሚኖርባት የሰቆቃ ምድር እንደምትሆን የተናገሩት ዶክተር ዲማ ህዝቡ አገሩን ከምስቅልቅል፤ ራሱንም ከስቃይ ለመታደግ ብቸኛው አማራጭ በጋራ መታገል መሆኑንም አስምረውበታል።
በመጨረሻም የሽብር ቡድኑ በሸረበው ሴራ የህይወት መስዋዕትነት በመክፈልና በመፈናቀል እንዲሁም በውጭ ኃይሎች ጫና ሳይንበረከክ የጋራ ጠላቶቹን በአንድነት በጽናት እየተፋለመ ላለ ለኢትዮጵያ ህዝብም ምስጋና አቅርበዋል።
ምንጭ :ኢ.ፕ.ድ
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር… Read more: ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያ
- የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡየቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እግረመንገዳቸውን… Read more: የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡ
- Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamismPermitting foreign firm’s involvement in the import, wholesale and retail business, which… Read more: Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamism
- መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀMore stories የኢትዮጵያን ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት አቅም የሚያሳይ የጥናት ሰነድ ይፋ… Read more: መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀ